Get Mystery Box with random crypto!

ORACLE OF CHRIST

የቴሌግራም ቻናል አርማ oraclekb — ORACLE OF CHRIST O
የቴሌግራም ቻናል አርማ oraclekb — ORACLE OF CHRIST
የሰርጥ አድራሻ: @oraclekb
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 943
የሰርጥ መግለጫ

ወንጌል ለሁሉም!!!
“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4
@oracleKB

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 19:32:26 "★መንግሥት በአስቸኳይ ይህንን የርኩሰት ፊልም ያስቁም!"

★ ክርስቲያኖች ተጠንቀቁ!! " ፍልሰት" በሚል ርዕስ በቃና ቲቪ የሚተላለፈውን የሴት ሰዶማውያን /ሌዝብያን / ፊልም ፈጽሞ እንዳታዩ። ★ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፣የራሳቸውን ጥቅም እንጂ በትውልድ ሕይወት ላይ የሚያመጣውን መጥፎ ተጽኅኖ የማያገናዝቡ ስግብግብ ግለሰቦች ያገኙትን የውጪ ፊልም ሁሉ በገንዘባቸው እያስተረጎሙ ትውልድን እያረከሱ ሃገርን እያቆሸሹ ይገኛሉ።

ይህ "ፍልሰት" የሚል የማታለያ ትርጉም የተሰጠው ፊልም "Orfaos da Terra" ከሚል የፓርቹጋል ቋንቋ የተወረሰ ሲሆን የፊልሙ ዋና ዓላማ በስደትና በፍቅር ስም የሴት ሰዶማዊነትን /ሌዝቢያዊነትን/ በትውልድ ልብ ውስጥ ለማስገባትና ወጣቶችን በረከሰ ተግባር ለማጥመድ በምሥጢር ታቅዶ የተሰራ ፊልም ነው። ፊልሙ እጅግ በረቀቀ ዘዴ ወጣቶችን በመሳብ ልባቸውን እያንጠለጠለ የአዕምሮ እጥበት/Brain wash/ በማድረግ ሴት ከሴት ጋር በዝሙት መጨመላለቅን እንደ ዘመናዊነትና እንደ ሥልጣኔ ለማሳየት የተዘጋጀ አጋንንታዊ ፊልም ነው።

እንዳይታወቅባቸው ግን በጦርነት ምክንያት የሚፈጠር ስደት አስመስለው ነው ያቀረቡት። ፊልሙ በማር የተለወሰ መርዝ ነው።... ስለዚህም ይህ" ፍልሰት " በሚል ርዕስ በተከታታይ ለሕዝብ በይፋ በቃና ቲቪ የሚተላለፍ ነውረኛ ፊልም በአስቸኳይ መቆም አለበት።

@oraclekb
53 views✞ቃለ-አብ✞, edited  16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:31:50
44 views✞ቃለ-አብ✞, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 21:46:43 የምናመልከው እየሱስ እግዚአብሄር ሁሉን ነገር የፈጠረበት፣መጀመርያውም መጨረሻውም የሆነ፣እግዚአብሄር የተንፀባረቀበት፣እግዚአብሄር የተናገረበት፣በውስጣችን የተሰወረው የእግዚአብሄር ሚስጥር፣በሰማይ ያለው ብቸኛ አማላጃችን፣እግዚአብሄር የሀጥያት ይቅርታ የሚያደርግበት ብቸኛው መንገድ፣እግዚአብሄር አብ የሚታወቅበት ብቸኛው መንገድ፣ፅድቅም ጥበብም ቅድስናም ቤዛነትም ከእግዚአብሄር ዘንድ የሚገኝበት መንገድ፣እግዚአብሄር ፍቅሩን የገለጠበት፣የእግዚአብሄር አንድያ ልጅ፣እርሱን በማመን የሀጥያት ይቅርታ የሚያስገኝ፣የእግዚአብሄር ውዱ ስጦታ፣የዘለአለም ህይወት ያገኘንበት መንገድ፣በኛና በእግዚአብሄር ያለው መሀከለኛ፣ፀሎታችን ተሰሚነት የሚያገኝበት መንገድ፣ወደ እግዚአብሄር የሚያደርሰን መንገድ፣ከዘለአለም ፍርድ የሚያድነን መንገድ፣ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያስገባን በር፣እርሱን በማመናችን መንፈስ ቅዱስን ያገኘንበት መንገድ፣እግዚአብሄርን የምናመልክበት፣የነፍስ እረፍት የሰጠን፣የነፍሳችን እረኛ፣መዳን ያገኘንበት መንገድ፣የቤተክርስቲያን ራስ፣በሞቱ ከእግዚአብሄር ጋር ያስታረቀን፣የእግዚአብሄር ልጆች ያረገን፣በእግዚአብሄር ዘንድ ያለ ጠበቃችን፣ከሀጥያት ያነፃን፣የመለኮት ሙላት የሚኖርበት፣የእግዚአብሄር የተስፋ ቃሎች ፍፃሜ ያገኙበት፣የስብከታችን ርእስ፣እግዚአብሄር ስሙት ያለው አካል፣ከአዳም ጀምሮ ቅዱሳን ያመኑት፣የቤተክርስቲያን መስራችና መሰረት፣በእግዚአብሄር ቀኝ ያለ ሊቀ ካህናችን፣ስለ ስሙ መነቀፍ ከሁሉ የሚበልጥ ባለጠግነት የሆነለት፣የእግዚአብሄር ጥበብና የእግዚአብሄር ቃል፣ያለ እርሱ ምንም ማድረግ የማይቻል፣ወደ እግዚአብሄር ቤት መግቢያው በር፣የጥበብና የእውቀት መዝገብ ያለው፣የሰይጣንን ራስ የሚቀጠቅጠው የሴቲቱ ዘር፣ታላቁ አምላካችን፣መድሀኒታችን፣አዳኛችን፣የምንጠብቀው የተባረከው ተስፋችን እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ እየሱስ.....


እየሱስ ማነው ከሚል መፅሀፍ የተወሰደ

@oracleKB
61 views✞ቃለ-አብ✞, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:14:28
@oracleKB
87 views✞ቃለ-አብ✞, edited  18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 17:07:03 የሐይል እጥረት ገጥሞናል!

የዛሬ 15 አመት አካባቢ አንድ ወንድም ቤተክርስቲያንንና ትውልድን በፍጥነት እየወረረ እየመጣ ስላለው ጨለማ ሲናገር ሰምቼ ነበር፡፡ ያ ጨለማን በዚያም ጊዜ ይሁን አሁን በሚገባ እንደተረዳሁት የአለማዊነት ወረርሽን ነው፡፡ ሴኩላሪዝም ( አለማዊነት) የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የመታበት ጊዜ እንደአሁን ያለ አይመስለኝም፡፡

ለዚህም አንዱ ማስረጃው ብዙ አማኞች ህይወታችን ከማያምኑ ከሚባሉት በምንም የተሻለ አለመሆኑ ነው፡፡ በህይወት፣ በዕውቀት፣በስራ ውጤት፣ በአመራር እና በመሳሰሉት የተሻልን አይደለንም፡፡ «ክርስቲያን መሆን የሞትና የህይወት ውሳኔ መሆኑ ቀርቶ ከመንገድ አላፊ ከጎረቤት የሚኮረጅ የመጨረሻው ፋሽን የሆነም ይመስል በየመድረኮች ዘመናዊዎችና ስልጡን ንቁዎች እንዲሻሙት ብልጭልጭ ማስታወቂያ በዝቷል፡፡» ይህም ደቀመዝሙር ሳይሆን ደጋፊውችን አፍርቷል፡፡ ሌላው ማስረጃ በሀገራችንም ይሁን በመላው አለም ላይ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጣው ሰው ቁጥር የጨመረ ቢመስልም ቁጥር ብቻ እየሆነ ነው፡፡ አንዳንድ እስታስትቲኮችም እንሚያሳዩት በመደበኛነት ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው ሰው ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ ነው፡፡በአጠቃላይ ከፍተኛ የመንፈሳዊ ነገር ፍላጎት ማጣት እየታየና ለሌሎች ነገሮች ቅድሚያ መስጠት የተለመደ ሆኗል፡፡

የላቀ ህይወት ለመኖር ፍላጎት ቢኖረንም አቅመቢሶች ሆነናል፡፡ የምንሰማው ቃል ህይወታችንን ሊለውጠውና ክርስቶስን እንድንመስል ሊያደርገን አልቻለም፡፡ ቁሳቁሳዊነት እና ሸማችነት የተቆጣጠሩን ይመስላሉ፡፡ የአፋችን ቃልና ሕይወታችን እርስ በርስ ይጣረሳሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ፕሮቴስታንት ነን እያሉ እንደፈለጉ የሚኖሩ ሰዎች ህይወትን ቢያንስ በሃሳብ ደራጃ በአንድ ድምጽ እኛን አይወክልም ማለት አቅቶናል፡፡ ለምሳሌ ውሸት፣ ሌብነት፣ ሙስና፣ ብሔርተኝነት የመሳሰሉት የወንጌላውያን እምነት አይወክሉም በማለት በአደባባይ ለመገሰጽ የሞራል አቅም አጥተናል፡፡በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያጠፉትንም መገሰጽ ብርቅ እየሆነ መቷል፡፡

በርግጥ በሃሳብ የተለዩ የሚመስሉንን ሰዎች ኃጥያት እንደሰሩ ያህል እናወግዛቸዋልን፡፡ እናም ይህን ዘመን ስታዘበው በአጠቃላይ የመንፈሳዊ ነገር ፍላጎትና አቅም ያጣንበት ዘመን ነው፡፡ ለመንፈሳዊ ነገሮች ላለመትጋት ሰበባ ሰበብ የምናበዛ ሆነናል፡፡ ለዚህ ችግሮቻችን መፍትሔው ብዙ ቢሆንም አሁን ከምን ጊዜውም የበለጠ ግድአለሽ የሆነን እንደ ቤተክርስቲያን አካል በሰከነ እና በጠለቀ ሁኔታ አይኖቻችንን ከፍተን ሌላው ቢቀር የት እንደነበርን? የት እንዳለን? ወዴት እየሄድን እንደሆነ መመልከትና እርምጃ መውሰደ ይገባናል ብዬ አሳስባልሁ፡፡

ለችግሩ መፍትሔው ብዙ ሊሆን ቢችልም እኔ ዋና ነው ብዬ እያሰብኩት ያለው እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ወለድ ሪቫይቫል ነው፡፡ እውነተኛ መነቃቃት በልሳን መናገር ብቻና በማህበር ተሰብስቦ ሞቅ ባለ ሙዚቃና «በአስጨፋሪዎች» ላብ እስከሚያልበን መጨፈር አይደለም፡፡ እውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ሲመጣ አማኝ በቀጣይነት በመንፈስ ቅዱስ እየተሞላና የጌታን ወንጌል እያበሰረ በልዩ ልዩ የአገልግሎት ፀጋዎች ተሞልቶ በትጋት እና በመቀጣጠል እንደሚያገልግል እንዲሁም የኑሮ ፍሬ እንደያፈራ ያደርጋል፡፡ መንፈሳዊ አቅም እናገኛልን፡፡ መንፈስ ቅደስ እንደገና ጸጋውንና ሐይሉን ሲሞላን ነገሮች እንደነበሩ አይሆኑም፡፡ ጨለማው ይሸነፋል፡፡ የላቀ ህይወት ለመኖር መንፈሳዊ አቅም እናገኛለን፡፡ ለጌታ የተለየ ሕይወት ለመኖር፣ ለጸሎትና እንድንተጋ ያደርገናል፡፡ እውነተኛ የመንፈስ ቅደሱ ሪቫይቫል ከሚናፍቁ አንዱ ሆኛለሁ፡፡

እርሱ መንፈሱን እንደገና ያፍስልን፣ ጉብኙቱን አያዘግይብን፡፡ ወደ ራሱ ይመልሰን፡፡

በወንድም ዳንኤል ይልማ

Share it

@OracleKb
154 views✞ቃለ-አብ✞, edited  14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 17:59:46 የወንድማማች መዋደድ ይኑር።ዕብ 13-1

እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
( ሮሜ 12፡10)
እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ ።
(1 ተሰ 5፡14 )
እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ።
( ሮሜ 12፡10 )
እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።
( 1ጰጥ 4፡19 )
እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ
( ያዕ 5፡16 )
እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሱ።
( ኤፈ 4፡ 2 )
እርስ በርሳችሁ ተሸካከሙ።
ገላ 6 ፡ 2 )
እርስ በርሳችሁ አገልግሉ
( ገላ 5፡ 13 )
እርስ በርሳችሁ አቅኑ።
( ገላ 6፡1 )
እርስ በርሳችሁ ታነጽ።
1ቆሮ 3፡ 10 )
እርስ በርሳችሁ ተስማሙ።
( 1ቆሮ 1፡ 10 )
እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ
( ኤፈ 4፡ 25 )
እርስ በርሳችሁ አጽናኑ።
( 1ተሰ 4፡18)
እርስ በርሳችሁ በዝማሬ በመንፈሳዊ
ቅኔ ተነጋገሩ። ( ኤፈ 5-19)
እርስ በርሳችሁ በሰላም ሁኑ ።
( 1ተሰ 5፡12)
እርስ በርሳችሁ አምስተምሩና ገሥጽ
( ቆላ 3፡16)
እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ።
(ቆላ 3፡9)
እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።
( ቆላ 3፡13
እርስ በርሳችሁ ትዕግስትን አድርጉ
( ቆላ 3፡13)
እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች
ሁኑ። ( ኤፈ 4፡39)
እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካም
ለማድረግ ትጉ። ( 1ተሰ 5፡15)
እርስ በርሳችሁ በተቀደስ አሳሳም
ሰላምታ ተሰጣጡ። ( ሮሜ 16፡16)
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ሁኑ።
( ሮሜ 15፡6)

እንዋደድ ለ ክርስቲያን ወንድሞቻቹ Share አድርጉላቸው

Join us

@OracleKb
176 views✞ቃለ-አብ✞, edited  14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 22:44:03 የ ካታኮንቡ ሰማእታት

Share for others

@oraclekb
233 views✞ቃለ-አብ✞, edited  19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 09:43:28 የቸገረኝ ሌታ....

ሁሉ ሲጠምብኝ ፣ ሲሆን ያለ ዕቅዴ
ችግር ተደራርቦ ፣ ሲመጣብኝ በአንዴ
ለክፉ ቀን ያልኩት ፣ ጥሎኝ ሲሄድ ጓዴ
እጄ አቅም ሲያጥረው ፣ ደክሞ ሲዝል ክንዴ

በራሴ ሞክረው ፣ አልሆን ያለኝ ለታ
አንተን ልለምንህ ፣ ወዳንተ ብመጣ
አታባርረኝም ፣ ትቀበለኛለህ
መቼ እንደሰው አንተ ፣ ቂም ትቋጥራለህ

ግን ለምን....???

ይልቅ ፊትህ ልውደቅ ፣ በደስታዬ ወራት
ፍቅር ሰላም ደስታ ፣ ተድላ በበዛበት
አልርሳው ትናንቴን ፣ ባከበርከኝ ማግስት
ምህረትህ አይሁነኝ ፣ ለመጥፍያዬ ምክንያት

ትጎሳቆል ነፍሴ ፣ ትቅለጥ እንደሻማ
ተድላ እና ፍስሃ ፣ ከለያት ካንተማ
በክፉም በደጉም ፣ አትጣኝ ከፊትህ
ሌት ተቀን ልጠማህ ፣ ውዴ ሆይ እባክህ

yku

@OracleKb
288 views✞ቃለ-አብ✞, 06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:42:04 አፀዳድተን እንጠብቀው!!

ባለቤቴና እኔ ቤታችን እንግዳ የጋበዝን ለታ አይ የሽር ጉዱ ብዛት!

ማብሰያ ቤቱ ይፀዳል
መታጠቢያ ቤቱ ራሱ ይታጠባል
ወለሉ ልቡ እስኪጠፋ ይወለወላል
አልጋዎቹ ዘንጠው ይነጠፋሉ
ወንበር ጠረቤዛው በአግባቡ ስፍራውን ይዞ ይቀመጣል
መብራቶቹ ፍዋ ብለው በያሉበት ድምቀት ይጨምራሉ
መልካም ጠረን አየሩ ላይ ተሽ ተሽ ይደረግበታል
ምግቡ ደግሞ ባማረ ሁኔታ ተሰናድቶ እነሆ እያለ ይጠብቃል!

በማንኛውም መንገድ የእንግዳችንን ምቾት የሚነሳ አንዳች ነገር እንዳይኖር ልባችን ውልቅ እስኪል ድረስ ተዘጋጅተን እንጠብቃለን!

ተጋባዡ በቤታችን የሚኖረው ቆይታ ፍፁም ደስታን የሚፈጥርለት እንዲሆን እንጂ ምንም ዓይነት ቅሬታ እንዳይሰማው ጠብ እርግፍ ብለን ሁሉን አሰማምረን ስናበቃ በፈገግታ ውጭ ውጭውን እያየን እንጠብቀዋለን!

ታዲያ...........

ኢየሱስዬ እኮ ከየትኛውም ወዳጃችን
የሚበልጥ ተናፋቂ እንግዳችን ነው!!
ሃሌሉያ!!!

ልባችንን አፀዳድተን እንጠብቀዋ!!!
"እኛ ቤቱ ነን" እንዲል መፅሐፉ!

አሁን መንፈስ ቅዱስን ብንጠይቀው የፅዳቱን ዓይነትና መጠን ሰፈሩን ከነቀበሌው ከነቤት ቁጥሩ ይኸውልህ/ ይኸውልሽ / ያቺኛዋ/ ይሄኛው / ያኛው አየኸው አይደል? እያለ ዘርዝሮ አብጠርጥሮ ይነግረናል እኮ!

እኛ እሺ እንበል እንጂ መንፈስ ቅዱስማ ሁሌም ዝግጁ ነው!

ዛሬም መንፈስ ቅዱስ የአገልጋዮን የጳውሎስን አንደበት ተውሶ እንዲህ ይለናል!

"በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና: እንደ ንፅሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና"

2ኛ ቆሮ 11:2

ቸር ቆዮልኝ

ዘማሪ ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን
Join us
Join us
@oracleKB
278 views✞ቃለ-አብ✞, 12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 22:17:37
1ኛ ተሰሎንቄ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥
⁵ ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤
⁶ እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ።
⁷ የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፥ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤
⁸ እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤
⁹ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።
¹⁰ የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።
¹¹ ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።

@oracleKB
116 views✞ቃለ-አብ✞, edited  19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ