Get Mystery Box with random crypto!

ለዚህች ሀገር እዘኑላት የንባብ ቅምሻ ደራሲ -ካህሊል ጂብራ መፅሀፍ -የጠቢባን መንገድ በአንዱ | ኑ እናንብብ

ለዚህች ሀገር እዘኑላት
የንባብ ቅምሻ

ደራሲ -ካህሊል ጂብራ
መፅሀፍ -የጠቢባን መንገድ

በአንዱ ቀን ጠዋት ደቀ - መዛሙርቱ ነብዩን ከበው ተቀመጡ፡፡ በአይኖቹ ላይ ርቀቶችና ትዝታዎች ነበሩበት። ሀፊዝ የሚባለው ደቀ - መዝሙሩም እንዲህ አለው፦ «መምህር ሆይ! ስለ ኦርፋሴስ ከተማ ንገረን፡፡ በእነዚያ አስራ ሁለት አመታት ስላረፍክበት ሀገርም ንገረን፡፡»

አልሙስጠፋ ዝም አለ። ወደ ጋራዎቹና ወደ አድማሱም ፊቱን አዙሮ ተመለከተ። በፀጥታው ውስጥ ጦርነት ነበር!!
ከዚያም አላቸው
"ወዳጆቼ ሆይ በእምነቶችና በባዶ ሀይማኖቶች ለተሞላች ሀገር እዘኑላት...

"በጥባጮችን እንደ ጀግና በእልልታ ለምትቀበል ገዳዮችን እንደ ለጋስ ለምታሞካሽ ሀገር እዘኑላት...

"ያልሸመነውን ጨርቅ ለሚለብስ፤ያልጋገረውን ዳቦ ለሚመገብና ያልጠመቀውን ወይን ለሚጠጣ ሰው እዘኑለት።


"ፍቅርን በህልሟ ለምትንቅ ሰትነቃ ግን ለምንትበረከክለት ሀገር እዘኑላት...

"ወደ መቃብር ሲወርድ ካልሆነ በስተቀር ድምፁ ለማይሰማ፤ እንዲሁም አንገቱ በሰይፍ እና በግንዲላ መካከል ሲጋደም ካልሆነ በስተቀር ለማያምፅ ህዝብ እዘኑለት...

"መሪው ቀበሮ ፣ፈላሰፋው ቀጣፊ ፣ጥበቡም መኮረጅና መለጣጠፍ ለሆነ ህዝብ እዘኑለት...

"አዲስ ገዢዎቹን ጥሩምባ እየነፋ ለሚቀበልና እንደገና ጡሩምባ እየነፋ ሌላውን ለመቀበል ሲል ብቻ በንቀት ጩኸት ለሚያሰናብታቸው ህዝብ እዘኑለት....

"አዋቂዎቹዋ እድሜ በመግፋት ዲዳ ለሆኑባትና ልጆቹዋ ገና ከህፃን አልጋ ላይ ላልተነሱላት ሀገር እዘኑላት...

"ግዛቷ ለተበጣጠሰና እያንዳንዱ ብጥስጣሽ ራሱን እንደ አንድ ሀገር ለሚቆጥርባት ሀገር እዘኑላት...

@Zephilosophy
@Zephilosophy