Get Mystery Box with random crypto!

ግብረ ቀንድ አውጣ ወጣ ከዛጎሉ፤ ገባ ከዛጎሉ፤ ሁሉም ቀንዳውጣ ነው፤ ዛጎል ነው ባካሉ፡ ብቅ ጥ | ኑ እናንብብ

ግብረ ቀንድ አውጣ

ወጣ ከዛጎሉ፤
ገባ ከዛጎሉ፤
ሁሉም ቀንዳውጣ ነው፤ ዛጎል ነው ባካሉ፡
ብቅ ጥልቅ ይላል ፣ የቀንዳውጣ አመሉ፤
ፍርሃቱና ጉራው ፣ አብረው ይጠልቃሉ፤
ደስታና መከራው ፣ እኩል ይዘልቃሉ፡፡
ወጣ ከዛጎሉ፡
ገባ ከዛጎሉ፡
የቀንዳውጣ ኑሮ፣ የቀንድ አውጣ አመሉ፤
ፀጥ ሲል መመዥረጥ፣ ኮሽ ሲል ከሸሉ፡፡

ይስማዕከ ወርቁ

@NuEnanbib