Get Mystery Box with random crypto!

ከንሥር እንግዳ ፦ ፋኖን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ !! ነሃሴ 22/2014 ************** | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

ከንሥር እንግዳ ፦ ፋኖን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ !!
ነሃሴ 22/2014
*********************

ፋኖን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ !! እኛም ለምንሞትለት ህዝብ ሲባል እኩይ ድርጊታችሁን እናስቆማለን።

የክልሉ ህዝብ እና መንግስት የተለያዩ ናቸው።
የክልሉን መንግስት የሚዘውሩት ስነ ልቦናቸው ተንበርካኪ እና የስልጣን ጥመኞች ናቸው።

የተላላኪነት መንፈሳቸው፣ዕውቀት ጠልነታቸው ፣ አድርባይነታቸው እና አማራን አሳልፎ በመስጠት ፓለቲካውን ለማበላሸት በኦህደድ በኩል ውክልና የተሰጣቸው ናቸው።

የአማራ ህዝብ ደግሞ በሃገረ መንግስት ያለውን ድርሻ ተነጥቆ የአምባገነኖች እና የአሸባሪ ሃይሎች መጫወቻ ከሆነ ሰነባብቷል።

ስለሆነም የህዝባችን ጠላቶች ቀዳማይም ድሃራይም ቅጥረኛ ብአደኖች ናቸው።

ስለሆነም ህዝባችንን እያስወረሩ በስልጣን መቀጠል ተገቢነት የሌለው አካሄድ በመሆኑ በሁሉም አቅጣጫ ያሰራችኋቸውን እውነተኛ የህዝብ ልጆች ፍቷቸው።

ፋኖን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ ።
በሁሉም ዘርፍ እየተባላን የግፈኞችን ስልጣን የምናስቀጥልበት መሰረታዊ ምክንያት መቆም አለበት!!

አማራነት /ሞት በማለት ሲልከስከስ የነበረው ሃይል ጭምርም በፋኖወቻችን ላይ ያደረገውን ክህደት አንረሳውም።

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወድህ የሚታዩት መጓተቶች መሰረታዊ ምክንያታቸው የብልፅግና መዋቅር ቢሆንም በተለይ የአማራን የህልውና አደጋ በውል ያልተረዳው ቅጥረኛ ሃይል በጊዜ ከድርጊቱ እንድያቆም ብንወተውትም ሁኔታዎች ግን የበሳ መቀጠላቸው ዕረፍት ሊሰጠን አልቻለም።

የአማራ ህዝብ የቅጥረኞች መናሃሪያ በመሆን እውነተኛ የህዝብ ታጋዮችን ጭምር ሲያስበላ መኖሩ ሳያንስ አሁንም ለህወሓታዊ ወረራ ምክንያት በመሆን ታጋዮቻችን አሳስሮ ተጨማሪም ጥቃት እነሰዲፈፀምብን አንሻም።

ስለሆነም ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ባሉ አካባቢዎች የታሰሩ እና የተሳደዱ የፋኖ አመራር እና አባላቶች በይቅርታ ተፈትተው ለህልውናችን ተግዳሮት የሆነውን አሸባሪ ሃይልና ግብረ አበሮቹን በጋራ ልንታገል ይገባል።

የአማራ ህዝብ በታሪክ ከስህተቱ እንዳይማር ያደረጋችሁ የፓርቲ ብር ተከፋፋዮች ሁሉ አሁንም ከፋኖ ላይ ያላችሁን የተዛባ አረዳድ በጊዜ ለማስተማር ያባከነውን ጊዜ ሁሉ እንድንፀፀትበት አታድርጉን።

ጀግኖቹ የአማራ ልጆችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፍቱ!!
ወንድሞቻችን የታሰሩት የግፈኞችን ስልጣን ለማስቀጠል በዱር በገደል አሸባሪን የታገሉ እንጅ የስልጣን ጥመኞች በሚፈብረኩት የብልፅግና አጀንዳ አይደለም።

የአማራ ታጋዮችን በፓለቲካዊ መንገድ ማሰር የተለመደ ቢሆንም የአሁናዊ ዕስር ግን የሚለየው ህዝቡ በተለየ ሁኔታ የጥቃት ተጋላጭ እንድሆን መደረጉ ነው።

ፋኖን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት የክልሉን ህዝብ እና መንግስት ተቀራርቦ የተቃጠበትን ጥቃት ለመመከት ወሳኝ ተግባር በመሆኑም ጭምር ነው።

ፋኖን አታሳዱት!!
የትርክት ሰለባ አታድርጉት!!ክድ

ከንሥር እንግዳ
ነሃሴ 22/2014
ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።