እንኳን አደረሰሽ (ለኢትዮጵያ ) ከፀሀይ በታች፥ አዲስ ነገር ባይኖርም መልካም አዲስ አመት፥ ማለት አናቆምም። ዘመን ባይለወጥ፥ አዲስ ቀን ባይወጣ ከድጥ ወደ ማጡ፥ ቢሆንም የኛ እጣ ። እንኳን አደረሰሽ ማለት አላቆምም በሚመሩሽ እንጂ፥ እኔ ባንቺ አላዝንም ። እንኳን አደረሰሽ እንደ አምና ፥ ካች አምና ፀሀይም ባትኖር፥ ሌሊትሽ ባይነጋ መላው መሬትሽም፥ ቢርስ በሰው እንባ ዘመን ቢተካካም፥ አዲስ ቀን ባይወጣ ። በእንጥፍጣፊ ተስፋ፥ ከልቤ በቀረው እንኳን አደረሰሽ ፥ ዛሬም እልሻለው። ኬቲኤል 1.7K views15:16