Get Mystery Box with random crypto!

OMEGA SCHOOL A.A SINCE 1989 E.C

የቴሌግራም ቻናል አርማ omegaschoolaa1989 — OMEGA SCHOOL A.A SINCE 1989 E.C O
የቴሌግራም ቻናል አርማ omegaschoolaa1989 — OMEGA SCHOOL A.A SINCE 1989 E.C
የሰርጥ አድራሻ: @omegaschoolaa1989
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.25K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-06 18:44:07
787 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 10:08:35
#ማስታወቂያ

መስከረም 30/2015 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መስከረም 26-28 ተጠቃለው  በመግባት መስከረም 29 ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች  ገለጻ የሚደረግበት ዕለት መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ሆኖም የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29/2015 ዓም እሁድ ጠዋት  መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑን እና የፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ /Orientation/ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እሁድ ከሰዓት በኋላ እንዲሰጥ መደረጉን በአክብሮት እየገለጽን የእምነቱ ተከታይ ተማሪዎችም ይህንን አዉቃችሁ በተጠቀሰዉ ሰዓት በመገኘት ገለጻ /Orientation/ እንድትከታተሉ እናሳስባለን ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር !
1.2K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 10:08:13
1.1K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 16:47:09 #ለወላጆች

" ወላጆች ያምኑናል ብለን ተስፋ እንደርጋለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ከቤተሰባቸው ርቀው ነው ፈተናውን የሚወስዱት በዚህ ወቅት ስልክን ጨምሮ ምንም አይነት የመገናኛ ቁሳቁስ ይዘው መሄድ አይችሉም ፤ ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት ባለመቻላቸው የሚፈጠር #የስነልቦና_ጫና ይኖር ይሆን ? ይሄ እንዴት ይታያል ? የወላጆች ኃላፊነትስ ምንድነው ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተናገሩት ፦

" .... ሆን ብለው ችግሮችን ለመፍጠር ካሰቡ ብዙ ምክንያቶችን ማድረግ ይቻላል ግን አሁን እነዚህ ልጆች ማትሪክ ሲያልፉ ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሊኖሩ ነው አይደለም እንዴ ለረጅም ጊዜ ፤ ለአራት ቀን ለአምስት ቀን ሲሆን እንደውም በዛ እድሜ ላይ ያሉ ልጆች ደስ እያላቸው የሚሄዱ ነው የሚመስለኝ።

ይሄ አድቬንቸርም ነው ከቤት ወጥተው ፣ ዩኒቨርሲቲ ሄደው ይፈተናሉ ይሄ አዲስ ነገር ነው። በዚህ አመት ለሚያደርጉት ይሄ ነገር የተጀመረው የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች ስለሚሆኑ ለልጆቻቸውም የሚነግሩት ነገር ይዘው ነው የሚሆነው ፤ ታሪካዊም ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ይሄ የተደረገው ፤ በእኛ ጊዜ ነው ይሄ የሆነው ፣ ይሄ ነገር ምን አለው የሚለውን ያያሉ።

በእኛ በኩል ዋና ኃላፊነታችን ሰላማቸው እንዲጠበቅ ማድረግ ፣ በምግብ ችግር እንዳይኖርባቸው ማድረግ ፣ ህክምና ማዘጋጀት በየዩኒቨርሲቲዎቹ ይሄንን እያዘጋጀን ነው።

ሰላም መግባታቸውን ፣ ችግር በሚኖር ጊዜ ለማሳወቅ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ተወካዮች አሉ አብረው የሚመጡ ወደ ግቢ አይገቡም ፤ ግን ችግር በሚኖር ጊዜ ከእነሱ ጋር ግንኙነት እየተደረገ ለቤተሰቦቻቸው መንገር የሚቻልበትን መንገድ አስቀምጠናል።

ሁሉን ነገር ለማየት ሞክረናል ይሄ ነገር አዲስ ስለሆነ ቀላል የሎጅስቲክስ ስራ አይደለም አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ሰው አንቀሳቅሶ ይሄን ማድረግ በተወሰነ ደረጃ እንደ ሀገርም ያውም ጦርነት እየተዋጋን ባለንበት ሁኔታ መንግስት ይሄን ማድረግ መቻሉ በእውነት የሚገርም ነው። እኛ ውስጥ ስላለንበትም እያየን ስለሆነ ነው ይሄን የምናገረው ቀላል የሎጅስቲክስ ስራ አይደለም።

እጅግ በጣም ብዙ ሰው ነው የሚሳተፍበት ወደ 8 ሺ የፌዴራል ፖሊስ ይሳተፍበታል ፣ ሰላሳ / አርባ ሺህ ፈታኞች ከየዩኒቨርሲቲው ወጥተው ይሳተፋሉ ፣ ብዙ ምግብ አብሳዮች ይሳተፋሉ። በአጠቃላይ ትልቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ነው። እንደ ሀገርም ችሎታችንን አቅማችንን፣ በተወሰነ ደረጃ እየተጠናከረ ትላልቅ ነገሮችን ለመስራት ያለን ብቃት እየጨመረ የሚሄድበት ነው ፤ ስለዚህ ደስ የሚልም ነገር አለው።

ለቤተሰቦች የምንለው በተቻለን መጠን የልጆቻችሁን ኃላፊነት ወስደን ነው ይሄን ነገር የምንሰራው። እንደ ልጆቻችን ልንጠብቅ ፣ እንደ ልጆቻችን እንዳይራቡ እንዳይጠሙ ልናደርግ ፤ ምንም አይነት የደህንነት አደጋ ውስጥ እንዳይገቡ ተጠንቅቀን ነው ይሄንን ነገር የምናደርገው። ያ ማለት ግን ምንም ነገር አይፈጠርም ማለት አይደለም መቶ በመቶ ማረጋገጫ መስጠት አይቻልም።

ማንኛውም ተማሪ ወደዚህም ቦታ ባይመጣ ቤቱም ሆኖ ሊታመም ይችላል ግን በእኛ በኩል ከህክምና ጋር በተያያዘ የጤና ባለሞያዎችን በየቦታዎቹ ላይ አስቀምጠናል ፤ ችግር በሚኖር ጊዜ ልጆቹ ህክምና እንዲያገኙ።

ቁርሳ ፣ ምሳ እንዲሁም እራታቸውን እንመግባቸዋለን ፤ ምግብ እንኳን ስናዘጋጅ የሃይማኖት ፤ የባህል ነገሮችም እንዳይመጡ እሱን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረግን ነው። ወላጆች ያምኑናል ብለን ተስፋ እንደርጋለን።

...ወላጆች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። ልጆቻቸው ወደ ፈተና በሚሄዱበት ጊዜ ትብብር ማድረግ ፤ ፈተናውን ለመፈተን በሚሄዱበት ጊዜ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ ከቤት ነው ይሄ ነገር የሚጀምረው ምክንያቱም የ12 ዓመት ጥረት አፈር ነው የሚገባው አንድ የተከለከለ ነገር ይዘው ቢገቡ ፤ ስለዚህ እኛ እንደውም ፍተሻው ፖሊስ ጋር መጥቶ ከመድረሱ በፊት ቤት ወላጆች ናቸው አይተው መላክ ያለባቸው።

ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጧቸው የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ይኖራሉ ለምሳሌ ፦ እንደ ደረቅ ምግብ ድንገት ለሊት ሲያጠኑ ቢያስፈልጋቸው ቆሎም ይሁን ሌላ የሚሰጧቸው ነገር ካለ ፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ እነዚህን እንደሚያዚዟቸው ሁሉ የዛን ያህል የተከለከሉ ነገሮችን እንዳይዙ መቆጣጠር አለባቸው፤ ይህንንም ያደርጋሉ ብለን እናምናለን።

ከዛ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚጮኸውን አለመስማት ነው ፤ ምክንያቱም ዋነኛው ስራቸው በእንዲህ አይነት ነገር ማህበረሰብን ማሸበር እንደ ችሎታ እና እንደእውቀት የወሰዱ ጤነኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎች ያሉበት ዘመን ላይ ነው ያለነው።

ወላጆች የልጆቻችሁን ጉዳይ በሚመለከት በቀንጥታ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር፤ የምንነግራችሁ ቁጥሮች አሉ፣ የምንልካቸው የአካባቢው ትምህርት ተወካዮች አሉ በዛ በኩል መገናኘት ያስፈልጋል።

አንድ ነገር ቢፈጠር #በእርግጠኝነት የምንነግራችሁ ፤ ከእኛ ውሸት አትጠብቁ የሆነውን ነገር ይሄ ነው የሆነው ብለን እንነግራችኃለን። ምንም የምንደብቅበት ምክንያት የለም።

ይሄ የፖለቲካ ስራ አይደለም ፤ ይሄ የትምህርት ስራ ነው።  የትምህርት ስራ ደግሞ ሁላችንንም የሚያገናኝ እና የሚያጣብቅ ስራ ነው።

ወላጅን ከአስተማሪዎች፣ አስተማሪዎችን ከአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱና ከትምህርት አስተዳዳሪዎች ጋር የሚያይዘው ውስጣችን ለልጆቻችን ጤንነት ፤ ለልጆቻችን የእውቀት ጥማት እና ህይወትን ለማሻሻል የሚያደርጉትን ጥረት ከማገዝ በላይ ምንም ሌላ ነገር የለም ከዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ጥቅም ሆነ ትርፍ የለም።

ይሄን ማወቁ ምንም የፖለቲካ ልዩነቶች እንኳን ቢኖሩ ትምህርትን የዛ መጠቀሚያ አናድርገው ፣ ትምህርትን ከዛ ውስጥ እናውጣው ትምህርት ስለልጆቻችን ነው። "

@tikvahethiopia
1.6K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 16:46:40
1.5K views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 12:29:21 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ለተፈታኞች የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ነገሮች ያቀረቡ ሲሆን በዚህም
የተፈታኞች መብቶች የሆኑት፡-
ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት
በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት
ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት
የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት
. በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት
ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት
የተፈታኞች ግዴታ የሆኑት፡-
. ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ
ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት
ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ
ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም
ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት
ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ
ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት
ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት
ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት
ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት
ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት
ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች
አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
ገንዘብ (ብር)
የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው
ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሓኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)
ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
1.1K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 11:57:55
1.2K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 11:56:25
1.2K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 11:55:54 ለኦሜጋ ትምህርት ቤት የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ
፨፨፨     ፨፨፨፨   ፨፨፨፨    ፨፨፨
ቀን 23/01/2015 ዓ.ም
በመጀመሪያ የማክበር ሰላምታችን እያቀረብን የ2014 12ኛ ክፍል ተፈታኞች የፈተና የጊዜ ሰሌዳ፣ የተፈታኞች መብት እና ግዴታ፣ በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ነገርች ከዚህ ቀጥሎ የምንለቅ ሲሆን ወላጆች ለተማሪዎቹ በማሳዬት ተማሪዎች ደግሞ ተግባራዊ እንድታደርጉ ት/ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል።
1.2K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ