Get Mystery Box with random crypto!

ከአሰልቺው ሰማይ ስር ( Abi.G ) ሰባኪው እንዳለው ፣ የሰው ትርፉ ድካም የእድሜያችን ርዝመት | ኑ እናንብብ

ከአሰልቺው ሰማይ ስር
( Abi.G )
ሰባኪው እንዳለው ፣ የሰው ትርፉ ድካም
የእድሜያችን ርዝመት ፣ በእርምጃ አይለካም
ቢለካስ ምን ሊኮን?
ምኞቱ ሳይሞላ ፣ የሞላ ወንዝ ወስዶት
ባጭሩ የቀረ ፣ ህልሙን ውሀ በልቶት
ወይ ከናቱ ማህፀን ፣ ማለም ሳይችል ገና
በውርጃ መኪና
መገጨት የሆነ ፣ የህይወት ፍፃሜው
ሳይራመድ ሟቹ ፣ ስንት ይሆናል እድሜው?
እግዞ!
የተራመደውም ፣ ተጉዞ ተጉዞ
መንገድ መርጦ ኑሮ ፣ ፍጥረት ሁሉ እንዳሻው
አለመጓዝ ሲሆን ፣ ጉዞው መጨረሻው
ስለምን ይጓዛል ?
ብልህ ለምን ለፍቶ ፣ ከንቱነት ይገዛል ?
እንጃ!
ግን በህይወት ፍርጃ
ጠንቋይ ቢጠነቁል ፣ የህይወትን ፍጥም
መሞቻውን አውቆ ፣ ከሞቱ አያመልጥም
ህይወት ርእስ ናት ፣ ሞት ለሚለው ግጥም!
ይሁና!
ይሄን ያሳብ መና
ተፈጥሮም አታጣም ፣ የሚችል ሊያፅናና
እድል እጣ ፈንታ
ጎኔን እየመታ
ወደ ምንምነት ፣ ቢችልም ሊያደርሰኝ
ምንምነት ራሱ
ምንም ነው 'ሚሆነው ፣ ከንፈርሽ ሲደርሰኝ!!
..