Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምግብ እርዳታን ላልተፈለገ ዓላማ በማዋል ተሳትፏል መባሉን ሰሞኑን ባ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምግብ እርዳታን ላልተፈለገ ዓላማ በማዋል ተሳትፏል መባሉን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አጣጥሏል

     ንሥር ብሮድካስት
     ሰኔ 6/2015

በምግብ እርዳታ ዝርፊያና ለራስ ጥቅም በማዋል የተሳተፉ የሠራዊቱ ክፍሎች ወይም ተቋማት የሉም በማለት የገለጠው መግለጫው፣ ሠራዊቱ ከተረጅዎች እርዳታ ሊነጥቅ ይቅርና ለእርዳታ ፈላጊዎች እርዳታ ለመስጠት በቂ የሎጂስቲክስ አቅርቦት ያለው ተቋም ነው ብሏል።

ሠራዊቱ በድርጊቱ በግለሰብ ደረጃ ተሳትፈው የተገኙ አባላቱ ካሉ ግን ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ሠራዊቱ ይህንኑ መግለጫ ያወጣው የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት በውስጥ ምርመራው በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ወታደሮችንና የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመመገብ እንደዋለ ደርሶበታል የሚል ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው።

=======================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት

YouTube 1: https://youtube.com/@nisirmedia2

YouTube 2: https://youtube.com/@nisir

FaceBook Page 1 :    https://www.facebook.com/Nisirbroadcast

FaceBook Page 2:  https://www.facebook.com/Nisirmereja    
  
Telegram:    https://t.me/nisirbroadcasting

Website: https://nisirbroadcasting.com
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.