Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ነገሮች ብዙ ያስገርማሉ። ለምሳሌ፥ አንዳንድ ትግራዊያን የሃይል ሚዛኑ ወደ መንግስት ሲያ | ኑ እናንብብ

አንዳንድ ነገሮች ብዙ ያስገርማሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ትግራዊያን የሃይል ሚዛኑ ወደ መንግስት ሲያጋድል ሰላም ይሰብካሉ። ወደ ህወሃት ሲሆን ደግሞ ጦርነት ጎሳሚ ይሆናሉ። ከዛ ደግሞ አልተረዳችሁንም ይላሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ የአማራ ሰዎች 'ትግሬዎች ህወሃትን ማስወገድ አለባቸው። አይጠቅማቸውም ገለመሌ' ይላሉ። እውነታው ግን ለአማራ ያልጠቀመውን ብአዴንን ማስወገድ ያልቻሉ መሆናቸው ነው።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ የጉራጌ ሰዎች 'የጉራጌ እጣ ፈንታ በጉራጌ ብቻ ይወሰን። እናውቅላችኋለን አትበሉን' ይላሉ። የወለኔን እና መሰል የማንነት ጥያቄዎችን ግን ይደፈጥጣሉ። 'በኛ ጉዳይ አትወስኑ' ባሉበት አንደበት በወለኔ ጉዳይ ፍርድ ይሰጣሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጆች የ19ኛውን ክፍለ ዘመን የሚኒሊክ ዘመቻ ያነሱና 'ኦሮሞ ተጨቁኗል፥ ኢትዮጵያ በድላናለች' ወዘተ ይላሉ። ነገር ግን በ16ኛው ክፍለ ዘመን በኦሮሞ መስፋፋት ዘመን የተፈጠረውን ነገር ማውራት አይፈልጉም።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ጴንጤዎች 'ፀበል አያድንም' ይላሉ ነገር ግን ከበሽታቸው ለመፈወስ ከእዩ ጩፋ ዘይት በ1ሺ ብር ይገዛሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ሙስሊሞች 'ሰሜኖቹ ክርስቲያናዊ መንግስት ለማቋቋም ስለሞከሩ ሊወገዙ ይገባል' ይላሉ። በተቃራኒው በጅማ እና በሃረር ተቋቁሞ የነበረውን እስላማዊ መንግስት ያሞግሳሉ። (ለኔ ሲሆን መብት ላንተ ሲሆን ጥፋት የሚል ሎጂክ

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ኦርቶዶክሶች 'ጴንጤዎች በመዝሙር ይጨፍራሉ' ይላሉ። ነገር ግን በንግስ ቀን ይሰክራሉ፥ ይጨፍራሉ፥ ይዘሙታሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ ኤቲስቶች 'አለምን እግዚአብሔር ፈጠረ' የሚለው ተረት ነው ይላሉ። በተቃራኒው 'አለም ከአንዲት ቅንጣት ተፈጠረች' የሚለውን ተረት ያምናሉ።

ለምሳሌ፥ አንዳንድ አማኞች 'ኹለት የፍልስፍና መፅሐፍ አንብባችሁ አምላክ የለም አትበሉ' ይላሉ። በተቃራኒው አንዱን የሃይማኖታቸውን መፅሐፍ በቅጡ ሳያነቡ አምላክ አለ ማለታቸውን ይረሳሉ


@Tfanos