Get Mystery Box with random crypto!

Success ስኬት @one_success

የቴሌግራም ቻናል አርማ one_success — Success ስኬት @one_success S
የቴሌግራም ቻናል አርማ one_success — Success ስኬት @one_success
የሰርጥ አድራሻ: @one_success
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 583
የሰርጥ መግለጫ

❖"Work Smart, Not Hard"
° ° [ በ Success ስኬት @one_success የቴሌግራም ቻናል ላይ ] ° °
➖የ ስኬት ጥቅሶች
➖የ ስኬት ቁልፎች
➖ታሪኮች
➖አባባሎች
➖አስተማሪ ንግግሮች ያገኛሉ።


° °

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 07:05:16
#የስኬታማ_ሰዎች_ባህሪያት

#ምኞት
ስኬታማ ሰው ግልጽ የሆኑ ግቦች አሉት። “ሀብታም መሆን” እንደሚለው አይነት ግልጽ ያልሆነ ግብ ይልቅ ፣ “በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ያለኝን አንድ ሱቅ ወደ ሶስት ሱቆች ማስፋፋት የሚል አይነት ውስን ግብ ያስቀምጣል።

#ተነሳሽነት
ስኬታማ ሰዎች በጣም ከሚገለጹበት ባህሪያት አንዱ ተነሳሽነት ነው። ስኬታማ ሰዎች ግባቸውን ለማሳካት ጠንካራ ተነሳሽነት ሊኖራቸው ይገባል። ጠንካራ የተነሳሽነት ስሜት ያለው ስኬታማ ሰው፥ በችሎታው ስለሚተማመንና ግቡን ለማሳካት ስለሚፈልግ ያለ ድካም መስራት ይችላል፨

#ለመማር_ፈቃደኛነት።
ስኬታማ ሰው ሁሉን አውቃለሁ አይልም፨ ከሁሉም ሰውና ከሚያጋጥሙት ሁኔታዎች ሁሉ ለመማር የተከፈተ አእምሮ አለው፨ እያንዳንዱ ተሞክሮ ለማደግ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ይረዳል፨ የማያውቀው ነገር እንዳለ ያምናል፥ አዲስ ነገር ለመማር ቦታ እንዳለው ሲገነዘብም እውቀቱን ለማሻሻል ይነሳሳል፨

#ታጋሽነት
ስኬታማ መሆን የምትፈልግ ከሆነ ትዕግስት ሊኖርህ ይገባል፨ ነገሮች ምንም ያህል አሁን እንዲሆኑ ብትፈልግ ሊደረስበት ዋጋ ያለውን ማንኛውም ነገር መጠበቅ ደግሞ ዋጋ አለው፨

#ስርዓት
ስኬት ወጥነት ይፈልጋል፥ ወጥነት እንዲኖር ደግሞ ስርዓት ሊኖር ይገባል፨ ብዙ ስኬታማ ሰዎች ህልማቸውን እውን ለማድረግና በጥረታቸው ውስጥ ወጥነት ያላቸው እንዲሆኑ የዕለት ተዕለት ተግባር ላይ መመስረት አንዱ ቁልፍ እንደሆነ ተገንዝበዋል።

ወጥነት ያለውና ሥርዓታማ በመሆንና ለማደግ ራስህን በመስጠት፣ በስራና በህይወት ውስጥ ብዙ ሽልማቶች እንድታገኝ ያደርግሃል፨ ይህ ሰዎች በሙያቸው ስኬትን ብቻ ሳይሆን ረጅም ዘመን ኖሯቸው እንዲደሰቱ የሚያስችል ቁልፍ ባህሪ ነው።

#ወደ_ሀብት_ጉዞ መጽሐፍ
82 views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 07:31:21 " ጥሩ ስብዕናን ለማጎልበት የሚያስፈልጉ ነጥቦች "

1: ድፍረት / Courage
2: መልካም አመለካከት / Positivity
3: ታማኝነት / Integrity
4: ደግነት/ ቅንነት / Kindness
5: ፅናት / perseverance
6 : አክብሮት / Respect
7 : ሀላፊነት / Responsibility
167 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 19:16:26
.ማገዝ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ተወዳጅ፦

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በራሳቸው ጥረት ብቻ የሚፈልጉት የስኬት ጫፍ ላይ ለመድረስ ሲታገሉ እንመለከታለን። በተለይ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሌሎችን እገዛ መጠየቅ የውድቀት መጀመሪያ መስሎ ይታያቸዋል። በዙሪያ የሚያግዙ ሰዎች መኖር ጥንካሬና ብርታትን ይሰጣል። ስለዚህ የሚያግዝህና ሃሳብህን የምታጋራው አስተዋይ ወዳጅ ይኑሩህ።
421 views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 03:36:18 Congratulations #Fias updating the platform

#FIAS
FIAS is an abrivation, It stands for Foreign Investment advisory service.
* በኮሚሽን የሚሰራ የማስታወቂያ ድርጅት ነው።
* ከተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ኔትዎርኮች ጋር ይሰራል።

እና በቀን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ለተመዘገቡ አባላቶቹ ይሰጣል። ስራዎቹ እጅግ በጣም ቀላል ናቸው። ክሊክ ማድረግ ብቻ ነው። በዛ ቢባል 5 ዲቂቃ ቢወስዱ ነው። አንድ አባል የሚሰጠው የስራ ብዛትና የሚያገኘው ብር እንደ ደረጃው ይለያያል። ደረጃዎቹ VIP-0, VIP-1, VIP-2, VIP-3, VIP-4, & VIP-5 ናቸው።


* You must start with 9 when entering a phone number.

* If you have more questions, you can ask.



1. VIP 0
* አንድ አባል ገና እንደተመዘገበ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 3 ስራዎችን ብቻ ነው።
* ለአንዱ ስራ 5 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 15.00, በወር 450.00, ይሰራል
* ብር ማውጣት የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ሆኖ ብሩም 100 ብር ነው።

2. VIP 1
* ይህ ደረጃ አባሉ 1,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 4 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 6 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 24 ብር, በወር 724.00 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

3. VIP 2
* ይህ ደረጃ አባሉ 3,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 6 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 84 ብር, በወር 2,520 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

4. VIP 3
* ይህ ደረጃ አባሉ 6,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 11 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 176 ብር, በወር 5,280 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

5. VIP 4
* ይህ ደረጃ አባሉ 10,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 17 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 18 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 306 ብር, በወር 9,180 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

6. VIP 5
* ይህ ደረጃ አባሉ 30,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 38 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 25 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 950 ብር, በወር 28,500 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

7. VIP 6
* ይህ ደረጃ አባሉ 60,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 50 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 39 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን1,950 ብር, በወር 58,500 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።


8. VIP 7
* ይህ ደረጃ አባሉ 100,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 70 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 48 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 3,360 ብር, በወር 100,800 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።


9. VIP 8
* ይህ ደረጃ አባሉ 180,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 95 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 67 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 6,365 ብር, በወር 190,950 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

* ልብ ይበሉ

አባሉ 1,000 ብር ከፍሎ VIP 1 ተመዝግቦ ከሆነና ደረጃውን ወደ VIP 2 ማሳዳግ ከፈለገ የሚከፍለው 2,000 ብር ነው። ምክንያቱም ለVIP 1 የከፈለው 1000 ብር ታሳቢ ይደረጋል።


ለመመዝገብ

https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=QGjZVq6z&t=1653645240613


contact through
@Online_world_com
445 views00:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 21:40:45 ጤና ይስጥልን
562 views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 09:07:34 የተሻለውን ማየት

በህይወት ውስጥ የልብን መሻት ለማግኘት መፍጨርጨር ግድ ነው። ያሰቡትን አግኝቶም ሆነ ሳያገኙ መቆም ግን ድክመት ነው፤ ተገቢ አይደለም። ከግቡ ባሻገር የተሻለውን የበለጠውን ማየትና እሱ ላይ ለመድረስ መገስገስ ያስፈልጋል።

"እኔ የምበላውን ካገኘሁ ይበቃኛል፤ ምን ያለፋኛል?" ማለት የሰነፍ ፣ የንፉግ እና የራስ ወዳድ ሃሳብ ነው። ካንተ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ እንዳትሠራ ምን ያግድሃል? ስንፍና ፣ ንፉግነት ወይም ራስ ወዳድነት ካልሆነ በቀር።

የዓለም ሊቃውንት እንዲያ ቢሆኑ ኖሮ ኑሮ ምን ያህል አስቸጋሪ ይሆን ነበር? ቶማስ ኤዲሰን እንዲያ 10ሺህ ጊዜ ባይሞክር ህይወታችን ምን ያህል ጨለማ በዋጠው ነበር።

የእጅ ስልክህ የስንት "ምን ቸገረኝ" ብለው ያልቆሙ እና የተሻለውን ማየት የቻሉ ሰዎች ውጤት ነው።

ወዳጄ ሆይ! ታካች አትሁን። በልፋት ውስጥ ደስታ አለ። እናቶች ሁሉ ልጅ የመውለድ ምጥ ምን ያህል ከባድ መሆኑን እያወቁ ልጅ ይወልዳሉ።

በልጁ መወለድ የሚገኘው ደስታ የተሻለ መሆኑን ያምናሉ፤ ያውቃሉም። "ምጥ በልጅ ይረሳል" አይደል የሚባለው።

ስላለህ ነገር ተመስገን ማለት ጥሩና ተገቢ ነው። በምስጋና ውስጥ ድል አለ። ከምስጋናው ባሻገር ግን የተሻለውን ማየትና በእጅ ለማስገባት ሳይስገበገቡ መስራት ያስፈልጋል። ሳይንገበገቡ የሚሠሩ በሚያጋጥማቸው እንቅፋት አያዝኑም፤ አይቆሙም። እንቅፋቱ በጉዞው ውስጥ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑን ይቀበላሉ፤ ተገቢውን ጥንቃቄ ያደርጋሉ። ሲያጋጥምም ለመፍትሔው ይሠራሉ።

ዛሬ የትናንት ሥራችን ውጤት ነው። ከትናንት የተሻለ ነገን ለመፍጠር ዛሬ ላይ ማሰብ ፣ መሥራት ፣ መጣር፣ አዲስ ነገር መሞከር ያስፈልጋል። "የተሻለውን ዓይተው የተጓዙ ጥቂቶች ቢሆኑም የሚሻለው አካሄድ እሱ ነው።

ለሀገራችን ፣ ለራሳችን ፣ ለሰው ልጅ የተሻለ ዓለም ለመፍጠር እንጣር፤ ዛሬ አዲስ ቀን ነው።

የተሻለ ልምድ የተሻለ ውጤት!

መልካም ቀን!
793 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 08:50:59
507 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 08:50:59 አንተ ደስተኛ እንድትሆን የግድ የምትፈልገው ሁሉ መሳካት የለበትም። ቀንህን ማሳመር ከፈለክ እጅህ ላይ ስላለው ነገር በጎ ነገር አስብ፤ አቅም አለህ፣ ወጣት ነህ፣ ብዙ ነገር መቀየር ትችላለህ ከሁሉ በላይ ደግሞ እየተነፈስክ ነው!

በዚህ አለም አንዳንድ ነገሮች የጎደሉህ ቀን ነው እንደነበሩህ ራሱ የምታውቀው፤ ለምሳሌ ስትታመም ነው ለካ ጤነኛ መሆን ወሳኝ ነገር እንደሆነ የሚገባህ። ወዳጄ የተሰጠህን ተመልከትና ቀንህን አሳምረው!

መልካም ቀን!
476 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 17:41:12 #ማድረግ_ተለማመድ

√ ጠዋት ከሰው ሁሉ በፊት ከእንቅልፍህ ተነስ
√ ቀንህን በጸሎት ጀምር
√ ውሎህን አቅድ
√ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርግ
√ ገላህን ታጠብ
√ የምትወደውን ልብስ ልበስ
√ ስራህን በሙሉ ትኩረት ስራ
√ የዛሬ ስራህን ዛሬ ጨርስ
√ በየቀኑ የንባብ ሰዓት ይኑርህ
√ ሰውነትህ የሚፈልገውን ያህል ብቻ ተመገብ
√ ብዙ ውሃ ጠጣ
√ በየቀኑ የቤተሰብ ሰዓት ይኑርህ
√ ለምታገኛቸው ሁሉ ሰዎች የደስታቸው ምክንያት ሁን
√ በየቀኑ ትንንሽ መልካም ነገሮችን አድርግ
√ ውሎህን ገምግመህ ፈጣሪህን አመስግነህ ተኛ
√ በቂ እንቅልፍ ተኛ

ስኬት እያዳንዷን ቀን በትክክል የመኖር ድምር ውጤት ነው!!

መልካም ምሽት!
560 viewsedited  14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ