Get Mystery Box with random crypto!

ላለመጾም ምክንያት ከመፍጠር ምክንያት ፈጥሮ መጾም በእጅጉ ይጠቅማል፡፡ ደሀው ድኅነት ራሱ ጾም ነው | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

ላለመጾም ምክንያት ከመፍጠር ምክንያት ፈጥሮ መጾም በእጅጉ ይጠቅማል፡፡ ደሀው ድኅነት ራሱ ጾም ነው ካለ፤ ሌላው ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ራሱጾም ነው ካለ ለመጾም ክርስቲያን መሆን ሳይሆን ሀገር ወይም ዜግነትመቀየር ሊያስፈልግ ነው ማለት ነው? ምእመናን ‹‹ይህ የሽማግሌዎች ጾም ነው›› ካሉ ስለ ጾም ማስተማርና ጾመው ማሳየት የሚጠበቅባቸው ‹‹ሰባክያን›› ደግሞ ‹‹ቃለ እግዚአብሔር ይመትር ነደ እሳት›› እያሉ ጾምን ሽሮ ለመብላት ጥቅስ ከጠቀሱ ጾምን በጽሑፍ እንጂ በሥራ ላናውቃትነው ማለት ነው፡፡

ሐዋርያት እንደታዘዙት ዓለምን ሁሉ ለማስተማር ከመሰማራታቸው በፊት መጀመሪያ ያደረጉት ጾምን ነው፡፡ ሐዋርያት አልጾሙም ማለት ከላይ የተብራራው የኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢትና ምሳሌ ሐሰት ሆነ ማለት ነው፡፡ ሎቱ ስብሐት! ቃሉም ተፈጽሟል ሐዋርያትም ጾመዋል፡፡ እኛም ጾሙን ጾመን የምናስበውና የምንሠራው በጎ ሥራ ሁሉ ይከናወንልን ዘንድፈጣሪ በረድኤት አይለየን!

ይቆየን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

☞ t.me/An_Apocalypse