Get Mystery Box with random crypto!

የትንፋሽ ሜዲቴሽን ሁለት አይነት የሙሉ እዕምሮ አተነፋፈስ ሜዲቴሽን አለ።አንዱ በቀን ውስጥ የተ | ኑ እናንብብ

የትንፋሽ ሜዲቴሽን

ሁለት አይነት የሙሉ እዕምሮ አተነፋፈስ ሜዲቴሽን አለ።አንዱ በቀን ውስጥ የተወሰነ ጊዜ መድበን ሲሆን ፤ሌላ ስራችንን ሁሉ አቁመን የምናደርገው ሲሆን ፤ተቀምጠን ወይም አልጋ ላይ ጋለል ብለን ወይም ራስችንን እንደተመቸን አስቀምጠን ሙሉ በሙሉ ትኩረታችን ትንፋሻችን መግባትና መውጣት ላይ ይሆናል ማለት ነው ።

ይሄን በየጊዜው አዘውትርን ያለማቁዋረጥ የምናድረግ ከሆነ በዚህ በራስችን ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ማለት ነው።ይህ እንግዲህ አዕምሮችን ከውስጥ ራሱ ከሚፈጥረው ችግርም ሆን ከውጭው አለም ከሚደርስብን ግፊት ራሳችንን መከላከል እንችላለን ማለት ነው ።

አዕምሮአችን ራሱ ከሚፍጥረው መጥፎ ሃስብም ሆነ በኑሮ ከሚመጣብን እንቅፋት ይልቅ ትኩረታችን ወደ ትንፋሽችን ሲሆን አዕምሮአችን የበለጠ ጤናምና ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ችግሮችን የመቋቋም ችሎታው ይዳብራል።

ሁለተኛው ደግሞ በቀን ውስጥ በየትኛውም ጊዜ ወይም ቀኑን ሙሉ በምናደርገው እንቅስቃሴ ትኩረታችንን ወደ ትንፋሻችንም ሆነ ወደ ሰውነታችን እንቅስቃሴ በማድረግ ነው ።

ለምሳሌ ስንራመድ ስንቀመጥም ሆነ በተገኘው ሁሉ አጋጣሚ ትኩረታችንን ትንፋሻችን ላይ ማድረግ ስንጀምር እርጋታን፤ነገሮችን በጥንቃቄና በሰከነ መንፈስ ማየት እንጀምራለን።

የትንፋሽ ሜዲቴሽን መለማመጃ

1.ተመቻችተህ በጀርባህ መንጋለል ወይም በደንብ ተስተካከለህ
ትቀመጣለህ ትከሻህን ዘና ታደርገዋለህ

2 .አይንህን ትጨፍናለህ ይህም ተስማሚ ሆኖ ካገኘህው ነው።

3 ትኩረትህን ሁሉ ወደ ሆድህ አምጣው፤ወደ ውስጥ ስትተነፍስ የሆድህን ወደ ላይ መውጣት ወይም ወደ ጎን ሰፋ ማለት እንዲሁም
ወደ ውጭ ስትተነፍስ የሆድህን ወደ ታች ማለት አስተውለው።

4 .ትኩረትህን ወደ ትንፋሽህ ጨምር፤ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ውጭ የምትተንፍስበትን ጊዚያት ሁሉ ከሱ ጋር አብረህ ሁን።በሃሳብ አንተ የትንፋሽህን ሞገድ የምትነዳው አድርገህ ገምትና አብረህ ወደታች ወደላይ በል።

5. አዕምሮህ ትንፋሽህን ዘንግቶ ወደ ለመደው ስራው መሄዱን ስትገነዘብ በእርጋታ መልስህ ወደ ትንፋሽህ አምጣው።እንደገና ወደ ውስጥና ውጭ ትንፋሽህ ትኩረትህ ይሁን።


6 .አንድ ሺህ ጊዜ አዕምሮህ ትንፋሽህን እየዘነጋ ወደ ሌላ ሃሳብ ሲዘል ያንተ ስራ በእርጋታ ወደ ትንፋሽህ እንዲመለስ ማድረግ ነው።

7. ይህን ሜዲቴሽን በቀን ለ 15 ደቂቃ ምንም ሳትደርግ ትንፋሽህ ላይ ብቻ በማተኮር ብተለማመድ ለውጡን በሳምንታት ጊዜ ታየዋለህ።

ይቀጥላል ..
@Zephilosophy
@Zephilosophy