Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ሃይል አቅምን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቋል | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ሃይል አቅምን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቋል ተፈፃሚነቱን በቅርበት የምንከታተል ይሆናል።

ንሥር ብሮድካስት
ነሃሴ 21/2014

ትናንት አርብ ነሐሴ 20 የፌደራሉ መንግሥት የተመረጡ የህወሓት ወታደራዊ ቦታወችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቋል።
መንግሥት እስከ ለሰላም ድርድር ቢጠብቅም ህወሓት ጥቃቱን እንደቀጠለበት ነው ሲልም ገልጿል።
በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለህወሓት ቡድን ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ቦታወች ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
ስለሆነም የትግራይ የምትኖሩ በተለይም ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች እራሳችሁን እንድታርቁ እንመክራለን ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram:https://www.instagram.com/nisirbroadcasting
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።