Get Mystery Box with random crypto!

ከንሥር እንግዳ _ የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላት ቅጥረኛው የስልጣን ጥመኛ እና ተጋሪዎቻቸው የአማራ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

ከንሥር እንግዳ _ የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላት ቅጥረኛው የስልጣን ጥመኛ እና ተጋሪዎቻቸው የአማራ ባለሀብቶች ናቸው።
ነሃሴ 22/2014
*********************************************

የአማራ ህዝብ በእነዚህ ሁለት ቡድኖች ሲዋረድ ኗሯል።
ወጣቱ ለሃገርና ለህዝቡ ታማኝ ነው። ሃገሩን እና ህዝቡን ለማዳን በሁሉም አቅጣጫ እየተዋጋ የህይዎት መስዋአትነት ከፍሏል።
አሁንም ውድ ህይዎቱን ለማጣት ከየአቅጣጫው እየተመመ ይገኛል። ትላንት ወያኔ ሶስተኛውን ወረራ በጀመረበት ጊዜ እንኳን ከመቅፅበት ውድ ህይወታቸውን ያጡት እልፍ የአማራ ወጣቶች ናቸው። ስለሆነም የአማራ ወጣቶች የህይዎት መስዋአትነት በምንና እንደት ባለ የትግል ስትራቴጅ ሃገሩንና ህዝቡን ሊያድን እንደሚገባ በደንብ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል።

ከአሸባሪው ሃይል በላይ ክልሉን ለጠላት አሳልፎ የሰጠው የአማራው ቅጥረኛ ሁሉ #የሎሌነት እሺቅድድሙ የት እንደሚያደርሰው ባይታወቅም የክልሉን ህዝብ ግን ዳግመኛ ከማስወረር አላዳነም።

ሶስት ጊዜ ሙሉ በቅጥረኛ ተላላኪዎች እና በሆዳሞች የክልሉ ህዝብ ተደፍሯል። የነቁ አማራዎችንና ነበልባሉ ፋኖን ሲያሳድድ የከረመው ቅጥረኛ የክልሉን ህዝብ ድጋሜ አስወረሮታል።አሁንም ተላላኪዎች ክልሉን ባልተገባ መንገድ ከማተራመስ ውጭ በጦርነቱ ላይ አበርክቶም አቅምም የላቸውም።

ስለሆነም የአማራ ልሂቃንን፣የአማራ ፋኖን እና የአማራ አክቲቪስቶችን ሲያሳድድ እና ሲያስገድል የነበረውን የአምባገነኖች ስልጣን አስቀጣይ ቅጥረኛ ሁሉ ከህዝቡ ላይ እጁን ያነሳ ዘንድ እጠይቃለሁ።


ቆሞ ቀር የፓለቲካ አካሄድ እና የሎሌነት እሺቅድድም የተራ ግለሰቦች ፍላጎት እና ጥቅመኝነት ቢሆንም በአማራው ህዝብ ዘንድ የጣሉትን ጠባሳ በታሪክ የምንረሳው አይደለም።

ስለሆነም ወገኔ ሆይ ከቅጥረኞች ጋር የምናደርገውን ትግል ከጠላት እኩል ልንዋጋቸው መቻል ይኖርብናል።
ህዝባችንን ከወረራ እና ከጠላት ለማዳን ሁነኛው መፍትሔ ሎሌዎችን ከህዝብ ትከሻ ላይ እንዲወርዱ ማድረግ ነው።

5ዐ ሚሊዮን ህዝብን በተራ ሎሌዎች እያስወረሪ መቀጠል ተቀባይነት የለውም።

የአማራን ህዝብ ጠላት ከሎሌዎቹ በላይ አልገደለውም።

ህዝብ የተደራጀ ሲመስለው እና መብቱን ለመጠየቅ ከድብታው በወጣ ጊዜ በጭካኔ የሚያስደበድበው ሃይል ወያኔም /ኦነግም አለመሆናቸው እየታወቀ ስለምን ቅጥረኞችንስ በሚገባቸው ልክ መናገር አቃተን።

ስለሆነም ጠላትን ለመፋለም ነፃ እና ምቹ ሁኔታ መፈጠር አለባቸው ብለን እናስባለን።
የምቹ ሁኔታዎች አንዱ መንገድ ደግሞ የቅጥረኞች እና የንዋይ ፍላጎታቸውን በአማራ ህዝብ ስም ያደረጉ አካላተን ሁሉ ማስወገድ ተቀዳሚ ሃላፊነታችን መሆኑን አንዘንጋ!!

የአማራ ህዝብን ለሶስተኛ ጊዜ ያለቅድመ ሁኔታ ያስወረሩ ሃይሎች ሁሉ በአማራ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው እና እንዲመሩት ጭምር ይሁንታ ያልስጣቸው ናቸው።

በሎሌነት እሺቅድድም ህዝብን ከወረራ ማዳን አይቻልም።

ከንሥር እንግዳ
ነሃሴ 22/2014



ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።