Get Mystery Box with random crypto!

መቃብር ህልም ራዕዩን ሲያረግዝ እየጨነገፈ፣ አበባ እምቡጥ ትልሙ እየተቀጠፈ ፣ ውትርትር ኣላማ | ኑ እናንብብ

መቃብር

ህልም ራዕዩን ሲያረግዝ እየጨነገፈ፣
አበባ እምቡጥ ትልሙ እየተቀጠፈ ፣
ውትርትር ኣላማው ከሽሉ እያለፈ፣
ራሱን እያነቀ ምኞቱን ሳይረካ፣
የሰው ልጅ የራሱ ፣ መቃብር ነው ለካ፡፡

ይስማዕከ ወርቁ