Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ ለማስተማር በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ ። | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

በአዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ ለማስተማር በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ ።

ንሥር ብሮድካስ
ነሃሴ 20/2014

በአዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ ለማስተማር በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።

"በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር አለማቀፋዊ መብት ነው፤ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና የመዳኝት መብት አላቸው" ያሉት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ ናቸው።

ይህን የሚጠይቁ አካላት በማንኛውም መልኩ ለማስተናገድ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዝግጁ መሆኑንም ገልፀዋል።

የት/ት ቢሮ ኃላፊው እንዳረጋገጡትም በቀጣዩ የትምህርት ዘመን አፋን ኦሮሞ በአዲሱ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ተጠቃሎ ለማስተማር በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በሆነው ፤ በኦሮምኛ እየተማሩ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይህንን ሂደት አንዳንድ አካላት ሌላ መልክ ለመስጠት እየሞከሩ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ "ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ ያለምንም ችግር እየሄደ ነው። " ሲሉም የስራ ኃላፊው አክለዋል።

በጉዳዩ ላይ ያለው ብዥታም ቀስ በቀስ ይጠራል ሲሉ ተደምጠዋል።

ንሥር ብሮድካስት የሁላችንም ድምፅ!

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube:https: https://bit.ly/3No0s7x
FaceBook:https://www.facebook.com/Nisirbroadcasting
Telegram:https://t.me/nisirbroadcasting Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter:https://twitter.com/NISIRInternati1