Get Mystery Box with random crypto!

ለሁላችንም ጥቆማ..... ቆም ብለን እንየውማ!! ❶]> ስማ ጀግናው ....ደ | شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

ለሁላችንም ጥቆማ.....
ቆም ብለን እንየውማ!!

<=============>

❶]> ስማ ጀግናው ....ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና አስተውል ተጠንቀቅ አትዝረክረክ ።
ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው በመረጃ ተመጠን ቆፍጠን በል ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ!!


❷]>ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።

❸]>ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣
ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣
ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ።

በየ ሔድክበት ፊትና የማያጣህ መርህ አልባ አቋመ-ተልባ አትሁን ወንድ ወንድ ሽተት ....
........ሰለፍይነት ማለት ወንድነት እንጅ ወዳገረድነት አይደለም።

ወላሒ ልብ በል

በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi