Get Mystery Box with random crypto!

➙ወላሒ ከልቤ አመሰግናቸዋለሁ «ክብር ይገባቸው» 'ባጭር ቀረን' ስንል፤ | شـبـاب السـلـــفــــيــــيــن

➙ወላሒ ከልቤ አመሰግናቸዋለሁ

«ክብር ይገባቸው»

"ባጭር ቀረን" ስንል፤
አይዟችሁ ብለው ተስፋ ላበደሩን፡
መንሀጅ አስተምረው፤
በቀደምቶች ፈለግ ቀርፀው ላሳመሩን፡
በሽርክ ስንጨልም፤
የተውሒድ ነፀብራቅ ለኩሰው ላበሩን፡
ከቢዲዐ አርቀው፤
በሱናውን መንገድ ላይ ለፍተው ላስከበሩን፡
---------------------------------------------
ፊታችንን ዐይተው፤
እንደተቸገርን ካይናችን ላወቁ፡
በአሏህ ስም ብለን፤
እስክንለምናቸው ቆመው ላልጠበቁ፡
ወቀሳውን ፈርተው፤
በየሸለቆው ዳር ስንቶች ሲደበቁ፡
ብዙ እየተባሉ፤
ሁሉን ነገር ችለው ለለውጥ ለበቁ፡
በተውሒድ ምክንያት፤
በጨቋኝ ስርዐት ግፍ ተፈርዶባቸው፡
እንባ እያፈሰሱ፤
ጀግንነት ላሳዩን ለሀይማኖታቸው፡
አቋም ላልቀየሩት፤
ለነዚህ አንበሶች ክብር ይገባቸው፡

የነብዩን ህይወት፤
የሶሀባን ታሪክ ለኛ ላስታወሱን፡
ምቀኞችን ንቀው፤
በሐቅ ላይ ፀንተው ፅናትን ላዋሱን፡
ታግለው ላታገሉን፤
ከጥመት አውጥተው ስኬት ላንተራሱን፡
የመንሀጅ መዐዛን፤
የሰለፍያን ወዝ ቀምሰው ላቀመሱን፡
ጥመት ላይ ስንተኛ፤
ኑ ብለው ወደኛ ሱናን ላስዳሰሱን፡
-----------------------------------------
በመንሀጅ ላይ ፀንተው፤
በአዳዲስ ፊትናወች ላልተቀያየሩ፡
ወደ ነፈሰበት፤
ጩኸት በበዛበት ላልሆኑ እንዳየሩ፡
ጠላት ሲዘምትበት፤
ዲናቸው ሲደፈር ቀድመው ለሚነሱ፡
በደዕዋ መንገድ ላይ፤
አይዟችሁ ለሚሉን ፊት ሆነው እነሱ፡
ሌት ከቀን ሳያርፉ፤
ለሚገሰግሱ ታሪክን ለመድገም፡
ውድቀትም ሲመጣ፤
ፈጥነው የሚነሱ ቶሎ ለማገገም፡

ለእምነት ዋጋ ከፍለው፤
በአሏህ እገዛ ዘወትር ወደ ፊት ለሚገሰግሱ፡
ለአንዷ ሐቅ ሲባል፤
ወድቀው ለማይጥሉ ነግሰው ለሚያነግሱ፡
ነውራችንን ዐይተው፤
በማራኪ ተግሳፅ ስህተት ለሚያፈርሱ፡
ነገር ከማራገብ፤
ችግርም ሲፈጠር ቶሎ ለሚደርሱ፡
ክብር ይገባቸው፤
አርቆ አስተዋዮች ሰው ናቸው እነርሱ፡

ለነዚህ ኮከቦች ይገባቸው ክብር፡
የአሏህን አደራ ያልቀየሩት በብር፡
በዱንያ ቆይታ ኢማንን ጨምረው፡
ሐቅ ላይ ለሞቱት በሐቅ ላይ ኖረው፡
በትንሹም ቢሆን ለቀራንባቸው፡
ለነዚህ ፅኑወች ክብር ይገባቸው፡

ውሸት በመሰከክ ሰው ለሚያጫርሱ፡
የጠራውን መንገድ ለሚያደፈርሱ፡
የኢስላምን ጠላት የሚገረስሱ፡
ህይወትን ለመክፈል ፈፅሞ እማይሳሱ፡
ለሒዝብያ መንጋ ለሽርክ ጠበቆች፡
ለኢስላም ነቀርሳ ለእውር ሙናፊቆች፡
የነዚህ መዳኒት ናቸው የኔ ሊቆች፡

በበሳል አካሔድ፤
ላባ ላረጉልን የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን፤
በሚገርም ጥበብ ተጫውተው ላከሙን፡
በቸከ ዘመን ላይ...
ስጋ-ለበስ ትንግርት ሆነው ላስደመሙን፡
የአርሹ ባለቤት፤
እውቀት ከልቀት ጋር የሰጣቸው አቅሙን፡
በቁርዐን በሀዲስ፤
በሰለፎች ፈለግ የነብያት ወራሽ፡
አስደማሚ ዶክተር፤
በመረጃ ውበት ሁሌ ፈጥነው ደራሽ፡
ሰለፍያን እንዳውቅ፤
ከአሏህ በመቀጠል«ጉልህ»ነው ድርሻቸው፡
የኢስላም ሙህራን፤
ሊቀ-ጠበብቶቹ ክብር ይገባቸው፡
።።።።።።።።።።።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በኑረዲን አል-አረቢ 1444

https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi