Get Mystery Box with random crypto!

....ግጥሙን. ታሪክ ደጋሚ ሲመጣ እጨርሰዋለሁ ኢንሻ አሏህ ➺ታሪክ አልባ አይደለህም ቀና በል!! | شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

....ግጥሙን. ታሪክ ደጋሚ ሲመጣ እጨርሰዋለሁ ኢንሻ አሏህ

➺ታሪክ አልባ አይደለህም ቀና በል!!

በጠላቶችህ ድንፋታና ቀረርቶ አትረበሽ አንተው ራስህ ተዳክመህ እንጂ ዛሬ እነሱ ለ❺ ተከፋፍለው የያዟትን ሀገር ያለ አንዳች ኮሽታ ⓱አመት በጥበብ የመራ ጀግና ነበረህ ግን አንተው ተዳከምክና ጠላቶችህ ይፋጁብሀል።

➺...አሁንም ከነቃህ ግን ትደርሳለህ ተናበብ በእምነትህ ፅና ቀና በል!!

«አህመድ የሚባል ስም»

አስራ ሰባት አመት በፍትህ የመራ፡
ሞገሱ አስደማሚ ግርማው የሚያስፈራ፡
ጀግና የጀግና ዘር ተብሎ እሚጠራ፡
ስሙ አህመድ የሚባል ጨለማ አብሪ ኮከብ፡
በፍትህ የናደ የጠላትን መርከብ፡
-------------------------------------
ድንፋታሙን ሁሉ በጦር ያሸነፈ፡
የጠላትን ሴራ ፈጥኖ ያከሸፈ፡
በመሪነት ሚዛን ፕላን የነደፈ፡
ምን ስሙ ቢጠለሽ ክብሩ ያላደፈ፡
ለእምነቱ ታማኝ ሀቅን የገደፈ፡

«ሽንብራ-ኩሬ»ላይ አፄን ያደባዬ፡
አሞተ ቆፍጣና ጀግና ነው አባዬ፡
የአፄውን ስርዐት ገጥሞ የማረከ፡
በሀይማኖቱ ላይ ያልተፍረከረከ፡
ድል ያገኘ ጊዜ ያልሔደ ለበቀል፡
ሞራሉ ጢቅ ያለ የማይንቀለቀል፡
የኢስላም አንበሳ ቀድሞ የዘመነ፡
በእምነቱ ኩሩ በአንድ አሏህ ያመነ፡
በአፄው ስርዐት ላይ ዘንቦ የዳመነ፡

ይሔ ነው አባቴ ሁሌ ደስ የሚለኝ፡
አፄ ነኝ ለሚል በግ አብሪ ታሪክ አለኝ፡
ዘመናት ተሻግሮ ዛሬም የሚፈራ፡
ከታሪክ ድርሳን ላይ አብቦ ያፈራ፡
ለካሀዲያን ብዛት ለህዝብ ቆጠራ፡
ስልቱን አዘጋጅቶ አሏህን የጠራ፡
ጀግናው ኢማም አህመድ ተብሎ እሚጠራ፡

ዛሬም ነግሶ ያለ ይሔ ነው የኔ አባት፡
በሀረር በደቡብ በወሎ በዳባት፡
የካፊርን ደውላ ግራ የሚያጋባት፡
ከላይ ከታች ብሎ ፈጥኖ እሚያዋክባት፡
ስሙ አህመድ ይባላል እሱ ነው የኔ አባት፡

በፍቱን መዳኒት በሽታን የሚያክም፡
አዛኝና ትሁት ለሀገር የሚደክም፡
ያለ ምንም አድሎ ፍትህ ፈራጅ ዳኛ፡
የጦር ሜዳ አንበሳ ወታደር አርበኛ፡
የመሪነት ብቃት ያለው ጥበበኛ፡

ጣዖታትን ሁሉ አፍርሶ እሚያከስም፡
የሁሉ እኩል መሪ ጠላት የማይጎስም፡
ሀበሻን የመራ አህመድ የሚባል ስም፡

«ልጅ ሲተካ እጨርሰዋለሁ ኢንሻ አሏህ»

➺በኑረዲን አል አረቢ1444

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi