2022-06-06 10:23:36
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council Official
የሐጅ በረራ ሽግሽግ እና የጉዞ ሰነድ መረከቢያ ቀንን ማሳወቅን ይመለከታል ።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ለሰኔ 1 ለሰኔ 2 ለሰኔ 3 ለሰኔ 4 ለሰኔ 5 እና ለሰኔ 6 የጉዞ ሰነድ መጅሊስ ግቢ ለመረከብ እንድትመጡ ቀጠሮ የተሰጣችሁ ሁጃጆች የበረራ ሽግሽግ ስለተደረገ የምትመጡት ከሐጅ ምዝገባ ቁጥር
1. ከ1 እስከ 820 የተመዘገባችሁ ሰኔ 8 ነው ።
2. ከ821 እስከ 1640 ያላችሁ ሰኔ 9 ነው ።
3. ከ1641 እስከ 2460 የምትመጡት ሰኔ 10
4.ከ2461 እስከ 3280 የምትመጡት ሰኔ 11
5.3281 እስከ 4100 ያላችሁ ደግሞ ሰኔ 12 መጅሊስ ግቢ ትመጣላችሁ ቀድማችሁም አትገኙ ፤ ዘግይታችሁም አትምጡ ።
የቀጣዮቹን ሁጃጆች የጉዞ ሰነድ መረከቢያ ቀናቶች በተመሳሳይ መልኩ የምንገልፅላችሁ መሆኑን ተረድታችሁ ስልካችሁን ከፍታችሁ እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን ።
የጉዞ ሰነድ ለመረከብ በቀጠሮአችሁ ቀን የምትመጡ መንገደኞች ተጨማሪውን 57,500 ብር ክፍያ ባንክ አስገብታችሁ ደረሰኝ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል ።
ማሳሰቢያ :-
ለሐጅው ጉዞው ለሳዑዲ መንግስት የሚከፈል በቂ ዶላርም እስካሁን እንዳልተገኘ ህዝበ ሙስሊሙ ከወዲሁ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል ። ተቀዳሚ ሙፍቲና የዑለማ ምክር ቤት አባላት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው በዱዓ እናግዛቸው !!
ለሀጅ ጉዞ የተዘጋጁ እናትና አባቶቻችን እንዳይንገላቱና መረጃው እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ተባበሩን ።
ይህ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው ።
https://t.me/sufiyahlesuna
23 viewsMehdi Temam, 07:23