Get Mystery Box with random crypto!

በረከታችሁን በከንቱ አታባክኑት! የ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ትዉልዶች የሆነዉ የማንበብና የመጻፍ ችግ | ንቁ'የመዳን ቀን ዛሬ ነዉ!

በረከታችሁን በከንቱ አታባክኑት!


የ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ትዉልዶች የሆነዉ የማንበብና የመጻፍ ችግር የለብንም ነገር ግን ዕዉቀትን በሕይወት ኑሮ ዉስጥ ተግባራዊ አድርገን የመኖር ትልቅ ፍርሃትና ችግር አለብን! በዚህም ምክንያት 95 በመቶ በጭፍኑ የሚጓዝ ሆኗል፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በሰጠን መክሊት ሰርተን ማትረፍ ስላልቻልን፥ የመክሊት ባለቤት መሆን ማለት የግድ፤ ዘማሪ፤ዲያቆን፤ ቄስ፤ ሰባኪ፤ መሆን ማለት አይደለም እነዚህ መክሊቶች እንደ አምላክ ቸርነት ከብዙ ልፋትና ጥረት በኋላ የሚገኙ ተጨማሪ ስጦታዎቻችን ናቸዉ እንጂ ቁጭ ብለን ስለፈለግናቸዉና እድለኛ ስለሆን ብቻ የምናገኛቸዉ አይደሉም መድሃኒታችን እግዚአብሔር እነዚህንና እነዚህን መሰል ሌሎች ተጨማሪ መክሊቶችን ሰርተን እንድናተርፍበት እጅ እግር ዓይን ጆሮ አንደበት ሆድ የሚባሉ መክሊቶች ለሁላችንም ተሰጥቶናል ችግሩ በረከቶቻችን በአግባቡ ተጠቅመንበት ሌላ ተጨማሪ በረከት አናተርፍበትም እንጂ ሳንታክት ብንሰግድ ሳንታክት ብንጸልይ እሺ በጀ ብለን ንስሀ ገብተን በቅዱስ ቁርባን ብንታተምና ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ፈጥረን ብንኖር መሆን የምንፈልገዉንና መድረስ ካለብን ደረጃ ላይ ከመድረስ የሚያግደን አንዳች ነገር አይኖርም ነበረ! ብዙሃኖቻችን ጋር አንድ የተሳሳተ አስተሳሰብ አለ እርሱም የ40 ዕድል የሚባል ነገር ይሄ አስተሳሰባችን ተጽዕኖ ስላሳደረብን ዉስጣችን ያለዉን ኀይል ወደ ዉጪ አዉጥተን እንዳንጠቀምበት አድርጎን በልባችን ዉስጥ ሸምቀን ለማስቀመጥ አስገድዶናል ልብ በሉ! እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ሲፈጥረን እኩል አድርጎ እንጂ አንዱን አሳንሶ አንዱን አስበልጦ አልፈጠረም፡ ችግሩ ከመሰረቱ ተይዘን የምናድግበት አስተዳደግና ራስ ጋር ሆነና እርሱ የሰጠንን በረከቶቻችንን በአግባቡ ሳንጠቀምበት በመቅረታችን መሆንና ማግኘት የምንፈልገዉን ነገር በልባችን ሸምቀን ለመቀመጥ ተገደድን እንጂ መድሃኒታችን እግዚአብሔር የሚያዳላ አባት ሆኖ አይደለም፥ ዛሬም ከልብ ለዉጥን በመሻት ወደ እግዚአብሔር ብንቀርብ ፈልገን የምናጣዉ አንዳች ነገር የለም፡ ስለዚህ የማይጨበጥ ተስፋ እያሰባችሁ የተፈጥሮ በረከታችሁን በከንቱ አታባክኑ ቁጭ ብለን ካለብን ችግር ዉስጥ ለመዉጣት ስለፈለግንና ስላሰብን ብቻ የምናመጣዉ ለዉጥ የለም ሀሳብ ወደ ተግባር ካልተለወጠ ደግሞ የማያልቅ ቅዠት ይሆንና ሕይወትን በምሬት ጀምረን በምሬት ለመጨረስ እንገደዳለንና ጥራችሁ ግራችሁ ሌላ መክሊት የምታተርፉበትን አንደበታችሁን እጅ እግራችሁ ዓይን ጆሮአችሁን ሆድና አእምሮአችሁን በከንቱና ለከንቱ ነገር አታዉሉት በጉልበታችሁ ስገዱበት በሆዳችሁ ጹሙበት በአንደበታች ጸልዩበት በዓይናችሁ ቅዱሱን መፅሐፍ አንብቡበት በጆሮአችሁ መልካም ነገር ስሙበት በአእምሮአችሁ መርምሩበት የሰበሰባችሁትን ዕዉቀት በሕይወት ኑሮአችሁ ኑሩት ለጥቆ ተጨማሪዉን መክሊት ለሰጪዉ ተዉለት ጊዜዉ ሲደርስ ዋጋችሁን በግልጥ ይሰጣችሁኋልና። ለራሳችሁ ጥቅም ስስታም አትሁኑ ቆማችሁ መጸለይ የማትችሁ ከሆነ አቅሙን እስክታገኙ ቁጭ ብላችሁ ጸልዩ ብዙ መስገድ ባትችሉ ጠዋት 3 ማታ 3 መስገድ አያቅታችሁም ግማሽ ቀን መጾም ባትችሉ አረፋፍዶ መመገብ አያቅታችሁም መፅሐፍ ቅዱስ ብዙ ማንበብ ቢያቅታችሁ አንድ ምዕራፍ ማንበብ አያቅታችሁምና ካለባችሁ ችግር ወጥታችሁ ብርሃንን ታዩ ዘንድ በምትችሉት ታገሉ ኦርቶዶክሳዊያን የጉስቁልና መንፈስ ነዉ ያለባቸዉ ለመባል የበቃነዉ ከእግዚአብሔር ርቀን ከአንገት በላይ በአፍ ብቻ አባታችን ሆይ እያልን የአባትነቱን ጣዕም ባለማወቃችንና በሕይወት ኑሮአችን ላይ እንዲገለጥ ባለመፍቀዳችን ነዉና ደጃችሁ በር አፍ ላይ ቆሞ በራችሁን እንድትከፍቱለት ለሚለምናችሁ በራችሁን ክፈቱለት ወደ ቤታችሁ ይገባ ዘንድ ፍቀዱለት።እንዲሁ በማሰብ በመመኘት በማዉራት በማስመረር ብቻ የሚፈጠር አንዳች ነገር የለም፤ የግድ ሀሳብ ወደ ተግባር መለወጥ አለበትና ተንቀሳቀሱ ከመድሃኒቱ ጋር ሕብረት ፈጥሮ ካልተጉ ዉጤት የለም ካልጣሩ ማግኘት የለም ካልታገሉ ማሸነፍ የለም ስለዚህ የህልም እንጀራና ምዕናብን መከተል ይብቃችሁና ሀሳባችሁን ወደ ተግባር ለዉጡት ተአምር ከሰማይ እንዲወርድ አትጠብቁ ተአምር የምትፈጥሩበት ዉድ የአምላክ በረከቶች አላችሁና ከተቀመጣችሁበት ተንቀሳቀሱ ለምትፈልጉት ነገር ቀጠሮ አትስጡ ነገም ሌላ ቀጠሮ ይዞ ይመጣልና ወደኋላም ዘወር ብላችሁ ትናንትናችሁንም ተመልከቱ ስንት ትናንቶችን ለነገ ብላችሁ በቀጠሮ በማለፋችሁ ዛሬም ምንም የመጣ ለዉጥ እንደሌለ አስተዉሉና ነገ ልታደርጉ ያቀዳችሁትን ዛሬ አድርጉት እግዚአብሔር ይዞ ሽንፈት የለምና!!!!!

እንኳን ለዓብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! መልካም የጾም ጊዜ ይሁንላችሁ በርቱና ጹሙ!

@Nkuyemedankenzare