Get Mystery Box with random crypto!

በጉማ አዋርድ ላይ ግንባሯን በጥይት መመታቷንና አፏን በሽቦ መለጎሟን በሚያሳይ ሜካፕ የቀረበችውን | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

በጉማ አዋርድ ላይ ግንባሯን በጥይት መመታቷንና አፏን በሽቦ መለጎሟን በሚያሳይ ሜካፕ የቀረበችውን ፍላጎት አብርሃምን ከስራ አገደ

ንሥር ብሮድካስት
ሰኔ 28/2015

ሰኔ 2/2015 ምሽት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው 9ኛው የጉማ ሽልማት ላይ የወገኗን መታፈን በሜካፕ ያሳየችው የቴሌቭዥን ፕሮግራም አዘጋጇና ታዋቂ ቲክቶከሯ ፍላጎት አብርሃም/የልጅ ማኛ/ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ከነበራት የኢትዮጵያ አይዶል የዳኝነት ስራዋ ተሰናብታለች።

ፍላጎት ከዚህ በፊት በአትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የተሰጥኦ ውድድር /ኢትዮጵያን አይዶል/ ላይ በዳኝነት ስራ ቀረፃዎችን ከውና እንዲሁም ከሚዲያው ጋር ውል ተዋውላ ነበር።

ይሁን እንጂ ተቋሙ አዲስ በገነባውና ነገ በሚያስመርቀው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንጻ ሰኔ 27/2015 ምሽት በጀመረው የኢትዮጵያን አይዶል ውድድር ላይ በፍላጎት ቦታ ከዚህ ቀደም በውድድሩ የዳኝነት ስራ ላይ ያልነበረው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ተተክቷል።

ሚዲያው ፍላጎትን ከዚህ ስራዋ ያገደበትን ምክንያት በግልፅ ማወቅ ባይችሉም ፣ በጉማ አዋርድ ላይ በሜካፕ ባስተላለፈችው መልዕክት ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮቻችን ነግረውናል ሲል ሮሃ ሚዲያ ዘግቧል።

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube: https://buff.ly/3mOQNyX

FaceBook Page 1 : https://buff.ly/3GZyFJA

FaceBook Page 2: https://buff.ly/3Ad8zPE

Telegram: https://buff.ly/3Tcx06A

Website: https://buff.ly/3DETCqV

Twitter: https://twitter.com/NISIRInternati1

Instagram: https://www.instagram.com/nisirbroadcast/
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።