Get Mystery Box with random crypto!

ፉክክር በአንድ ሀገር የሚኖሩ ባል እና ሚስቶች ነበሩ። ከዕለታት በአንድ ቀን ባል ከስራ | ቤትኤል ዘ-ተዋሕዶ

ፉክክር


በአንድ ሀገር የሚኖሩ ባል እና ሚስቶች ነበሩ። ከዕለታት በአንድ ቀን ባል ከስራ አምሽቶ ወደ አቤቱ ይገባና ከባለቤቱ ጋር የቤታቸው በር ክፍት እንደሆነ ይጨዋወታሉ። ጥቂት ከተጫወቱ ባል በስራ እጅጉን ስለደከመ ባለቤቱን እንዲህ ይላታል

ውዴ በሩን ዝጊው እና እንተኛ። ባለቤትየውም እራስክ ዝጋው ትለዋለች። ባልየውም መልሶ ምነካሽ ውዴ እንዴት ከስራ ደክሜ እንደመጣሁ እያወቅሽ እባክሽን አንቺ እራስሽ ዝጊው ይላታል።

እሷም መልሳ እኔም እቤት ውስጥ ስሰራ ውይ እጅጉን ደክሜአለሁ ትለዋለች። ባል እና ሚስቶቹም እንዲሁ እየተሟገቱ እና እየተጨቃጨቁ በሩን ሳይዘጉት እንቅልፍ ይወስዳቸዋል። እኩለ ለሊት ላይ አንደ ሌባ ወደ ቤታቸው ይገባና የተኙትን ባል እና ሚስቶች በጅራፍ ጀርባቸውን እየለጠለጠ ይገርፋቸዋል እነሱም ደንግጠው ይነሳሉ። በሁኔታውም ተደናግጠው   ሌባው የሚፈልገውን ነገር በሙሉ እንዲወስድና እንዲለቃቸው ይለምኑታል። ሰውየውም አሁኑኑ ቤታቹን ለቃቹ እኔ ወደማሳያቹ ቦታ ትሄዳላቹ ይላቸዋል። እነሱም በድንጋጤ ተስማምተው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ።

ወደተባለው ቦታ ሲደርሱም ሰውየው እንዲህ ይላቸዋል እናንተ እንዳሰባቹት እኔ ሌባ አይደለሁም ነገር ግን የሚስቴ መውለጃ ወራት ደርሶ ለሷ የሚሆን ምግብ የሚያዘጋጅላት ሰው አጥቼ ነበር እናም አሁን እናንተንም ስላገኘው አሁን ለምግብነት የሚሆነውን እህል ትወቅጣላቹ አላቸው። እነሱም አንተ ነክ ዝጋ እያልኩክ በሩን አንቺ ነሽ ዝጊው በሩን እያልኩሽ ለዚህ ያበቃሽኝ እየተባባሉ እህሉን መውቀጥ ጀመሩ ይባላል።

ከዚህ ታሪክ የምንማረው በጥንዶች መሃል በባለትዳሮች መሃል ክፍተት መፍጠር ልክ ወለል ብሎ ተከፍቶ እንዳደረው ቤት ለጠላት መግቢያ መንገድ መክፈት ነው። ሌባ ወይም ጠላት የተባለው ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ደግሞ በከፈትንለት በር ገብቶ በጅራፉ እየገረፈ እያሰቃየን ባሪያዎቹ ስለሚያደርገን ልንጠነቀቅ ይገባል። ስለሆነም በባለትዳሮች ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ መኃል፣በባለንጀራሞች መካከል ለጠላት ዲያብሎስ መግቢያ በር ወይም መንገድ አንክፈት ከፍተንም አንደር።