Get Mystery Box with random crypto!

      በዚህ ረገድ አሁንም ኢትዮጵያውያን መናጋት የለባቸውም፡፡ ነቅተው፣ ተደራጅተውና ተደማምጠው | The Niles ናይል 🇪🇹

      በዚህ ረገድ አሁንም ኢትዮጵያውያን መናጋት የለባቸውም፡፡ ነቅተው፣ ተደራጅተውና ተደማምጠው የጠላትን ሴራ ማምከንና ግድቡን ከዳር ለማድረስ መረባረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ሚዲያዎቻችንና የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ ትምህርት ቤቶችና የምርምር ተቋማት ከተለመደው አሰልቺ ነገር ወጥተው ለጉዳዩ ጠንከር ያለ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፡፡ የማንንም ፈቃድ ሳይጠብቁም ለመጪው ትውልድ የተሻለች አገር ለማስረከብ ዓባይ ዓባይ ማለት አለባቸው፡፡

     ሕዝባችንን በበቂ ሁኔታ ስለግብፅም ሆነ ስለሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ስትራቴጂካዊና ጂኦ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች ማሳወቅ፣ ማስተማርና ማንቃት የዘወትር አጀንዳ መሆን አለበት። ጠላቶቻችን የሚሠሩት ለአሉታዊ ትርክትና ለኢፍትሐዊ ተጠቃሚነትም ሲሆን፣ የራሳቸውን ሕዝብ በማንቃትና ወጥ አመለካከት እንዲኖረው በማድረግ ላይ አተኩረው ነው፡፡

     የእኛ የሕዝብም ይባሉ አብዛኞቹ የግል ሚዲያዎች የጠላትን ፕሮፓጋንዳ ለማምከንና ሕዝባችን ለብሔራዊ  ጥቅሙ መከበር በአንድ እንዲቆም ለማድረግ ብርቱ ሥራ መከወን እንደሚጠበቅባቸው ማስታወስ ያስፈልጋል። የግብፅ ሴራ በውስጥ ካሉ የአገር (የመንግሥት አላልኩም) ባላንጣዎች ዘመቻ ጋር ተቀናጅቶ የቀጠለ ሲሆን፣ ይህን ሰባብሮና አንኮታኩቶ መጣል፣ አሸናፊነታችንን በሁሉም መስክ ማስቀጠል የእኛና የእኛ ኃላፊነት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ የካይሮና ሼሪኮቻቸው ሴራ ቢያይልም፣ ዓባይ ለወገኑ ትሩፋት ከመሆን የሚገታው የለም ብሎ አፍ ሞልቶ መናገር የሚቻለውም ይህንኑ በማድረግ ብቻ ነው፡፡