Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት ማገርሸቱ ተሰማ ንሥር ብሮድካስ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

በሱዳን ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት ማገርሸቱ ተሰማ

ንሥር ብሮድካስት
ሰኔ 5/2015

ውጊያው የቀጠለው ተፋላሚዎቹ ቀደም ሲል የደረሱት የ24 ሰዓታት የተኩስ አቁም ጊዜው ካበቃ በኋላ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡

የ24 ሰዓታቱ የተኩስ አቁም ከእስካሁኖቹ በተሻለ ተከባሪ ነበረ ተብሏል፡፡

ቀዳሚዎቹ የተኩስ አቁሞች ተደጋጋሚ መጣስ ያጋጠማቸው ሲሆን ተፋላሚዎቹን በአንተ ነህ አንተ ነህ ሲያካሰሱ ሰንብተዋል፡፡

ትናንት የተኩስ አቁሙ እገዳ ውጊያ ተቀስቅሶባቸዋል ከተባሉት ስፍራዎች መካከል መዲናዋ ካርቱም እና ኦርዱርማን ይገኙበታል ተብሏል፡፡

2 ወራት ባስቆጠረው ጦርነት የተነሳ ሱዳንን ወደ ሕዝባዊ አስተዳደር ለማሸጋገር ተጀምሮ የነበረው ሂደት ተሰናካክሎ እንደቀረ ዘገባው አስታውሷል፡፡

=======================
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት

YouTube 1: https://youtube.com/@nisirmedia2

YouTube 2: https://youtube.com/@nisir

FaceBook Page 1 :    https://www.facebook.com/Nisirbroadcast

FaceBook Page 2:  https://www.facebook.com/Nisirmereja    
  
Telegram:    https://t.me/nisirbroadcasting

Website: https://nisirbroadcasting.com
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።