Get Mystery Box with random crypto!

በስመ መከላከያ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ አባላት ምን ያድርጉ? ***** መከላከያና ኦነግ በ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

በስመ መከላከያ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ አባላት ምን ያድርጉ?
*****

መከላከያና ኦነግ በጥምረት በተመሳሳይ አዛዦች እየተመሩ የአገር እለኝታ የሆነውን ፋኖ ለማጥፍት በሚል በአራት ኪሎ ትእዛዝ የአማራን ክልል ከወረሩ እነሆ ሳምንታትና ወራት እየተቆጠሩ ነው:: በየቀኑ የሰው ህይወት እየጠፋ ነው ነገር ግን ባለስልጣናቱ የሚጠፋውን ነፍስ የዝንብ ነፍስ ካደረጉት እመታትን አስቆጥረዋል::

መከላከያ የሃገር መሆኑ ቀርቶ የፓርቲ ስልጣን አስጠባቂነቱን ካስመሰከረ ሰነባብታል:: አሉ የሚባሉትን የድሮ የመከላከያ አባላት በሰሜኑ ጦርነት አስጨርሰዋል:: አሁን ኦነግም ሆነ መከላከያ የሚባለው ሃይል አንዱ ከአንዱ የሚለይ አይደለም:: ተመሳሳይ ዮኒፎርሞችን እንዲለብሱ እየተደረገ መከላከያና የሽመልስ ኦነግ ቡድን አብሮ በጣምራ አማራን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል::

ጥያቄው ግን የአማራ ብልፅግና አማራን ለመምራት ምን ሞራል አለው? የህዝቡን ብሶት የሚያውቀው የአማራ ብልፅግና የታችኛው ካድሬስ እንደተለመደው አመራሩን ወንበር እያስጠበቀና አማራን እያዋረደ ሊቀጥል ነው?

በመጨረሻም በስመ መከላከያ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ አባላት አሁን ላይ ምን ማድረግ አለባቸው? ሃሳበወን ያጋሩ::