Get Mystery Box with random crypto!

ኑ እናመስግን

የቴሌግራም ቻናል አርማ nu_enamasgin — ኑ እናመስግን
የቴሌግራም ቻናል አርማ nu_enamasgin — ኑ እናመስግን
የሰርጥ አድራሻ: @nu_enamasgin
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.02K
የሰርጥ መግለጫ

♦#✞የኢትዮጵያ /ኦ/ተ/ቤ/ክ♦
#ኑ_እናመስግን
#በዚህ_ቻናል ላይ ኦርቶዶክሳዊ
◈መዝሙሮችን
◈ ትምህርቶች
◈መንፈሳዊ ምስሎች
◈አባላቱን ሚያሳትፉ ጥያቄና መልሶች ይቀርባሉ
◈ የአባቶች ምክር

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-08 08:33:12 አማኑኤል አንተ ነህ

አማኑኤል አንተ ነህ ገመናዬን ሸፋኝ
አዶናይ አንተ ነህ ገመናዬን ሸፋኝ
እንዳንተ አላየሁም ክፉ ቀን ያወጣኝ 2
እኔስ አላየሁም እንዳንተ የረዳኝ
ገመናዬን ሸፋኝ


ወገን ዘመድ ጠልቶኝ ወጥቼ ከሀገር
ደም እየፈሰሰኝ በህመም ስቸገር
የአብርሀም አምላክ ክርስቶስ መጣልኝ
ልብሱን ብዳስሰው ደሜን አቆመልኝ
ገመናዬን ሸፋኝ


ዝሙት ስካር ዘፈን ህይወቴን አስሮት
በህጋቸው ያዙኝ እንድቀበል ሞት
የሁሉንም ኃጢአት አንተ ገለጥክና
ልጅህን አዳንከኝ ልቤም በአንተ ፀና
ገመናዬን ሸፋኝ


ጅራፍ የሚገባኝ በርባን እኔ ሳለሁ
የሰው ደም ያፈሰስኩ ባይኖቼ እያይሁ
ጌታ ተሰቃየህ እኔ ተፈትቼ
ላመልክህ መራጥኩኝ ፍቅርህን አይቼ
ገመናዬን ሸፋኝ

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
1.4K viewsLove and life, 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 18:49:49
ለድርጅቶ ወይም ለሆቴል /ለሬስቶራንት በፈለጉት መጠን የፈለጉትን ሎጎ እንሰራለን
For additional information
0925878995
0993507391
በ inbox እራሱ ትዕዛዝ እንቀበላለን
@Worrylessnes
@Worrylessnes
Please share our channel
@new_string_art10
1.6K viewsLove and life, 15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 21:32:46 @nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
1.6K viewsLove and life, 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 21:27:14 ስምኪ ጥዑም

ስምኪ ጥዑም ስምኪ ጥዑም/2/
የአምላክ እናት ማርያም " " "
ወለተ ሃና ወኢያቄም " " "
በበረሃ የወደቁ " " "
ስምሽንም የሰነቁ " " "
ማርያም ማርያም እያሉሽ " " "
ይጠግባሉ በስምሽ " " "
ተማፅኜ በዕንተ ስሟ " " "
አፌ ቅኔን እያሰማ " " "
ተመርጠሻል በአምላካችን " " "
ኪዳነ ምህረት እናታችን " " "
ቅድስት ሀና ደስ ይበልሽ " " "
ሊባኖስ ላይ ፀሀይ ወለድሽ " " "
ቅዱሳንን ያከበረ " " "
አጋነንትን ያሳፈረ " " "
ስምሽ ጣዕም ወይነ ቃና " " "
ላመስግንሽ በበገና " " "
አዝ-----
ስምከ ልዑል ስምከ ልዑል/2/
የበረንዳው አማኑኤል " "
የላፍቶ ሚካኤል " "
የጎፋው ገብርኤል " "
የመርካቶ ራጉኤል " "
የሸጎሌው ሩፋኤል " "
የካሳንቺስ ዑራኤል " "
አዝ-----
ስምከ ቅዱስ ስምከ ቅዱስ/2/
የአራዳው ጊዩርጊስ " "
የጎፋው መርቆሬዎስ " "
አባታችን ፊሊጶስ " "
አባታችን እስትንፋስ " "
አባታችን አማኑኤል " "
አዝ-----
ስምከ አበባ ስምከ አበባ/2/
ሚካኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ገብርኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ዑራኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ሩፋኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ራጉኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ዑራኤል ሆይ ቤቴ ግባ "

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
2.1K viewsLove and life, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 21:33:34 ምን ሰማህ ዩሐንስ

ምን ሰማ ዩሀንስ በማጸን ሳለህ/2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ/2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ/2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/2/
አዝ.........
ከተፈጥሮ በላይ ያስገደህ ክብር
እንዴት ቢገባው ነው የእናታችን ፍቅር/2/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ/2/
አዝ......
በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት/2/
እንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ/2/
አዝ..........
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም/2/
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ ከጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ/2/

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
1.6K viewsLove and life, 18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 15:32:10 ​​ አበባዮሽ

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2)
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ጌቶች አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ዘመን መጣ ብለን

አበባዮሽ ለምለም(2)
ባልንጀሮቼ ለምለም
ግቡ በተራ ለምለም
በእግዚአብሔር መቅደስ ለምለም
በዚያች ተራራ ለምለም
እንድታደንቁ ለምለም
የአምላክን ሥራ ለምለም
ህይወት ያገኛል ለምለም
እርሱን የጠራ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም (2)
ክረምት አለፈ ለምለም
ጨለማው ጠፋ ለምለም
የመስቀሉ ቃል ለምለም
ሆነልን ደስታ ለምለም
እናገልግለው ለምለም
ቤቱ ገብተን ለምለም
ትንሽ ትልቁ ለምለም
ተሰልፈን ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ያንን ኩነኔ ለምለም
ዘመነ ፍዳ ለምለም
የሞቱ በራፍ ለምለም
ያ ምድረበዳ ለምለም
ልክ አንደ ክረምት ለምለም
ሄደ ተገፎ ለምለም
ፀሐይ ወጣልን ለምለም
ጨለማው አልፎ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ይኸው መስከረም ለምለም
ይኸው ፀሐይ ለምለም
ንጉሡ ወርዶ ለምለም
ከላይ ሰማይ ለምለም
አውደ ዓመት ሆነ ለምለም
ደስታ ሰላም ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ ለምለም
በአርያም ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ይኸው አበባ ለምለም
ለምለም ቄጤማ ለምለም
አዲሱ ዘመን ለምለም
አምጥቷልና ለምለም
በሩን ክፈቱ ለምለም
መኳንንቶቹ ለምለም
የክብር ንጉሥ ለምለም
ይግባ ቤታችሁ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ቤታችሁ ይሙላ ለምለም
ሰላም ደስታ ለምለም
ሰጥቷችሁ እርሱ ለምለም
የሁሉ ጌታ ለምለም
ከዘመን ዘመን ለምለም
ያሸጋግራችሁ ለምለም
የሽበትን ዘር ለምለም
ይሸልማችሁ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ

ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ

ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
1.7K viewsLove and life, 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 14:04:52 አዲሱን አመት ባርክልን

#የአዲስ_አመት_መዝሙር

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
1.3K viewsŁøĢªŵ, 11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ