Get Mystery Box with random crypto!

ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ bethel_tube — ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ bethel_tube — ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ
የሰርጥ አድራሻ: @bethel_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.54K
የሰርጥ መግለጫ

የቤተክርስቲያንችንን ትውፊት እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ጹሑፎች ግጥሞች ትረካዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መልዕክት ያላቸው መንፈሳዊ ወጎች ይተላለፉበታል። በተጨማሪም ኪነጥበባዊ ለዛን የተላበሱ አዝናኝና አስተማሪ ፅሑፎችም የሚቀርቡበት ቻናል ነው።
ሀሳብ አስተያየታችሁን @downpost ላይ ፃፉልን።
………… ©ቤትኤል ቤተ-እግዚአብሔር …………

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 16:00:11 ይድረስ ለሴቶች እህቶቼ

አዲስ ተች ስልክ [smart phone]  የገዛችውን ልጅ አባቷ ሲያያት . . .

አባት ፡- “ስልኩን ስትገዢ በመጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው?” ብሎ ጠየቃት፡፡
ልጅ ፡- “በመጀመሪያ ያደረኩት . . . ስክሪኑ እንዳይጫጫር መከላከያ ስቲከር ለጠፍኩበት”
አባት ፡- "እንደዚ እንድታደርጊው የገፋፋሽ እለ?"
ልጅ ፡- "የለም!"
አባት ፡- "ያመረቱትን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን "
ልጅ ፡- "ኧረ አባዬ ! እንደውም የሚመክሩን እንድንለጥፍበት ነው!"

አባት ፡- "የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው?"
ልጅ ፡- "በነገራችን ላይ የሸፈንኩት እንዳይበላሽብኝ እና ብዙ ግዜ እንዲያገለግለኝ ስለምፈልግ ነው!"
አባት ፡- "ስትሸፍኝው ውበቱን አልቀነሰውም?"
ልጅ ፡- "እንደውም በጣም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ ይከላከልልኛል"
አባት ፡- በአባትነት ዓይን እያያት "አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽስ?" አላት
ልጅ:- "እሺ አባዬ ጠይቀኝ" አለች።

አባትም እንዲህ አለ: -  "ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው? እሺ ትይኛለሽ"?

ሁሌም አባታችን እግዚአብሔር በሰው ላይ አድሮ ይጠይቀናል ብቻ በብዙ ነገር ራሳችንን እንድንሸፍን ይጠይቀናል !

☞የምናስተውል ካለን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል"፤

ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸፍኑ  (1 ኛ ጢሞ 2፥9)

በሚሞት ስጋችሁ ሐጢያት አይንገስ ብልቶቻችሁን የፅድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ (ሮሜ 6፥12-14)

ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው። ካልተቻለ ዝሙትን ለመከላከል በአንድ ይፅና ከዚህ ውጭ ጉዞ ወደ እሳት ነው (1ኛ ቆሮ 7፥1)

ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱ ያፈርሰዋል ቤተ መቅደሱም እናንተው ናችሁ (1ኛ ቆሮ 3፥17)

የወንድ ልብስ የለበሰች ሴት በአምላክ ዘንድ የተጠላች ናት (ዘዳ 22፥5; ዘፀ 39፥28)

ፀጉሯን ሳትሸፍን የምትፀልይ ሴት እራሷን ያዋረደች ናት(1ኛ ቆሮ 11፥5)

☞ እንድናስተውል እና እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን። 
አሜን።
205 viewsEvєrℓαst, 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:36:24 ፉክክር


በአንድ ሀገር የሚኖሩ ባል እና ሚስቶች ነበሩ። ከዕለታት በአንድ ቀን ባል ከስራ አምሽቶ ወደ አቤቱ ይገባና ከባለቤቱ ጋር የቤታቸው በር ክፍት እንደሆነ ይጨዋወታሉ። ጥቂት ከተጫወቱ ባል በስራ እጅጉን ስለደከመ ባለቤቱን እንዲህ ይላታል

ውዴ በሩን ዝጊው እና እንተኛ። ባለቤትየውም እራስክ ዝጋው ትለዋለች። ባልየውም መልሶ ምነካሽ ውዴ እንዴት ከስራ ደክሜ እንደመጣሁ እያወቅሽ እባክሽን አንቺ እራስሽ ዝጊው ይላታል።

እሷም መልሳ እኔም እቤት ውስጥ ስሰራ ውይ እጅጉን ደክሜአለሁ ትለዋለች። ባል እና ሚስቶቹም እንዲሁ እየተሟገቱ እና እየተጨቃጨቁ በሩን ሳይዘጉት እንቅልፍ ይወስዳቸዋል። እኩለ ለሊት ላይ አንደ ሌባ ወደ ቤታቸው ይገባና የተኙትን ባል እና ሚስቶች በጅራፍ ጀርባቸውን እየለጠለጠ ይገርፋቸዋል እነሱም ደንግጠው ይነሳሉ። በሁኔታውም ተደናግጠው   ሌባው የሚፈልገውን ነገር በሙሉ እንዲወስድና እንዲለቃቸው ይለምኑታል። ሰውየውም አሁኑኑ ቤታቹን ለቃቹ እኔ ወደማሳያቹ ቦታ ትሄዳላቹ ይላቸዋል። እነሱም በድንጋጤ ተስማምተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ።

ወደተባለው ቦታ ሲደርሱም ሰውየው እንዲህ ይላቸዋል እናንተ እንዳሰባቹት እኔ ሌባ አይደለሁም ነገር ግን የሚስቴ መውለጃ ወራት ደርሶ ለሷ የሚሆን ምግብ የሚያዘጋጅላት ሰው አጥቼ ነበር እናም አሁን እናንተንም ስላገኘው አሁን ለምግብነት የሚሆነውን እህል ትወቅጣላቹ አላቸው። እነሱም አንተ ነክ ዝጋ እያልኩክ በሩን አንቺ ነሽ ዝጊው በሩን እያልኩሽ ለዚህ ያበቃሽኝ እየተባባሉ እህሉን መውቀጥ ጀመሩ ይባላል።

ከዚህ ታሪክ የምንማረው በጥንዶች መሃል በባለትዳሮች መሃል ክፍተት መፍጠር ልክ ወለል ብሎ ተከፍቶ እንዳደረው ቤት ለጠላት መግቢያ መንገድ መክፈት ነው። ሌባ ወይም ጠላት የተባለው ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ደግሞ በከፈትንለት በር ገብቶ በጅራፉ እየገረፈ እያሰቃየን ባሪያዎቹ ስለሚያደርገን ልንጠነቀቅ ይገባል። ስለሆነም በባለትዳሮች ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ መኃል፣በባለንጀራሞች መካከል ለጠላት ዲያብሎስ መግቢያ በር ወይም መንገድ አንክፈት ከፍተንም አንደር።
160 viewsEvєrℓαst, 08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:32:13
202 viewsEvєrℓαst, 09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:22:00 "ደቂቃዎች ጠብቀኝ"

ብልጥ እኔ ብቻ ነኝ ብሎ የሚኩራራና ሌላውን የሚንቅ አንድ ሰው ነበር፡፡ የተማረ ይኹን ያልተማረ፣ ትልቅ ይሁን ትንሽ ማንም ከፊቱ ቢቆም ደንታ የለውም፡፡ ሁሌም ቢሆን አዋቂ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ታድያ አንድ ቀን እግዚአብሔር ተገለጠለትና አናገረው፡፡ ሰውየው እግዚአብሔርን “የምጠይቅህ ነገር አለኝ” ስላለው እግዚአብሔርም ፈቀደለትና መጠየቅ ጀመረ፡፡

የመጀመሪያው ጥያቄ “ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ዘንድ አንድ ሚሊዮን ዓመታት ስንት ናቸው?” የሚል ነበር፡፡ እግዚአብሔርም “ደቂቃ እንደ ማለት ነው” ሲል ይመልስለታል፡፡ ሰውየውም ቀጠለና “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችስ በአንተ ዘንድ ስንት ናቸው” ሲል ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች በእኔ ዘንድ እንደ ጥቂት ሳንቲሞች ናቸው” ሲል ይመልስለታል፡፡ በዚህን ጊዜ ከማን ጋር እያወራ እንኳን በቅጡ ያልተረዳው በልጡ ሰው ፈጠን ብሎ “እግዚአብሔር ሆይ እንግዲያውስ ጥቂት ሳንቲሞችን ብቻ እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ” አለው፡፡ እግዚአብሔርም “ጥሩ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ጠበቀኝ” አለውና ሰውየው በብልጠቱ እንደተኮፈሰ ሳለ ትቶት ሄደ፡፡

ምሳሌ ከሚመሰልለት ነገር ማነሱ እንደተጠበቀ ሆኖ የዚህ ምሳሌያዊ ንግግር ዋና መልእክት ልብ ላለው ሰው ያለምንም ምብራሪያ ሰተት ብሎ ወደ አእምሮ የሚዘልቅ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከማን ጋር እንደሆኑ እንኳን ነገሬ ሳይሉ ብልጠታቸውና ዕውቀታቸውን በመጠቀም እራሳቸውን ለመጥቀም ይሞክራሉ፡፡

እውቀትና ጥበብ በደፈናው አይነቀፍም ችግሩ ግን ያንን እውቀትና ጥበብ የት፣ መቼ፣ ለማን ለምንና እንዴት እንደምንጠቀመው አለማወቃችን ነው፡፡ ትንሽ እውቀት አደገኛ ነው እንደሚባለው ይህ ሰው ባለችው ትንሽና አደገኛ እውቀቱ ተኮፍሶ ነበር፡፡ በመሆኑም ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ መሆኑን እንኳ ረስቶት በማታለል ራሱን ከበርቴ ሊያደርግ ሞክሯል፡፡

ለዚህም ነው ጥቂት ሳንቲም አስመስሎ ሚሊዮን ዶላር ከእግዚአብሔር ለመቀበል ያሰበው፡፡ ሲያምረው ቀረ እንጂ፡፡ ይህ ሰው ምን አልባትም ያነበባት ይህቺን ጥቅስ ብቻ ሊሆን ይችላል “እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት ፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ” 2ኛ ጴጥ 3፤8” በዚህች የንባብ ዕውቀቱ ነው እንዲህ ከእግዚብሔር በልጦ ለመገኘት የሞከረው፡፡

ብልጠት ለይሁዳም አልበጀው፡፡ ዐይናችን እያየ ልባችን ከመታወሩ በፊት ሁላችንም ልብ እንበል፡፡
295 viewsEvєrℓαst, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:44:45





441 viewsEvєrℓαst, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 14:36:43 በአንድ ሌሊት ፫ ጊዜ አምላኩን ለካደው ጴጥሮስ፣ ከቁጥር በደሉ ሺ ጊዜ የሚልቅ የተዘጋጀለት ይቅርታ ነበር።
696 viewsEvєrℓαst, 11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 21:09:39 ከፀሃይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች ሰልፍም ለኅያላን : እንጀራም ለጠቢባን: ባለጠግነትም ለአስተዋዮች : ሞገስም ለእዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ !ግዜ እና ዕድልግን ሁሉን ያገናኛችዋል!
መክ : 9 : 11

ተግሳፅን ስትሰሙ ቅናት የማይመስላችሁ! ደጋግ የተዋህዶ ልጆች ሆይ በሰላም እደሩ!
879 viewsEvєrℓαst, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 17:14:24
“… ያችኛይቱ ሔዋን ከአዳም ተገኝታ የተሠራችና አዳም ወደ እርስዋ እያየ ‘ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት’ የሚላት ናት፡፡

ይህችኛይቱ ሔዋን ድንግል ማርያም ግን ከአዳም ጎን የተገኘች ሳትሆን አዳምዋ ክርስቶስ ሥጋው በጅራፍ ግርፋት ሲቆስልና አጥንቶቹ ሲቆጠሩ በጭንቀት እያየች ‘ይህ አጥንት ከአጥንቴ ነው ፤ ይህ ሥጋም ከሥጋዬ ነው’ የምትል ሔዋን ናት፡፡

የቀደመችዋ ሔዋን አዳምዋ በእርስዋ ምክንያት ጠፍቶ ‘አዳም ሆይ ወዴት ነህ?’ ተብሎ ሲፈለግ በዛፎች መካከል ሆኖ ከአባቱ ከእግዚአብሔር ‘ፈርቼ ተሸሸግሁ’ የሚል አዳም ነበረ::

ሁለተኛይቱ ሔዋን ድንግል ግን አዳምዋን ፍለጋ የምትጨነቅና ወዴት ነህ? ስትለው አዳምዋ ‘በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንዲገባኝ አታውቁምን’ ብሎ የሚመልስላት ከአባቱ እቅፍ ያልተለየ አዳም እናት ናት፡፡

ለድንግል ማርያም ክርስቶስ ከእርስዋ የተገኘ አዳምዋ ብቻ ሳይሆን በቀናተኞቹ ቃየኖች አይሁድ በግፍ የተገደለባት አቤልዋም ጭምር ነው፡፡ ልዩነቱ የአቤል ደም ወንድሙን የሚከስስ ደም ሲሆን የእርስዋ ልጅ የክርስቶስ ደም ግን ‘ከአቤል ደም ይልቅ የሚሻለውን የሚናገር’ ‘ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ ደም’ ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የብርሃን እናት ገጽ 100
859 viewsEvєrℓαst, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 18:12:07 የሠው ልጅ ተስፋ ከሚያደርገው መንግስተ ሠማያት በተቃራኒ ሀጢያት ለሰራ ወይም እንደ ቤተክርስትያን አባቶች አስተምሮ በደል የፈፀሙ ሰዎች ስጋቸውና ነፍሳቸው ስለሚቃጠልበት ቦታ ሲኦል እንደ ቤተ ክርስትያን አባቶች አስተምሮ ፍፁሞ አስፈሪ ተደርጋ ትሳላለች ከቀደምት ታሪኮች አንፃር... አጥኑ ነዌ ስለበደሉ ብዛት በሲኦል እያለ በሲኦል ስላለው መከራ ስለ 6 ወንድሞቹ ፀለየ ይሕም ማለት በሲኦል ቢያንስ እንኮን መፀለያ ጊዜና ቦታ አለ ማለት ነው።

ሌላው በማርቆስ ወንጌል 16:16 ''ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል'' ይላል ይሕም ማለት እኛ በሥላሤ ያመንን በሲኦል ካለው እሳት ልንድን እንችላለን ማለት ነው። ለምሳሌ ያክል በላየሰብ ለብዙ ዘመናት የሰዎችን ስጋ ሲበላ የነበረ ሰው ነው።

ከለታት በአንድ ቀን ሕይወቱ ያልፍና በሕይወት ሳለ በእመቤታችን ስም ቀዝቃዛ ውሀ ስላጠጣ በእመቤታችን አማላጅነት ከሲኦል ተረፈ እንግዲሕ በክርስቶስ ያላመነው በላየሰብ ከሲኦል እሳት ከዳነ እኛ በሥላሤ ያመንን ባርባ ቀንና በሰማኒያ ቀናችን የተጠመቅን በፃድቅ ሰው ስም ቀዝቃዛ ውሀ እንኮን የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይከፋም የሚለውን ቃል መሠረት አድርገን በፃድቅ ስም ዝክር የዘከርን ከሲኦል እሳት እንድናለን ማለትነው።

ነገር ግን ሰው ሆይ ''አንተ ግን በተማርክበትና በተረዳህበት ነገር ፀንተህ ኑር"።

2ኛ ጢሞ 3:14
879 viewsEvєrℓαst, edited  15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 05:31:38 ከእለታት አንድ ቀን ልጅና አባት በፍቅር፣በደስታ በተሞላበት ቤት አብርው ይኖራሉ። ውዴታቸው መችም ከሌሎች የተለየ ነበር ምክንያቱም አንዱ ካንዳቸው ተነጥለው መኖር የሚችሉ አይመስል። ከለታት አንድ ቀን ልጅ ትታመማለች አባት ልጁን ይዞ ሀኪም ቤት ሄደ።

ሀኪም መፍትሄ አልሰጣትም ልጅት አሁንም አልተሻላትም ልጁን ይዞ ወደ ፀበል ወሰዳት መፍትሄ የለም የሳይኮሎጂ ባለሙያ አማከረ፣ ያልሄደበት የለም በቃ ልጅት ግን ልትተርፍ አልቻለችም ልጁ ሞተች። አባት አንጀቱ ተቆረጠ፣ የሚይዘው፣ የሚጨብጠው አጣ ተስፋ ቆርጦ ቤት ዘግቶ እራሱን በሀዘን መቅጣት ጀመር።

ሌት ተቀን ማልቀስ ማልቀስ በእንባ ሲታጠብ ይውላል፣ያድራል። የሰፈሩ ሰወች ሊያፅናኑ፣ ሊያበርታቱ ቢሞክሩም እሽ አላለም ባሰበት ሀዘኑ። አንድ ቀን በህልሙ ሰማይ ላይ ያሉ ህፃናት ልጆች ውድድር ይቀርባሉ ለሁሉም ሻማ፣ ጧፍ ተሰጡ እና አሁን ሁላችሁም አብሩት ተባሉ ሁሉም አበሩት።

ነገር ግን የሱ ልጅ ሻማው አልበራላት አለ ብትለው፣ ብትለው ልጄ የሁለም እየበራ ያንች ይጠፋል ለምንድን ነው ብሎ አባት ጠየቃት?

ልጅም አባዬ የኔ የማይበራው እኮ አንተ ሁልጊዜ ስለምታለቅስ እንባህ ነው የሚያጠፋብኝ አለችው። አባት ከዛ ቀን ጀምሮ ከሀዘን ወጣ፣ ከማህበረሰቡ ጋር በደስታ፣ በፍቅር፣ ስለዚህ ብዙ ማዘን እኛን ብቻ ሳይሆን፣ የሞተውንም ሰው ነፍሱን እንረብሸዋለን ማለት ነው። በሀዘን ላይ ብዙ መቆየት ተገቢ አይደለም። ጸሎት በማረግ ለተለየን ሰው ምህረት መጠየቅ ነው ትልቁ ነገር።

እግዚአብሔር የፈቀደው ነው ሚሆነው።
782 viewsEverlast, 02:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ