Get Mystery Box with random crypto!

ሕይወት ምንድን ነው? ምንጭ ፦ ዘላለማዊነት (ራምፓ) ትርጉም ፦ ሱራፌል ግርማ በእውነቱ፣ ያለ | ኑ እናንብብ

ሕይወት ምንድን ነው?

ምንጭ ፦ ዘላለማዊነት (ራምፓ)
ትርጉም ፦ ሱራፌል ግርማ

በእውነቱ፣ ያለው ነገር በሙሉ “ሕይወት” ነው፡፡ “ምውት” ብለን የምንጠራው ፍጡር እንኳ ሕያው ነው፡፡ “ምውት” ብለን እንድንጠራው ያደረገን ተለምዷዊ የሕይወት ቅርፁ ማብቃቱ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ያ “ሕይወት” ሲያበቃ አዲስ ዓይነት ሕይወት ይፈጠራል፡፡ የመፍረስ ኺደት በራሱ ሕይወት ይፈጥራል!

ያለ ነገር በሙሉ ይነዝራል፡፡ ሞለኪውሎችን የያዘ ነገር በሙሉ በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ላይ ነው። በአቶም፣ በኒዩትሮን፣ በፕሮቶን ፋንታ “ሞለኪውል” የምንጠቀመው ይሄ ትምህርት የኬሚስትሪ አሊያም የፊዚክስ ሳይሆን የዲበ-አካል በመሆኑ ነው፡፡ በማይጠቅሙ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ፋንታ አጠቃላይ ምስሉን ለመፍጠር ነው የምንሞክረው፡፡

ምናልባት በመጀመሪያ ስለ ሞለኪውሎችና አተሞች ጥቂት ማለት ሳይኖርብን አይቀርም፡፡ ሞለኪውሎች በኤሌክትሮን ማይክሮስኮፕ ብቻ ሊታዩ የሚችሉ ቅንጣቶች ናቸው። በመዝገበ ቃላት ፍቺው መሠረት ሞለኪውል፣ የአንድ ነገርን ባሕሪያት ይዞ ለብቻው ሕላዌ ሊኖረው የሚችል ቅንጣት ነው። ሞለኪውሎች በጣም ደቃቅ ቢሆኑም ከእነርሱ ባነሱ “አቶም” በሚባሉ ቅንጣቶት የተዋቀሩ ናቸው፡፡

አቶም በሥርዓተ ፀሐይ ሊመሰል ይችላል፡፡ የአቶሙ አስኳል ፀሐይን ይወክላል። በዚህ “ዐሐይ” ዙሪያ ፕላኔቶች ፀሐይን እንደሚዞሯት ኤሌክትሮኖች ይዞራሉ፡፡ እንደ ሥርዓተ-ፀሐይ ሁሉ የአቶም አብዛኛው ክፍል ባዶ ሥፍራ ነው፡፡

እያንዳንዱ ነገር በኒውክለሱ ውስጥ የሚኖረው የኤሌክትሮኖች ቁጥር የተለያየ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ዩራኒያም ዘጠና ሁለት ኤሌክትሮኖች አሉት። ካርቦን ደግሞ ስድስት ብቻ ነው ያለው፡፡ ለኒውክለሱ የሚቀርቡት የካርበን ኤሌክትሮኖች ሁለት ሲሆኑ አራቱ ደግሞ በርቀት የሚዞሩ ናቸው። ነገር ግን ዋና ጉዳያችን ሞለኪውሎች በመሆናቸው ስለአቶሞች በሰፊው አንነጋገርም።

ሰው በፍጥነት የሚሽከረከሩ ሞለኪውሎች ስብስብ ነው፡፡ ሰው ጠጣር ይመስላል፤ ሥጋችንንና አጥንታችንን በጣታችን መሠርሠር አንችልም፡፡ ሆኖም ግን ይሄ ጠጣርነት የሰው ፍጡር በመሆናችን ለማመን የተገደድንበት ምትሀት ነው፡፡ በጣም ደቃቅ የሆነ ፍጡርን፣ ከሰው አካል በርቀት ሆኖ ሊመለከተው የሚችልን አስቡ ያ ፍጡር የሚያጥበረብሩ ፀሐያትን፣ በጣም ርቀው ያሉ ከዋክብትን ይመለከታል፡፡ በጣም ለስላሳ በሆኑ የሰውነት አካላት ላይ የሚገኙ ሞለኪውሎች የተበታተኑ ናቸው። እንደ አጥንት ባሉ ጠንካራ የሰውነት አካላት ላይ የሚገኙ ሞለኪውሎች ደግሞ በጣም ጥቅጥቅ ያሉ፤ እርስ በርሳቸው በጥብቅ የተሳሰሩ በመሆናቸው የከዋክብት ስብስብን ይመስላሉ፡፡

ጨረቃና ከዋክብት ብሩህ ባደረጉት ምሽት ከተራራ ጫፍ ላይ ቆማችሁ በምናባችሁ ይታያችሁ፡፡ ብቻህን አይደለህም ፤ ወደ ሰማይ ከሚፈነጠቁት የከተማ የኤሌክትሪክ ብርሃናት ባሻገር ካረበበው እርጥበት የተነሣ ሰማየ - ሰማያት ደብዝዘው ይታያሉ፡፡ (ለዚህ ነው የሕዋ ምርምር ጣቢያዎች ከከተማ ርቀው በሚገኙ ሥፍራዎች የሚገነቡት) አንተ በራስህ ተራራ ጫፍ ላይ ነህ። ከአንተ በላይ ክዋክብቱ ብሩህ ብርሃን ይፈነጥቃሉ፡፡ ማለቂያ በሌለው ሰልፍ ከፊትህ ሲሽከረከሩ እነርሱን አተኩረህ ትመለከታለህ፡፡ ታላላቅ የከዋክብት ስብስቦች ከፊትህ ተዘርግተዋል። ከዋክብቱ የምሽቱን ጨለማ አስጊጠውታል፡፡ ከሰማየ ሰማያት ባሻገር “ሚልኪ ዌይ” የተባለው የከዋክብት ስብስብ ሰፊና በጭጋግ የተሸፈነ ዱካ መስሎ ይታያል፡፡ ከዋክብት፣ ዓለማት፣ ፕላኔቶች፣ ሞለኪውሎች:: ልክ እንደዚሁ ነው “ማይክሮስኮፒክ” የሆነው ደቃቅ ፍጡር አንተንም የሚመለከትህ!

በሰማየ - ሰማያት የሚገኙት ከዋክብት በመካከላቸው የማይታመን ክፍተት ያለ የብርሃን ነጥቦች ሆነው ነው የሚታዩት፡፡ በቢሊየን፣ በትሪሊየን የሚቆጠሩ ከዋክብት ቢኖሩም በመካከላቸው ካለው ክፍተት የተነሣ ጥቂት መስለው ነው የሚታዩት፡፡ የጠፈር መረብ ቢኖር በከዋክብቱ መካከል አንዱንም ባለመንካት ለማለፍ ይችላል፡፡ በከዋክብቱ፤ በሞለኪውሎች መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ እንደምትችል በምናብህ ስታስብ ምን ልታይ ትችላለህ? ከርቀት አንተን እየተመለከተህ ያለው ደቃቅ ፍጡርም ይሄን እያሰበ ይሆን ያ ፍጡር የሚያየው ሞለኪውሎች በሙሉ “እኛ” መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን፡፡

እንግዲያውስ በሰማየ-ሰማያት የሚገኙ ከዋክብት የመጨረሻ ቅርፅ ምን ዓይነት ነው? እያንዳንዱ ሰው በራሱ ፍጥረተ ዓለም ነው፡፡ በዚህ ፍጥረተ-ዓለም ውስጥ ሞለኪውሎች በማዕላዊ ፀሐይ ዙሪያ ይሽከረከራሉ፡፡ እያንዳንዱ ዐለት፣ ቀምበጥ ወይም የውኃ ጠብታ ማለቂያ በሌለው ሞለኪውሎች የተዋቀረ ነው፡፡

ሰው፣ በእንቅስቃሴ ላይ ከሚገኙ ሞለኪውሎች የተሠራ ነው፡፡ እንቅስቃሴው የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፣ በላየ ራስ ከሚያመነጨው “ኤሌክትሪክ” ጋር ሲዋኃድ ስሜት ያለው ሕይወት ይሰጣል። በምድር ዋልታዎች ዙሪያ ያለው መግነጢሳዊ ሞገድ ለባለ ሕብረ-ቀለማቱ አውሮራ ቦሪያሊስ መንስኤ ነው፡፡ በሁሉም ፕላኔቶችና ሞለኪውሎች ዙሪያ መግነጢሳዊ ሞገዶች በቅርብ ከሚገኙ ዓለማትና ሞለኪውሎች ከሚመነጩ መግነጢሳዊ ሞገዶች ጋር መስተጋብር ይፈጥራሉ፡፡ “አንድም ሰው ለራሱ፧ ለብቻው ዓለም አይደለም!” ያለ ሌሎች ዓለማት ወይም ሞለኪውሎች አንድም ዓለም ወይም ሞለኪውል ሕላዌ ሊኖረው አይችልም፡፡ እያንዳንዱ ፍጡር፣ ዓለም ወይም ሞለኪውል በሌሎች ፍጡራን ዓለማት ወይም ሞለኪውሎች መኖር ነው
ሕላዌው የሚወሰነው።

የሞለኪውል ስብስቦች እንደ ከዋክብት ስብስቦች በሕዋ ላይ የሚዋልሉ የተለያየ የጥግግት ደረጃ ያላቸው መሆኑ ሊታወቅ፤ ሊደነቅ ይገባል፡፡ በፍጥረተ ዓለም የተወሰነው ክፍል በጣም ጥቂት ከዋክብት ወይም ፕላኔቶች ሲኖሩ እንደ ሚልኪዌይ ባለው ጋላክሲ ውስጥ ደግሞ ፕላኔቶች ተጠጋግተው ይገኛሉ፡፡

በተመሳሳይ መልከ ዐለት በጣም ጥብቅ የሆነ የሞለኪውሎች ስብስብን ወይም ጋላክሲን ሊወክል ይችላል፡፡ የአየር የሞለኪውሎች ይዘት የሳሳ ነው፡፡ በርግጥም አየር በውስጣችን፣ በሳንባችን በማለፍ ወደ ደም ሥሮቻችን ያመራል። ከአየር ባሻገር፣ የሐይድሮጅን ሞለኪውሎች ተበታትነው የሚገኙበት ሥራ አለ፡፡ ወና፣ ሰዎች እንደሚያስቡት ባዶ፥ ምንም የሌለበት ሳይሆን የሐይድሮጅን ሞለኪውሎች . . . ከሐይድሮጅን ሞለኪውሎች የተፈጠሩ ዓለማት፣ ከዋክብትና ፕላኔቶች የተሰባሰቡበት ነው፡፡

አንድ ነገር ጥብቅ ከሆኑ የሞለኪውል ስብስቦች የተዋቀረ ከሆነ ሌላ አካል በእርሱ ውስጥ ለማለፍ እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ከተበታተኑ
ሞለኪውሎች የተዋቀረውና “መንፈስ” ተብሎ የሚጠራው በግድግዳ ውስጥ እንኳ ሲሆን አልፎ ለመሄድ ይችላል፡፡ የደንጊያ ግድግዳን አስበው፧ በአየር ላይ እንደተንጠለጠለ የአቧራ ደመና ያሉ ሞለኪውሎች ጥብቅ ስብስብ ነው፡፡ የቱንም ያህል የማይቻል ቢመስልም በእያንዳንዱ ሞለኪውል መካከል ክፍተት አለ (ልክ በከዋክብት መካከል እንዳለው) ስለሆነም፣ ከዚያ አካል ሞለኪውሎች ይበልጥ በተበታተነ ሞለኪውሎች የተዋቀረ ደቃቅ ፍጥረት በጥብቅ ሞለኪውሎች በተዋቀረው የደንጊያ ግድግዳ ውስጥ እንኳ ምንም ሳይነካካ ለማለፍ ይችላል፡፡

ይህም፣ “መንፈስ” በተዘጋ ክፍል ውስጥ እንዴት ሊከሰት እንደሚችል እና በግድግዳ ውስጥ ሊያልፍ እንደሚችል እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ እያንዳንዱ ነገር አንፃራዊ ነው ፤ ለአንተ ጥብቅና ጠጣር መስሎ የሚታይህ ግድግዳ ለመንፈስ ወይም ለከዋክብቱ ፍጥረት ክፍል ሊሆን ይችላል፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy