Get Mystery Box with random crypto!

# የሟቹ_ኑዛዜ ፡ የምንዱቡን ትንፋሽ ፥ ሞት በግፍ ቢነጥቅም ሟች ቀኑን ያጣ ቀን ፥ ገዳዩ አይታወ | ኑ እናንብብ

# የሟቹ_ኑዛዜ

የምንዱቡን ትንፋሽ ፥ ሞት በግፍ ቢነጥቅም
ሟች ቀኑን ያጣ ቀን ፥ ገዳዩ አይታወቅም ፤

አፋኙ ጣረ ሞት
አንደበቱን ይዞ ፥ ነፍሱን የነጠቀው
በምን ይናገራል ፥ ገዳዩንስ ቢያውቀው ፤

ብቻ ጀምበር ዕድሜው
በመአልቱ ጽልመት ፥ ማልዶ የታገተ
እስከ ሽበት ደርሶም ፥ አፍ ሳይፈታ ሞተ ፤

ምናልባት ምናልባት ፥ እንደ መልካም ዕጣ
ድንገት በለስ ቀንቶት ፥ የኔም ቀን ከመጣ
ሚጠይቁም ካሉ
ያሟሟቱ ነገር ፥ እንዲህ ነበር በሉ
.
''ሲለው መሶብ መስሎ ፥ ጎድሎ እንዳጎደለው
ሲሻውም ቀን ሆኖ ፥ ከፍቶ እንደበደለው
እድሜውን በልቶ ነው ፥ ዘመን የገደለው"
------------------------//-----------------------

( ኢዛና መስፍን Ezana Mesfin )
("የዜማ ናፍቆት" የግጥም ስብስብ፣2010 ዓም)

@NuEnanbib