Get Mystery Box with random crypto!

ዳግም ምጽዓት

የቴሌግራም ቻናል አርማ dagmele19 — ዳግም ምጽዓት
የቴሌግራም ቻናል አርማ dagmele19 — ዳግም ምጽዓት
የሰርጥ አድራሻ: @dagmele19
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 366
የሰርጥ መግለጫ

It's you find new Orthodox new
#ልጄ_ሆይ_እንዳትሆን_መናፍቅ_ሐይማኖትህን_እወቅ።
በዚህ ቻናል የእትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
መዝሙሮች እና ትምህርቶች ይገኛሉ።
ለሌሎች ሼር ያድርጉ
👉ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር👈
👇click & Share it 👇
@Dagmele19
🚷Leaveአትበሉችግርካለአሳውቁኝ
➛ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
በ @Dagmele19_Bot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-03 00:27:51 ''እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡

ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''
#ቅዱስ_ኤፍሬም

እኛስ እውነተኛ ጿሚ ልንባል ይገባን ይሆን?
@Dagmele19
1.0K views21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 00:27:30 "አሁን እየጾምክ ነው? እስቲ ጾምህን በተግባር አሳየኝ? የቱን ሰራህ? ድሃውን ባየህ ጊዜ ምህረትን አሳየው። ጠላትህን ስታየው ታረቀው። ስኬታማ የሆነ ወንድምህን ስታየው አትቅናበት በመንገድ የምትሔድ ሴትን ስታይ ዝም በለህ እለፋት። በአጠቃላይ አፍህ ብቻ አይጹም ነገር ግን ዓይንህ፣ እግርህ፣ እጅህ ሁሉም አካልህ ይጹም። እጅህ ከመስረቅና ከስስት ይጹም፣ እግሮችህ ወደ ኃጢአት ከመጓዝ ይከልከሉ፣ አይኖችህም በሌሎች ሰዎች ውበት ላይ ተተክለው ከመዋል ይጹሙ።

አሁን ስጋ እየበላህ አይደለም አይደል? በዓይንህም መጥፎ ነገር አትመልከት፤ መስማትንም ጹም። የፈውስ ጾም ክፉን አለመስማት የሌሎችንም ስም አለማጥፋት ነው። አንደበትም ከክፉና ከአጸያፊ ንግግር ይጹም። የዶሮና የአሳ ስጋ ከመብላት እንከለከላለን ነገር ግን የወንድማችንን ስጋ ስናኝክና ስንበላ እንውላለን። የወንድሙን ስጋ የሚበላ ደግሞ የተረገመና አሳች ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” እንዳለን። ገላ.5:15

ሆዳችንን ከምግብ ብቻ ባዶ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን ሁለንተና ሕይወታችንን ራሳችንንም የምንቆጣጠር እኛ ወደ መንፈሳዊ ነገሮች የምንመራ መሆን አለብን።"

(የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን ውርስ ትርጉም #መምህር_ንዋይ_ካሳሁን)
@Dagmele19
1.1K views21:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 23:27:59
Elohe_picture

ይቀላቀሉን

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk
451 views20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 23:27:24 ታኅሣሥ_፲፱ በዓለ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፡፡
ቅዱስ ገብርኤል፤
#ሊቀ_መላእክት_በመላእክት_ሁሉ_ላይ_የተሾመ_ነው_ሄኖክ_10፥14
#የአርባብ_የ10ሩ_ነገደ_መላእክት_አለቃ_ነው
#ከከበሩ_መላእክት_አንዱ_ነው_ሄኖክ_6፥7፤
#አካሉ እንደ ቢረሌ የሚመስል (ጽሩይ የሆነ) ፥ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ የሆነ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነው፡፡/ዳን.10፥5-9/
#መልአከ_ራማ_ዘራማ_ልዑል_ነው፤ (የራማ ልዑል ነው)
#አብሣሬ_ትስብእት_ነው፤
#መጋቤ_ሐዲስ_ነው፤ ቅዱሳንመላእክት
#በእግዚአብሔር_ፊት_የሚቆም_መልአክ_ነው_ሉቃ_1፥19፤
#ለቅዱሳን_እውቀትን_የሚገልጽላቸውና_ከአላውያን_የሚታደጋቸው_ነው_ /ድርሳነ_ገብርኤል/
#መልአከ_ሰላሞሙ_ወመልአከ_ኪዳኖሙ_መልአከ_አድኅኖ_መልአከ_ኀይል_መልአከ_ፍስሐ (የሰላም መልአክ ፥ የኪዳን መልአክ፥ አዳኝ መልአክ፥ ኀያል መልአክ ፥ የደስታ መልአክ ነው)
#ከሣቴ ጥበብ (ጥበብን የሚገልጽ ነው) /ት.ዳን./
#ናዛዜ_ኅዙናን_ (ያዘኑትን_የሚያጽናና_) መልአክ_ነው፨
✤ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፤ የወልደ እግዚአብሔርን መወለድ አብሥሯልና፨ አንድም የሁለት ቃለት ጥምር ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ሲሆኑ ትርጕማቸውም ገብር አገልጋይ ማለት ሲሆን ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው፤ በተገናኘ ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ/ ማለት ነው፡፡
✼ ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኃይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፥5-9) ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡
፠ “እነሆ ከዋነኞቹ አለቆች” አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”(ዳን.10፥13) ብሎ በተናገረው ንግግሩ በመላእክት ላይ የተሾሙ ሌሎች አለቆች እንዳሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምደር ያለውን የሚታየውንና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” (ቈላ.1፥16) በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡ ከዚህ ተነሥተን መላእክት በተለያዩ ዐበይት ነገዶች የተከፈሉና ለእያንዳንዱም ነገድ የራሱ የሆነ አለቃ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከ100ው ነገደ መላእክት መካከል ከበታቹ የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉት፤ ከተማቸውም በሰማየ ራማ ነው፡፡

✼ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ፤ እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን ቅዱስ ገብርኤል በመቃወም ‹‹ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ (ነአምሮ) ለአምላክነ “አይዟችሁ ፈጣሪያችን እስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” (አክሲማሮስ ገጽ.35) በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡

✼ ቅዱስ ገብርኤል በተወዳጁ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል አድርጓል ራእ12፥7፤ ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” (ኢሳ.14፥16) በማለት ገለጠልን፤ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡

✼ ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል (ሉቃ 1፥19)፤
✼ ታላቁ ነቢይ ሄኖክም ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መስክሯል ‹‹በአበቦች ላይ በገነትም በጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው፡፡›› ሄኖክ 6፥7፤ ‹‹በሦስተኛውም በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ሄኖክ 10፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል፡፡

** ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ነገር ግን ያደረጋቸው ተዓምራቶች በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በመልክኡ፣ በድርሳኑ፣ በተአምሩ፣ …. የተጻፉ ቢሆንም፤

✤✼ ታኅሣሥ 19 ካደረጋቸው ተራዳኢነት..
፠ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) ያዳናቸው ያዳነበት ቀን ነው፡፡ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) የፋርስ ባቢሎን ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር በዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ ላቆመው ጣየዖት ምስል ስገዱ ሲላቸው …. የምናምነው አምላክ ያድነናል፤ ባያድነን እንኳን (አምላካችን በእሳት ሰማዕት እንድንሆን ፈቃዱ ቢሆነረ አንኳን) አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም ብለውታል፡፡ ንጉሡም ወደ እቶን እሳት እንዲጣሉ አድርጓቸዋል፤ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ግን ከእቶን እሳቱ የልብሳቸው ዘርፍ እንኳን እሳት ሳይነካው ከእሳቱ ድነዋል፡፡እኛንም ያድነን አሜን::
እንዲሁም ታኀሣሥ 19፤

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሀገረ_ቡርልስ_በዓለ_ዕረፍቱ_ እንዲሁም
#ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ስነ_ኢየሱስ_ (#ገዳማቸው_በሰሜን_ጎንደር_ትክል_ድንጋይ_አካባቢ_የሚገኘው_) #በዓለ_ዕረፍታቸው_ነው_፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/
#share
T.me/dagmele19
445 views20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-27 15:06:15 አሰበላችብህ..........
በድሮ ጊዜ አንድ እረኛ ነበረ ታድያ ከብቶቹን ወደ መስክ ይዞ
ሲወርድ የግጦሽና የውኃ ቦታ እየራቀው እሱም እየደከመው
ሲመጣ አንዳንድ ጊዜ ከብቶቹን ሜዳ ላይ በትኖ ወደ ቤቱ
ይመለሳል።
ቤተሰቦቹ ከብቶቹስ? ሲሉት "ለቅዱስ ሚካኤል
አስጠብቄያቸዋለሁ" ብሎ በዕምነት ይናገራል። በማግስቱ ሲሄድ
ከብቶቹ አውሬ ሳይነጥቃቸው፣ ሽፍታ ሳይንዳቸው፣ ከቁጥር
ሳይጎድሉ በደሕና ያገኛቸዋል።
በዚሁ መሠረት አንድ ጊዜ ለቅዱስ ገብርኤል፣ ሌላ ጊዜ ለቅዱስ
ጊዮርጊስ በአደራ አስጠብቄያቸዋለሁ እያለ ይናገር ነበር። ታድያ
አንድ ቀን ወላጅ አባቱ "ዛሬስ ለማን አስጠበክምቸው?" ብለው
ይጠይቁታል። እሱም ኮራ ብሎ "ዛሬ ለእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም አስጠብቄያቸዋለሁ" አለ።
ተናግረውት የማያውቁት አባት "አዬ ልጄ እሷማ አስበላችብህ
አሉት" መጠነኛ ፈገግታ እየፈገጉ። ልጁ የአባቱ ንግግር አላምር
ብሎት "እንዴት አባባ እመቤቴ የእኔን ከብቶች መጠበቅ አቅቷት
ነው የምታስበላብኝ?" ብሎ አባቱ ላይ አፈጠጠ።
አባቱም "አየኸ ልጄ እሷ ርህሪት በመሆኗ የራበው ጅብ ከመጣ
አትከለክለውም፤ ያንተን ከብት እንዲበላ ታሰናብተዋለች እንጂ"
አሉት። ልጁ ይኽን ሲያስብ "እውነትም ታስበላብኛለች" አለና ወደ
ከብቶቹ ሂደ።
በዚህ ታሪክ ማስተላለፍ የተፈለገው የእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያምን ርህራሄና አዛኝነት እንጂ ሌላ ነገር አይደለም።
ለተጠማ ለውሻ የራራች ለጅቡም ከተራበ ለእርሱ ትራራለች
ብለው ነው። ድንግል ማርያም ኃጢአቱን ለሚያምን ሁሉ ከልጇ
ከወዳጇ ምሕረትና ይቅርታን ለምና ታሰጣለች።
ረድኤቷ፣ በረከቷ፣ ፈጣን ምልጃዋ አይለየን
564 views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-27 14:34:27 ​አንድ ወጣት ድምፁን ከፍ አድርጎ ድንግል ማርያም አታማልድም አታማልድም እያለ በአደባባይ ይጮሃል:: ከዛ ድንገት እያለፉ የነበሩ አንድ አባት ድምጽ ይስሙና ወደ ወጣቱ ጠጋ ብለው ልጄ አንዴ ላስቸግርህ ከዛ ፊት ለፊት ካለው ሱቅ 1 ኪሎ ብርትኳን አምጣልኝ አሉት ወጣቱም እሽታውን ገለፀላቸው አባትም ብርትኳኑን አንዳችም ሳያስቀሩ ከበሉ በኃላ ልጄ ብርትኳኑ እንዴት ነው? ይጣፍጣል አይደል ?አሉት ወጣቱም አንዴ ሰውዬ ያምዎታል እንዴ ብርትኳኑን እኮ ብቻወትን ነው የበሉት እና እንዴት ጣሙን ላውቅ እችላለሁ አላቸው በተረጋጋ አንደበት አባም አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ ብርትኳን የድንግል ማርያም ጣዕሟ አልገባህም ስለዚህ ልጄ ወደ ቤቷ ግባ ጣዕሟንም ቅመሰው ያኔ የድንግል ጣዕም ይገባሃል አሉት ይባላል፡፡



እኛስ ተመርጠን ምልጃዋን ተቸርን፣ ረድኤቷን ቀመስን ክብር ምስጋና ይግባት።
424 views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 18:33:36 "እንኳን ለጾመ ነብያት አደረሳችሁ"
ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውን ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ድረስ በአምላካችን ቅዱስ ፈቃዱ እንጾማለን!

እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ ከንጽሕተ ንጹሓን፣ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም መወለዱን፣ ወደ ግብጽ መሰደዱን፣ በዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርተ ወንጌልን ማስታማሩን፣ በመጨረሻም በሞቱ ሞትን ማጥፋቱን፣ ትንሣኤውንና ዕርገቱን ሁሉ አስቀድመው የተነሡ ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ትንቢት በተናገሩት መሠረት ተፈጽሟል፡፡ ነቢያቱም ትንቢታቸው እንዲፈጸም ‹‹አንሥእ ኀይለከ ፈኑ እዴከ፤ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው መምጫውን በጊዜ እየለኩ ሲጠባበቁ ኑረዋል። ትንቢቱም ጊዜው ሲደርስ ተፈጽሟል፡፡ እኛም ከዚህ በመነሣት ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሠረት ልንጾም ይገባናል፡፡

ጾሙ የሚጠራባቸው ስያሜዎች
፩.ጾመ ነቢያት
ይህ ጾም ከላይ ለመግለጥ እንደሞከርነው ሁሉ ነቢያት የእግዚአብሔርን ሰው መሆንና ዓለሙን የሚያድነበትን ጊዜ እየተጠባበቁ የጾሙት በመሆኑ ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም) ተብሏል።
፪. ጾመ አዳም
ለአዳም የተነገረው የድኅነት ተስፋ ስለመፈጸሙ የተሰጠው ስያሜ ነው።
፫. ጾመ ስብከት
ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት በመሆኑ ጾመ ስብከትም እየተባለ ይጠራል።
፬. ጾመ ሐዋርያት
ሐዋርያት በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እንፈታለን፤ በዓለ ልደትንም ይህን ጾም ጾመን እንፍታ ብለው ሲጾሙት ስለነበር ጾመ ሐዋርያት ይባላል።
፭. ጾመ ፊልጶስ
ሐዋርያው ፊልጶስ በአፍራካ አውራጃዎች በመዘዋወር ወንጌልን እየሰበከና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ያመኑትን እያጸና፣ ያላመኑትን እየመለሰ ቆይቶ በሰማዕትነት ዐረፈ። ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ቢሹ አጡት፤ ተሰውሮባቸው ነበርና። እግዚአብሔር እንዲገልጥላቸው ሱባኤ ይዘው በጾም በጸሎት ቢለምኑት በሦስተኛው ቀን ተገልጦላቸዋል። እነሱም በክብር አሳረፉት። ጾሙን ግን እስከ ጌታ ልደት ቀን ድረስ ጹመውታል። በዚህም ምክንያት ጾመ ፊልጶስ እየተባለ ይጠራል።
፮. ጾመ ማርያም
እመ አምላክ፣ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ወልደ እግዚአቤሔርን እንደምትወልደው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቢያበሥራት ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ፀንሼ፣ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ›› በማለት በትሕትና ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጹማ ነበርና ጾመ ማርያም ተብሏል።
እንግዲህ ከላይ ያየናቸው ቀደምት ቅዱሳን በዚህ ጾም ተጠቅመውበታል። እኛም አምላካችን ምሕረት ይሰጠን ዘንድ እንዲሁም ከቅዱሳኑም በረከት እናገኝ ዘንድ ልንጾመው ግድ ነው።
ተወዳጆች ሆይ! ስንጾም እነዚህን ነገሮች ልብ ማለት ይገባል።
ሀ. በእምነት ሁነን መጾም፦ እግዚአብሔር ይሰማኛል፤ ዋጋ አገኝበታለሁ ብለን እያመንን መሆኑን ማስተዋል ይገባል።
ለ. በፍቅር መጾም፦ ከወንድሞችና ከእኅቶች ጋር በመስማማትና በአጠቃላይ ክፋት በማይታሰብበት ልቡና ሆኖ መጾም ያስፈልጋል።
ሐ. ንስሓን፣ ጸሎትን፣ ምጽዋትን፣ ይቅርታን ገንዘብ በማድረግ መጾምን አለብን።
መ. ከክፉ ነገር ሕዋሳቶቻችንን ዐቅበን (ጠብቀን) መጾም፦ ዐይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር፣ አፍ ይጹም ብሎ እንደነገረን ቅዱስ ያሬድ እኛም ከክፉ ሁሉ ተከልክለን እንዲህ ባለው አኳኋን ከጾምን ቸሩ አምላካችን ምሕረቱን ይልክልናል።
በመጨረሻም ስንጾም በመከራ ውስጥ ስላሉት ወገኖቻችን እያሰብን እንዲሁም ሁሉም ነገር መልካም የሚሆነው ሀገር ሰላም ሲሆን ነውና ለሀገራችን ሰላምን፣ ለሕዝቦቿም ፍቅር፣ አንድነትን እያሰብን አምላካችንን እንለምነው።
የራሔልን ዕንባ የተቀበለ አምላካችን ጾማችንን ይቀበልልን፤ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

t.me/Dagmele19
413 views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 17:48:04
364 views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 17:47:45
354 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 17:47:19 [የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ክብር]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ [በድጋሚ የተለጠፈ]
❖መልአክ የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲኾን “ለአከ” ማለት (ላከ) ማለት ነው፤ ስለዚኽ መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው፤ ይኸውም ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው የሚያመላልሱ የሚላኩ ስለኾነ የተሰጣቸው ሥያሜ ነው፡፡

❖ ልዑል እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ በዚያው በዕለተ እሑድ መላእክትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ማእምራን (ዐዋቂዎች) ለባውያን (አስተዋዮች) አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ከነዚኽ መላእክት ውስጥ አንደኛውና የመላእክት አለቃ የኾነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

❖ ቅዱስ ሚካኤል የሚመራቸው ነገደ ኀይላት የሚባሉ በኢዮር ሰማይ የሚኖሩ መላእክትን ነው፤ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለራብዕ ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኀይላት ወሊቆሙ ሚካኤል ወአንበሮሙ በራብዕ ሰማይ” ይላል አራተኛው ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኀይላት ሲላቸው እነዚኽም ባለሰይፍ ሲኾኑ የእግዚአብሔርን ወዳጆች ሲጠብቁ ጠላቶቹን ይቀጣሉ፤ የእነዚኽ ነገደ መላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ሲኾን በኢዮር በአራተኛው ከተማ አስፍሯቸዋል እንዲል፡፡

❖ ሳጥናኤል “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ብሎ የስሕተት ንግግርን በተናገረ ጊዜ አስቀድሞ ሰራዊቱን በመያዝ ከነገደ ዲያብሎስ ጋር የተዋጋ መልአክ ነውና፤ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ኀያልነት በራእ ፲፪፥፯-፱ ላይ፡- “በሰማይም ሰልፍ ኾነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም ዓለሙንም ኹሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ ርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከርሱ ጋር ተጣሉ” በማለት ዲያብሎስን የተፋለመ መልአክ መኾኑን ገልጾታል፤ በዚኽም “መልአከ ኀይል” ተብሏል (ዳን ፲፥፲፫፤ ፲፥፳፩፤ ፲፪፥፩)፡፡

❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡-
ስለ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃነቱ ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይለዋል፡-
╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ
በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ
ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ
ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ”
(የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡-

❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ፡-

╬ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ
ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ
እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ
ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ”
(የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና)

╬ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት
ለሚካኤል ሊቀ መላእክት
ዘይስእል በእንተ ምሕረት
መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት”
(የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡

❖የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡
የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ
╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ
ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ”
(የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

❖ቅዱስ ያሬድም፡-
╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ
ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ
መልአኮሙ ሥዩሞሙ
የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ”
(ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል

❖በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር፤ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡-
╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ
ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ”
(መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው)

❖የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡-
╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ
ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ”
(የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

❖ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡-
╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ
ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
ሐመልማለ ወርቅ”
(ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡

❖የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡-
╬ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ
በመንክር ትሕትናከ
አስተምህር ለነ ሰአልናከ”
(በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ)

╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ
አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ
ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ
ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ”
(ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡

╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንዲል።

❖ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡- ለምሳሌ ያኽል ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡
የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በረከት ይደርብን፤ መልካም በዓል፡፡
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
391 views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ