Get Mystery Box with random crypto!

የተመረጠ ትውልድ (The choosen generation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ onegodonlyjesuss — የተመረጠ ትውልድ (The choosen generation)
የቴሌግራም ቻናል አርማ onegodonlyjesuss — የተመረጠ ትውልድ (The choosen generation)
የሰርጥ አድራሻ: @onegodonlyjesuss
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.89K
የሰርጥ መግለጫ

Apostolic Church of Ethiopia believe in One God, Water Baptism
in the name of Jesus Christ
#እስራኤል_ሆይ_ስማ_አምላካችን_እግዚአብሔር_አንድ_እግዚአብሔር_ነው
#ዘዳ 6:4
☞ @onegodonlyjesusss
☞ @onegodonlyjesuss
🗣ስብከቶች🗣
✍የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች✍
🎵 መዝሙሮች🎶
🗣መንፈሳዊ ትረካዎች🗣
📝 ሕይወት ለዋጭ.....

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-19 22:56:22 አንድ አምላክ ብቻ አለ፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንድ አምላክ ብቻ ነው እንጂ ሰዎች እንደሚመስላቸው
ሦስት አምላክ የለም፡፡ እንፍጠር፤ እንውረድ፤ ... ወዘተ ስላለ ከአንድ አምላክ በላይ ነው
ብለው ወስኗል። ቃሉ ግን በማያሻማ ሁኔታ ከአንድ አምላክ ሌላ እንደሌላ ያስተምረናል።
ዘዳ.4:35 እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ ከእርሱም
ሌላ አምላክ የለም። ዘዳ.4:39 እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር
አምላክ እንደ ሆነ ሌላም አንደሌለ ዛሬ እወቅ፥ በልብህም ያዝ። ኢሳ.43:10-12 ታውቁና
ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ
ናችሁ ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኀላ አይሆንም። እኔ
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ
አሳይቼማለሁ፤ በእናንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥
ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ። ኢሳ.44:6-7 የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር
የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኀለኛ ነኝ
ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም ከጥንት
የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ። አትፍሩ
አትደንግጡም ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኀችሁምን? ወይስ አላሳየኀችሁምን? እናንተ
ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም። ... እንደ
እግዚአብሔር ቃል ከአንድ አምላክ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌላ እንደማይኖርም በዘመናችን
ሁሉ እንመሰክረለን፡፡ .... ይቀጥላል
@onegodonlyjesuss
714 views🇦 🇧 🇪 🇱 🇦, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 11:53:46 የስላሴ አጠያያቂ ሚስጥር መጽሀፍ ለማግኘት
1.0K views𝓔𝓹𝓱𝓻𝓮𝓶 , 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 23:26:33
1.1K views𝓔𝓹𝓱𝓻𝓮𝓶 , 20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 20:08:03 የተወደዳችሁ የ Telegram ወዳጆቼ፤ በክርስቶስ ፍቅር ያለሽንገላ እወዳችኋለሁ ።


እናም አዲሱ አመት በነገር ሁሉ በመቀደስ ለክርስቶስ ዳግም መምጣት የምንዘጋጀበት አመት ይሁንልን።

ለሚወዱት ምርጦቻችሁ ያጋሩ
Share&join
https://t.me/apostolicdoc12
1.0K views𝓔𝓹𝓱𝓻𝓮𝓶 , 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 23:59:56 እንኳን ለ 2015 አዲስ አመት ኢየሱስ በሰላም በጤና አደረሳቹ።
              አመቱን
የፍቅር
የሰላም
የደስታ
የምስጋና
የምህረት
የሐሴት
የትጋት
የፅናት
የመነቃቃት
የተስፋ
የፀጋ
የአንድነት
ጊዜ ያድርግልን።
1.2K views🇦 🇧 🇪 🇱 🇦, 20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 10:34:41 የቤተክርስቲያን አባላት መመሪያ
906 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 14:25:24

913 views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 20:35:33 Apostolic Church of Ethiopia (የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን) pinned «አንድ የ78 ዓመት አባት እራሳቸውን ስተው ወደሆስፒታል ይወሰዳሉ ። ለ24 ሰዓት የሚያቆያቸው የመተንፈሻ ኦክስጅን ተሰጣቸው ። ከጥቂት ግዜ በኃላ ተሻላቸውና ዶክተሩ የተጠቀሙበትን ሂሳብ የ500 ዶላር ደረሰኝ ሰጣቸው ። እኝህ አባትም የተሰጣቸውን ደረሰኝ በተመለከቱ ግዜ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። ዶክተሩም ስለ ገንዘቡ ማልቀስ አይገባዎትም በአንድ ግዜም ባይሆን ቀስ እያሉ መክፈል እንደሚችሉ ነገራቸው ። ሆኖም…»
17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 19:19:56 #ለምስጋና_ተመለሱ
“ኢየሱስም መልሶ፦ አሥሩ አልነጹምን ? ዘጠኙስ ወዴት አሉ ? ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም አለ ። ” ሉቃ. 17፡17-18 ።የለምጽ በሽታ እንደ ዛሬው ያለ የቆዳ በሽታ አልነበረም ። የመጀመሪያ ተላላፊበሽታ ነው ። ሁለተኛ ከርኩሰት ጋር የተያያዘ ነው። ለምጽ ያለበት ሰው በካህኑ አዋጅ ራሱን ከሕዝቡ ለይቶ በምድረ በዳ ይኖራል ። ከተፈወሰ ሲመለስ ፣ ካልተፈወሰ በዚያው ይሞታል። የሚወዳቸው ቤተሰቦቹም ቤዛ ሊሆኑለት አይችሉም ። “ርኩስ ነኝ” ብሎ በራሱ ላይ ያውጃል ፣ ሰው ከቀረበውም እየሮጠ ይሸሻል ። ከባድ ጭንቅ ነው ። ጌታችን በሰማርያ ሲያልፍ አሥር ለምጻሞችን በምድረ በዳ አገኘ ። እነዚህ ለምጻሞች
ያገናኛቸው ኑሮ ሳይሆን ችግር ፣ ከተማ ሳይሆን ምድረ በዳ ነው ። ሐኪም ቤትና ስደት ያፋቅራል ።ችግሩ ያ ሲያልፍ መረሳሳት ይመጣ ይሆናል ። የችግር ቦታዎች ጥላቻና ራስ ወዳድነት የሚገረዝባቸው የግርዛት ኮረብታዎች ናቸው።ጌታችንን ባገኙት ጊዜ አልሮጡም ፣ እንደውም እየጮኹ ቀረቡት ። እርሱ የሚያነጻ ነውና ርኩሶችን አይሸሽም ። የሰው ቅድስና ግን ከራሱ አልተርፍ ስትል መሸሽ ይጀምራል ። “ኢየሱስ ሆይ አቤቱ ማረን አሉት ። ማረን ቢበድሉም ባይበድሉም ትልቅና የመጨረሻ ጸሎት ነው ። ቢታመሙም ባይታመሙም ሐኪም ጋ መሄድ መልካም ነው ። ስለ መፈወስ ቢለምኑ አንድ ልመና ነው ። እርሱ ከማራቸው ግን ሁሉም ጸጋ የእነርሱ ነው ። ማረኝ የጸሎት አባ ጠቅል ነው ። ምሕረት ያለውን ጌታ ማረኝ አሉት ። ማረኝ የሚባልም እርሱ ብቻ ነው ። ሰው ይቅር ይላል ፣መማር ግን የአንድ አምላክ ግብር ነው። ሰው ይተዉልናል ፣ እግዚአብሔር ግን እንዳልበደለ አድርጎ ይቀበለናል ። ጌታችን “ራሳችሁን ለካህን አሳዩ” አላቸው ። ለምጻም ናችሁ ብሎ ያረጋገጠውና በአዋጅ የለያቸው ካህኑ ነውና የሚመልሳቸውም ካህኑ ነው። ፈውሱን ጌታ አደረገና አዋጁን ግን ለባለሥልጣኑ ካህን ተወለት ። እግዚአብሔር ራሱ የሠራውን ሥርዓት ራሱ አያፈርስም ። “እነሆም ሲሄዱ ነጹ” ይላል ። በጣም ድንቅ ነገር ነው ። ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ ጌታችንን ሊያመሰግን ወደ ኋላ ተመለሰ ። ሌሎቹ ግን ቤተሰቦቻቸውንና የተለዩትን መንደር ለማግኘት ገሰገሱ ። አንገታቸው ወደፊት እንጂ ወደኋላ ዞር ብሎ የሚያይ አልነበረም ። ይህ አንዱ ሰው በጌታ እግር ላይ ወድቆ ማመስገን ጀመረ።ያ ሰው ግን የተናቀ ሳምራዊ ነበረ ። ከተናቀው ሰው የከበረ ምስጋናና ውለታ አክባሪነት ወጣ ። በማይጠበቅ ቦታ የማይጠበቅ ግብር ይገኛል። ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ብዙ አሉ ፣ ይህ ሰው ግን በቀትር የዘነበ ምስጋና አለው ። ድብልቅ ከሚባል ሕዝብ የጠራ ምስጋና ወጣ። ወገኑ ሳምራዊ ሳለ እንዴት አብሯቸው ከረመ ብንል የከፋ ችግር የሚያንሰውን ዘረኝነት አስረስቷቸው ነው ። በዘረኝነት የሰከሩ የባሰ ችግር ሲመጣ ይረሱታል ። “እዬዬ ሲዳላ ነው” ይባላል ። ሰው በጦርነት መሐል ልቅሶ አይቀመጥም ። ተደላድሎ ሲቀመጥ ግን ስለሞተው ወንድሙ ማልቀስ ይጀምራል ። ካልበሉ እንባም አይመጣም ። “ኢየሱስም መልሶ፦ አሥሩ አልነጹምን ? ዘጠኙስ ወዴት አሉ ? ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም አለ ።” ለምስጋና የሚመለስ ከአሥር አንድ መሆኑ ይገርማል ። ዘጠኙ ተፈውሰዋል
ውለታው የነካው ግን አንዱ ነው ። ዛሬም ከአሥሩ አንዱ ብቻ ለምስጋና ይመለሳል ። እነዚያ ዘጠኙ የገሰገሱት ግን ወደ ሚያልፉት ወዳጆቻቸው ነው። ደግሞም ርኩስ ብላ ወደ ገፋቻቸው ዓለም ነው ። ዛሬም ሰዎች ሲፈወሱ ወዳወገዘቻቸው ዓለም ይመለሳሉ ። ለምስጋና የሚመለሱ ጥቂቶች ናቸው ።የሚበዛው የምስጋና ዕዳ ያለበት ነው ። ወዳጆቼ ትልቁ በደል የእግዚአብሔርን ውለታ መርሳት ነው ። መቃብራችሁ የተደፈነላችሁ ፣ ከጫካ ሕይወት ወጥታችሁ ከሰው ቊጥር የተደመራችሁ ፣ የክረምትን ያህል በእንባ የታጠባችሁ ፣ ከሩቅ አገር ወደ ክርስቶስ የመጣችሁ ፣ … ለምስጋና ተመለሱ። ፈውስም ማግኘትም ዘላለማዊ አይደሉም ። ዘላለማዊ እግዚአብሔር ብቻ ነው ።
@onegodonlyjesuss
Join & Share
787 views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ