Get Mystery Box with random crypto!

ግራ ዘመን (ተስፋኣብ ተሾመ) ላይ ላዩን ሲታይ የኛ ዘመን ጥሩ ይመስላል። በትክክል ግን ግራ አጋ | ኑ እናንብብ

ግራ ዘመን
(ተስፋኣብ ተሾመ)

ላይ ላዩን ሲታይ የኛ ዘመን ጥሩ ይመስላል። በትክክል ግን ግራ አጋቢ  ዘመን ነው። የማይጨበጥ ዘመን!

ዛሬ ላይ አላስፈላጊ መተራመስ ውስጥ ነን፥ እርጋታ የለም፥ የጋራ እሴት የለም።  ግለሰባዊነት ማበቡ ያልበቁ ግለሰቦች እንዳሻቸው እንዲፈነጩ አድርጓል። ያልተማሩቱ መምህራን የሚሆኑበትን እድል አግኝተዋል። ራሱን ለመግዛት ያልታደለ የመንጋው አውራ ለመሆን በሚያደርገው ትግል የተነሳ መንጋው ታምሳል። እውነተኛ ተመሪ ልከኛ መሪ የለም። ልክ ያልሆነ ቦታ መቀያየር ተፈጥሯል

በመረጃ ጎርፍ ብንጥለቀለቅም እውቀት አልሆነንም። ጥራዝ ነጠቅ አደረገን እንጂ!
በየሴኮንዱ ከሚለቀቀው መረጃ መኻከል እውነት የሆነውን የመለያ ጥበብ አላዳበርንም። ትርምስ ብቻ።

ዘመናችን ግራ አጋቢ ነው። በግራ አጋቢ ዘመን በግራ መጋባት እየተራመስን ነው። ትርምስ ብቻ!

ዘመን መዋጀት ይኹንልን!


https://t.me/Tfanos