Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ( አጭር ልቦለድ) (በእውቀቱ ስዩም) ጢም ማቀምቀም በጀመርኩበት ዘመን በከተማችን አንድ | ኑ እናንብብ

ሰው
( አጭር ልቦለድ)
(በእውቀቱ ስዩም)
ጢም ማቀምቀም በጀመርኩበት ዘመን በከተማችን አንድ ተአምረኛ ባህታዊ ብቅ አለ፤ 'ጥቁር ኢየሱስ ብለው ሊጠሩት የደፈሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ ፤ ባህታዊው እውር ያበራል፤ ጎባጣ ያቀናል፤ ባንድ ጊዜ የከተማው ሆስፒታሎች ሁሉ ባዶ ሆኑ፤ የሆነ ጊዜ ላይ እንዲያውም ሙት ማስነሳት ሁሉ ጀምሮ ነበር፤ የከተማችን አስተዳዳሪ ግን “ ለተነሺዎች ማቋቋሚያ የሚሆን በጀት የለንም ብሎ ከለከለው፤

ባህታዊው ባንድ ወቅት ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ወልደ ሰንበት ከተባለ የከተማው ነዋሪ ጋራ ተገናኘ፤ ወልደ ሰንበት በራዛ ዘመቻ ጊዜ ፈንጅ ብልቱን ቆርጦበታል፤ በጥሮታ ከተገለለ በሁዋላ ‘መራባት የተሳናቸው ወንዶች ማህበር’ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያገልግላል፤

ወልደሰንበት ባህታዊውን ሲያየው “ አባት ሆይ፥ አገሬን አገሬን ብየ ስዋትት ዘሬን ሳልተካ ላልፍ ነው፤ ፈውሰኝ “ ሲል እግሩ ላይ ወድቆ ተማጠነው።

ባህታዊው ወደ ሰማይ አንጋጦ ትንሽ ከጸልዩ ሲያበቃ ወልሰንበትን አስወልቆ ጉያውን ዳበስ አደረገው ፥ መቸም አታምኑኝም ፤ ግን ሀቅ ከከመመስከር አልታገድም፤ የሰውየው ጉምድ ብልት ወዲያውኑ አቆጠቆጠ። ተአምረኛውን ሰውየ ያጀቡ ወንዶች አፋቸውን በጋቢያቸውና በኮሌታቸው ጫኑ !የሴቶች እልልታማ ፤እስከመተማ ፤ ተሰማ፥

ባህታዊው ይህንን ተአምራዊ የብልት- ተከላ ፈጽሞ ትንሽ አለፍ እንዳለ ወልደ ሰንበት እያለከለከ ደረሰበትና እግሩ ስር ተደፋ፤

“ አሁን ደግሞ ምን ፈለግህ?” አለው ባህታዊ፥ በታከተ ሰው ድምጽ ፥
ወልዴ እንዲህ ሲል መለሰ፥

“አባት ሆይ ! በነካ እጅህ ትንሽ ተለቅ ልታረግልኝ ትችላለህ?”