Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

በሱዳን በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ

ንሥር ብሮድካስት
ሐምሌ 17/2015

የሱዳን ጦር በፖርት ሱዳን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቋል።

የሲቪል አንቶኖቭ አውሮፕላኑ በመብረር ላይ እያለ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞት ነበር።

ከሟቾቹ መካከል አራት ወታደራዊ አባላት እንደሚገኙበት ተጠቁሟል። አንዲት ወጣት ልጅ ከአደጋው እንደተረፈች ተነግሯል።

በሚያዝያ ወር አጋማሽ በጦር ሠራዊቱ እና በአርኤስኤፍ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ከሶስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን እስካሁን ለግጭቱ ማብቃት የመፍትሄ ምልክት አላሳየም።

-------------------------------------------------------------
ወቅታዊ፤ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት

Youtube :-https://www.youtube.com/channel UC9yOQepDMiEq7xHUodXo0kQ

FaceBook Page 1 :    https://www.facebook.com/Nisirbroadcast

FaceBook Page 2:  https://www.facebook.com/Nisirmereja 
 
Telegram:    https://t.me/nisirbroadcasting

Website: https://nisirbroadcasting.com
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።