2022-12-22 17:37:00
ታላቁ የታሪኽ ሊቅ ተቁዩዲን አሕመድ ቢን ዐሊ'ይ አል መቅሪዚ'ይ (845 አ.ሂ.) በትንሽ ግዜ ውስጥ ስለተለየቻቸው ባለቤታቸው የህይወት ታሪኽ «ዱረሩ'ል ዑቁድ አልፈሪዳ'ህ - ፊ ተራጂሚ'ል አዕያኒ'ል ሙፊዳ'ህ» የተሰኘው ኪታባቸው ላይ ሲናገሩ :
ሰፍራ ቢንት ዑመር ቢን ዐብዱል ዐዚዝ ትባላለች ...
ኒካሕ ያሰርኩላት ሀሙስ 15 ሸዋል በ782 አ.ሂ. ነበር ...
በ786 አ.ሂ. እሁድ 19 ረቢዑል አወል የመጀመርያ ልጄን ወለደችልኝ ...
በ789 ደግሞ ሁለተኛ ልጄ ተወለደ ..
በ790 አ.ሂ. ታመመች .. በህልሜ አብራኝ እንደማትቆይ የሚያመላክት ነገር አየው በጣም ተረበሽኩ ጭንቀት ወረርኝ ። በዛው አመት ወደ አኼራ ተሻገረች ... አሉ
ከዛም እንዲህ አሉ
« ኢስቲግፋር በጣም አበዛላት ነበርና አንድ ግዜ አጋጣሚ በህልም አየኋት .. የከፈንኳት ግዜ በነበረው ሁኔታዋ እኔ ጋር ነበር የመጣችው ።
መሞቷን አስታወስኩና : «የሙሐመድ እናት .. የምልከው ነገር ግን ይደርስሻል ? » አልኳት (ኢስቲግፋሩን ማለቴ ነው ..)
እሷም አዎ «ሰዪዲ .. ስጦታህ በየቀኑ ይደርሰኛል ..»አለችና አለቀሰች .. «ታውቃለህ ሰዪዲ ውለታህን መመለስ እንደማልችል ..» አለች ።
«ምንም የለብሽም .. በቅርቡ እንገናኛለን » አልኳት..
አላህ ይማራትና ከእድሜ ትንሽነቷ ጋር በዲኗም እራሷን በመጠበቅም በታማኝነቷም በአቅለኛነቷም የዘመኗ ኸይረኛ ሴት ነበረች .. ከሷ ቡኃላም እሷን በመሰለ አልተካስኩም ...»
#mededulhabib
ዱረሩ'ል ዑቁድ አልፈሪዳ'ህ ፡ 2/79
https://t.me/mededulhabib
8 viewsMd, 14:37