Get Mystery Box with random crypto!

“እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?” ( | Apostolic Church of Ethiopia (የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን)

“እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?” (ኢዮብ 9፥12)።
ቢሾፕ ተክለማሪያም ገዛኸኝ የተወለዱት በአድዋ አውራጃ በአምባይሰይነይቲ ወረዳ ልዩ ቦታ ጮማእምኒ በሚባል ስፍራ ሚያዝያ 11 በ1929 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ብዙ የሕይወት ውጣውረድ ያጋጠማቸው ሲሆን በዘመድ ቤት ሆነው በአድዋ ከተማ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወር 15 ብር ከመንግሥት እየተከፈላቸው ተከታትለው በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቅቀዋል።
ቀሪውን ሕይወታቸውን በሙሉ እግዚአብሔርን በመፈለግ የእግዚአብሔር ጥሪ ገና በ14 ዓመት ዕድሜአቸው የመጣላቸው በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት አንገታቸውን ወደ መንፈሳዊ ነገር አዙረው አንድ ወጣት ጓደኛቸው እሳቸውንና መጽሐፍ ቅዱስን አስተዋወቃቸው። ስለ መንፈስ ቅዱስም ሙላት ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 እየጠቀሰ ሲያስረዳቸው ወ/ም ተክሌም ጥማት አደረባቸው፤ ፍለጋውን ይቀጥሉና ከብዙ ምኞትና ፍለጋ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።
በመቀሌ፣ በወሎ፣ በወልዲያ እና በሰሜኑ ክፍል አንድ ብሎ የጀመሩት የወንጌል እንቅስቃሴ ወደ ኤርትራ ተሻግሮ የእስራት ገፈትም ገና ቅምሻ የጀመረባቸው ከመጀመሪዎች አከባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው።
ጥቅምት 5 ቀን በ1957 ዓ.ም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። በኅዳር 5 ቀን የመጀመሪያውን የኢየሱስን ድንቅ ተአምራት በሕይወታቸው አዩ።
በሉተራን መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ለአራት ዓመታት ቲዮሎጂን ተከታትለዋል። ቀጥሎም በናዝሬት (አዳማ) በሚገኘው በሜኖናይት መጽሐፍ ቅዱስ አካዳሚ ተከታታይ ሁለት ዓመታት የክረምት ትምህርት ተምረዋል።
ግማሽ ምዕተ-ዓመት የሚጠጋ ዓመታትን ቤተክርስቲያንን ከኢየሱስ እጅ በታች የበላይ ጠባቂ በመሆን መርተዋል። ከደርዘን (ከ12) በላይ የስነመለኮት መጽሐፍትን ለትውልድና ለቤተክርስቲያን አበርክተዋል። በርካቶች በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በኦሮሚኛና በትግሪኛ ትርጉም የእሳቸው ሥራዎች ለአንባቢያን በቅተዋል።
ከእነዚህም፦
መለኮታዊ ኃይል በ1961
እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?
ጥያቄዎቻችሁና መልሶቻቸው
ትምህርተ-መለኮት
አዲስ ልደት
መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለጀማሪዎች
መጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊያን
ስነመለኮት (Bible writers theology)
ኢየሱስን ማን ይሉታል?
ቃሉ ይናገር
የመልዕክቶች አጠቃላይ ትምህርት
በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ
አንድ መንጋ
በስርዓት ታነጹ...ይጠቀሳሉ።
የአንድ አምላክ ትምህርትና የስሙ ጥምቀት በአጥንታችን ሰርጎ እስኪገባ፣ በደማችን እስክዋሄድ ዕድሜ ልካችን ሲናገሩ ኖረዋል። የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ናቸው፣ ዘማሪ ናቸው፣ የስነመለኮት አስተማሪና ተመራማሪ ናቸው፣ የተዋጣላቸው ሰባኪ፣ ጸሐፊም ነበሩ።

ቤተክርስቲያንን በዓለም አቀፉ ይዘት የመሩ መሪም ነበሩ፡፡ የእኚህ ሰው ሁለገብ አገልግሎታቸው እንዲሁ በሰው ጥበብ የተገኘ ተስጥኦ ነው ለማለት እንቸገራለን፤ ከሰማይ አምላክ የተሰጠ ጸጋ ነው እንጂ።

የጥንቱ መሰረት ዳግም በአንድ ሰው ልብ ተጸንሶ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በግለሰብ ቤት የተጀመረውን የሐዋርያትን ትምህርት ሰንሰለት ከ82 በላይ በዓለም አገራት እንዲስፋፋ የራሳቸውን ጥረት አድርገው ለእግዚአብሔር ፍቃድ ተገዢ ሆነዋል።
እኚህ ታላቅ ሰው በአሜርካን ሀገር በሚገኘው Christian life college የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ተሸልመዋል። በ1993 ዓ.ም በካናዳ ሀገር ከሚገኘው ከጄነስስ ኢንስቲትዩት የስነመለኮት ትምህርት ተከታትለው ሦስተኛ ድግሪያቸውን "The mystery of God revealed እና mentally arrested by the myth of psychotherapy" በተባሉ ርዕሶች የምርምር ጽሑፋቸውን በማቅረብ በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አድናቆትን አግኝተዋል።
በኢትዮጵያ ምድር የሐዋርያት ወንጌል እንዲስፋፋ ያደረጉት ትግል እንዲህ በጥቂት ገጾች ተጽፎ የሚበቃ አይደለምና ክብር ይገባቸዋል። ታሪካቸው ከቤተክርስቲያን ታሪክ ጋር በእሳቸው የተሰራው የኢየሱስ ሥራ ሲወሳ ይኖራል።
የእግዚአብሔር ቃል “የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ” (ዘካ 4፥10) እንደሚል ከእሳቸው ጋር መንፈሳቸውን ደግፈው ከተነሱ በጣት በሚቆጠሩ አባቶች የተጀመረው ይሄው እንቅስቃሴ ዛሬ ከ7 ሚሊዮን በላይ የአንድ አምላክ ልጆችን ከአለም ዙሪያ አስተሳስሯል ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል፡፡
ዶክተር ቢሾፕ ተክለማሪያም አንድ ወቅት ጣሊያን አገር ለህክምና በሄዱበት ሀከሙ