Get Mystery Box with random crypto!

Abu-Hureyra-አቡ ሁረይራ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nurmesjidgondar — Abu-Hureyra-አቡ ሁረይራ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ nurmesjidgondar — Abu-Hureyra-አቡ ሁረይራ
የሰርጥ አድራሻ: @nurmesjidgondar
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 652
የሰርጥ መግለጫ

#የዚህ ቻናል ዋነኛ አላማ
:- ኢስላማዊ ትምህርቶችን, ምክሮችን እና ታሪኮችን
👉 የስነ-ልቦና ትምህርቶችን
👉 የስነ-ልቦና ምክሮችን
👉 አነቃቂ ፅሁፍ እና አነቃቂ ንግግሮችን
👉መፅሐፍትን
👉ጥቅስ እና አባባሎችን
👉ፍልስፍና,ሳይንስ እና ጠቅላላ ዕዉቀትን በማቅረብ መልካም ስብዕናን፣ ዕዉቀትን እና በጎ አሰተሣሠብን ሰወች እንዲላበሱ ማድረግ ነዉ!
ለአስተያየትዎ - @JAMALUDIN4992

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 11:55:03 ተክቢራ አንርሳ

#Share
#Share
#Share

@nurmesjidgondar
129 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), edited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 11:01:19
#ማሻላህ

#Share
#Share
#Share

@nurmesjidgondar
122 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), edited  08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:36:22
በዛሬው የአረፋ ቀን በብዛት ማለት የሚወስድ ዚክር

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ

‹ላኢላሀ ኢልለሏሁ ዋህደሁ ላሸሪከለህ፣ ለሁል ሙልኩ፣ ወለሁል ሐምድ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር።

› «ከአላህ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው››

#Share
#Share
#Share

@nurmesjidgondar
122 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:32:23 ¦

በህይወትህ ያጣኸውን፣ የሌለህን እየቆጠርክ ያልተገባ አመለካከት ከመያዝህ በፊት እስኪ እራስህን በደንብ ተመልከተው። አንተ ጋር፣ ባንተ ውስጥ፣ ባንተ ላይ፣ ባንተ ዙሪያ፣ ባንተ እጅ ገንዝብ ሊግዛቸውም ሆነ ሊተካቸው የማይችላቸው ብዙ ብዙ ነገሮች አሉ። ወዳጄ አይንህን፣ ሃሳብህን፣ ልብህን ወደ ማዶ አሻግረህ ከመሄድህ በፊት፣ ስሌለህ ነገር እያሰብክ እንደተበዳይ እራስህን ከመውሰድህ በፊት ወደ ውስጥህ ተመልከት።

#Share
#Share
#Share

@nurmesjidgondar
131 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:51:39 አስታውስ ማስታወስ ለ ሙእሚኖች ይጠቅማልና።(50:55)
ከአቢ ቀታዳህ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ። እንዲህም
አሉ፡-
ﻳﻜﻔِّﺮ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﻤﺎﺿﻴﺔ ﻭﺍﻟﺒﺎﻗﻴﺔ
“ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል
ያብሳል።” [ኢማም ሙስሊም እና አህመድ ዘግበውታል]
የአረፋ ቀን (ዙልሂጃ 9 ማለትም ነገ ጁመዓ ይውላል፡፡

Suayya Sualih

S@@z

#Share
#Share
#Share

@nurmesjidgondar
148 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:10:49 በቂያማ ትርምስ መሀል ድንገት ተጣሪ ስምህን ከሰዎች ለይቶ በጩኸት ይጠራኻል። ትርበተበታለህ፣ ትወለጋገዳለህ፣ እግሮችህ አንተን መሸከም ይሳናቸዋል። ያሳለፍከውን የአመፅ ህይወት እያወራረድክ በመላዕክት ተቀፍድደህ ከተጠራህበት ስፍራ ላይ ብቻህን እንድትቆም ትደረጋለህ።
ስትፈራ፣ ስትቸር፣ ስትርበተበት አንገትህን አቀርቅረህ የምትገፈተርበትን የጀሀነም ሸለቆ እያሰብክ ሳለ ድንገት ከፊትህ መዛግብት ይዘረጋልኃል። አንዱ መዝገብ የአይንህን አድማስ ተሻግሮ ትመለከተዋለህ። ጫፉን አታየውም። ትደነግጣለህ። የሱ ድንጋጤ ሳይለቅህ ሌላ ተመሳሳይ 99 መዝገቦች ከፊትህ ይዘረጋጋሉ። ውስጡን እንድታይ ትደረጋለህ። ስትመለከተውም ከህይወት ጅማሬ እስከፍፃሜው የቀጠፍካቸው ወንጀሎች በሙሉ ሰፍረው መልካም ስራዎችህን ውጠዋቸው ታገኘዋለህ።
ተስፋ ትቆርጣለህ። አፍህ ይለጎማል። ጀሀነም ላይ ክፍል እንደተዘጋጀልህ ታስባለህ። ያኔ አፈር ሁነህ ብትቀርም ትልቁ ምኞትህ ይሆናል።
ድንገት የመዝገቦቹ ተሳሳቢህ፦ ‹‹የምታስተባብለው አለን?›› ሲል ይጠይቅኃል!
ተስፋ በቆረጠ አንደበት፦‹‹አላስተባብልም›› ብለህ በገዛ ነፍስህ ላይ መስካሪ ትሆናለህ።
‹‹መዝጋቢዎቹስ በድለውኃልን›› ብሎ ዳግም ይጠይቅኃል? አንገትህን እንዳቀረቀርክ፦ ‹‹አልበደሉኝም›› ትላለህ ስራህን ስለምታውቅ።
‹‹ታድያ በምን ታስተባብላለህ? ከዚህ የሚታደግህ መልካም ተግባር ይኖርሃል?›› ብሎ ይጠይቅሀል።
‹‹የለኝም›› ትላለህ ሁሉ ጨልሞብህ።
‹‹አንድ መልካም ስራ እኛ ዘንድ አለችህ፤ እሷም ትመዘናለች ዛሬ እኛ ዘንድ ማንም አይበደልም›› ይልህና አንዲት ብጣሽ ወረቀት ይመዝልኃል።
‹‹ጌታዬ እሷን ባትመዝናትስ? ይኼን ሁሉ የኃጥያት መዝገብ ከዚህች ብጣሽ ወረቀት ልታመዛዝን›› ትለዋለህ።
ንግግርህ ወድያ ተትቶ ሚዛንህ ላይ አድማሳትን ያካለለው የኃጥያት መዛግብትና ይህች ብጣሽ ወረቀት ይጫናሉ። ብጣሿ ወረቀት ያን ሁላ መዛግብት ከመመዘን አልፋ መዛግብቱ በሰማይ ላይ ይበታተናሉ።
ደስታ ምትሆነውን ያሳጣሀል። ተስፋህ ይለመልማል። ህይወት ታጓጓኃለች። ዕጣፋንታህን ቀይራ ለጀነት የዳረገችህን ወረቀት ስትመለከትም የጌታህን እና የነበይህን ስም ተፅፎበት ታገኘዋለህ።
‹‹ላ ኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱን ረሱሉላህ››

#Share
#Share
#Share

@nurmesjidgondar
136 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), edited  07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 12:36:35 አንድ ንጉስ አስር አመት ሙሉ በታማኝነት ያገለገለው አገልጋዩ እንዲት ስህተት ስለሰራ ብቻ ቅጣትን አስተላለፈበት፡፡ በንጉሱ ሕግ መሰረት ማንኛውም ስህተት የሰራ አገልጋይ በኃይለኛነታቸውና በተናካሽነታቸው የታወቁት የንጉሱ ውሾች ወደሚኖሩበት ግቢ ለቅጣት ታልፎ ይሰጣል፡፡

ይህንን የንጉሱን ውሳኔ የሰማው ታማኝ አገልጋይ በሁኔታው በጣም አዘነ፡፡ እሱን ያሳዘነው የተላለፈው ቅጣት ሳይሆን፣ ለአስር አመታት ካለምንም ስህተት አገልግሎ፣ አንዲት ስህተት ብቻ ስለተገኘችበት የንጉሱ መጨከን ነው፡፡

ይህ አገልጋይ ቁጭ ብሎ፣ “ይህንን ቅጣት አስቀረሁትም፣ አላስቀረሁት ንጉሱ ግን ይህንን ጥሩ ያልሆነ ልምምድ የሚያቆምበትን አንዲት ትምህርት ባስተምረው ደስ ይለኛል” ብሎ አሰበና አንድ ብልሃት መጣለት፡፡

ንጉሱንም፣ “ቅጣቱን እቀበላለሁ፣ ቅጣቱ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ግን አስር ቀን ይሰጠኝና ከዚያ በኋላ በፈቃዴ ለቅጣቱ እመጣለሁ” ብሎ ጠየቀው፡፡ ንጉሱም ፈቀደለት፡፡

በእነዚህ አስር ቀናት ለውሾቹ የሚሆንን ምግብ አዘጋጅቶ እነሱ ያሉበት ግቢ በመሄድና ቀስ ብሎ በመቅረብ እያበላቸው፣ እየተንከባከባቸውና እያሻሻቸው በሚገባ ካገለገላቸው በኋላ በአስረኛው ቀን ወደ ንጉሱ መጣ፡፡ ፍርዱ አልቀረለትም ነበረና ወደውሾቹ ግቢ እንዲጣል ትዝዛዝ ተላለፈበትና ተጣለ፡፡ ውሾቹ ለአስር ቀን የተንከባከባቸውንና ያገለገላቸውን ይህንን ሰው ምንም ነገር አላደረጉትም ነበር፡፡

ንጉሱም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሁኔታ በመሆኑ ተገርሞ አስጠራውና የተፈጠረውን ጠየቀው፡፡ አገልጋዮም፣ “ንጉስ ሆይ፣ እርሶን አስር አመት በታማኝነት አገልግዬ አንዲት ጥፋት ስለተገኘብኝ ብቻ ያ ሁሉ ታማኝነቴና አገልግሎቴ ተረሳና ምህረትም አላገኘሁም፡፡ እነዚህ ውሾች ግን ለአስር ቀናት ብቻ ስላገለገልኳቸው ምንም እንኳን ጥፋተኛ ሆኜ ለእነሱ ታልፌ ብሰጥም ያንን አገልግሎቴን ባለመርሳት ምንም አላደረጉኝም” አለው ይባላል፡፡

ንጉሱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህንን ባህሪውን ለማረም ክፍት ወደመሆን እንደመጣ ይነገራል፡፡

ሰዎች ያሳዩንን የብዙ ዓመታት ታማኝነትና አገልግሎት በአንዲት ስህተት ምክንያት በዜሮ አናባዛው፡፡ ይቅርታን እንልመድ! ለሰዎች ሁለተኛ እድልን መስጠትን እንልመድ! ውለታ ቢሶች አንሁን!

#Share
#Share
#Share

https://t.me/nurmesjidgondar
151 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), edited  09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 12:35:15 ለማስታወስ

የዙልሂጃ ማለትም የዚህ ወር 9ኛውን አረፋን መፆም ትልቅ አጂር ያለው ነውና ካሁን እሰቡበት። ቀኑም #ጁሙዐ ቀን ነው። ንያው በቀልብ ነው እንዲህ እንላለን (ነወይቱ ሰውመ የውሚ አረፋ)(نويت صوم يوم عرفة)

ቀዷ ያለበት ቀዷውን ካሁን ይፁም።

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን።

#Share
#Share
#Share

https://t.me/nurmesjidgondar
128 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), 09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:59:04
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን.

ምን ያማራ ኻቲማ

ሃጅ ለማድረግ ከሀገሩ መጥቶ በመካ ወደ አኼራ ሄዷል
አላህ ጀነተል ፍርዶውስ ይወፍቀው

#share
#share
#share

@nurmesjidgondar
206 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:09:33
ሁጃጆች እንዲህ እጅግ ባማረና በተዋበ መልኩ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።

➲ያኢላሂ ይችን ቀን ለኛም ወፍቀን አንተ ሁሉን ቻይነህና!

#Share
#Share
#Share

@nurmesjidgondar
226 viewsÅĐĤÅM-ĴÅMÃŁŮĐÏŇ (ÅJ), edited  17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ