Get Mystery Box with random crypto!

የካይሮ ሴራ ቢበረታም ማምከኛው በእጃችን ላይ ነው በንጉሥ ወዳጅነው        ታላቁ የህዳሴ | The Niles ናይል 🇪🇹

የካይሮ ሴራ ቢበረታም ማምከኛው በእጃችን ላይ ነው

በንጉሥ ወዳጅነው

       ታላቁ የህዳሴ ግድብ የተገነባበት ረዥሙ ዓባይ ወንዝ ተዝቆ የማያልቅ ታሪክ፣ የተፈጥሮ ሀብትና ውበት፣ ፀጋና በረከት የሞላበት ነው። የእኛኑ ዓባይ ግብፆች የህልውናቸው መሠረት በመሆኑና በኃያልነቱ የተነሳ ‹‹ኢሲስ›› እና ‹‹ኦሲሪስ›› የሚባሉ አማልክት ፈጥረውለት ሲያመልኩት ኖረዋል። በዓለማችን 263 ያህል ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ቢኖሩም፣ ረዥም ርቀት በመጓዝና በርካታ አገሮችን በማቋረጥ ቀዳሚ የሆነው ዓባይ (ናይል) ወንዝ 6,650 ኪሎ ሜትር በመጓዝ 11 አገሮችን  የሚያካልል መሆኑም የሚስጥሩ መጀመርያ ነው፡፡

    ዓባይን ሦስት ወንዞች ተጣምረው ይፈጥሩታል። እነሱም ከብሩንዲ ሰንሰለታማ ተራሮች የሚመነጨው ነጭ ዓባይ፣ ከኢትዮጵያ የሚመነጨው ጥቁር ዓባይና የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ሱዳን ሲደርስ ‹‹አትባራ›› በሚል ስያሜ የሚጠራው ‹‹ተከዜ ወንዝ›› ናቸው፡፡ እነዚህ ሦስት ወንዞች ካርቱም ላይ ከተገናኙ በኋላ ‹‹ናይል›› ይሰኛሉ።

     የሱዳንና የግብፅን በረሃዎችን ሰንጥቆና አቋርጦ ረዥሙ የናይል ጉዞ እስከ ሰሜናዊ ግብፅ በመዝለቅ በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ይጠናቀቃል። የናይል ወንዝ 86 በመቶ ያህሉ የውኃ ሀብት የሚሄደው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህ ውስጥ የዓባይ ወንዝ ብቻውን 53 በመቶ ይሸፍናል፣ የዓባይ ታላቅነት ቅኔም ሌላው መገለጫ ይኼኛው እውነታ ነው፡፡

      ያም ሆኖ ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ መፈጠሪያ ሆና ለዘመናት በዓባይ የመጠራት እንጂ የመልማት ዕድሉ  አልነበራትም፡፡  ማንኛውም አገር ባሉት ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ሌሎች የተፋሰሱ አገሮችን በማይጎዳ መንገድ በውኃ ሀብቱ የመልማት ተፈጥሯዊና ሕጋዊ መብት እንዳለው ቢታወቅም፣ ለዘመናት ከሀብታችን ሳንጠቀም መቆየታችን ነው የሚያስቆጨው፡፡ 

      በእርግጥ ዓባይ ለግብፆች ብቸኛ የውኃ ምንጫቸው ነው፡፡ የከርሰ ምድር ውኃ ሊኖራቸው ቢችል እንኳ ስለእሱ ማሰብ አይፈልጉም፡፡ ዓይናቸው፣ ጆሮአቸውና ልባቸው ያለው ዓባይ ላይ ብቻ እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ ዓባይ ለግብፆች የዕለት ጉርሳቸውና የዓመት ልብሳቸው ነው፡፡ ሥጋታቸው፣ ቅዠታቸው፣ ጌጣቸው፣ ክብራቸው፣ ኩራታቸውና አጠቃላይ ህልውናቸው በዓባይ ውኃ ደኅንነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

ሊዚህም ነው ትናንትም ሆነ ዛሬ ካይሮ የትኛውንም ወጥመድና ሴራ በመፈጸም እንኳንስ እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለውን ፕሮጀክት፣ የትኛውንም የውኃ ልማት ለማሰናከል ወደ ኋላ የማትለው፡፡ ትርፉ ትዝብት እንጂ በተቀየረ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ፣ እያደገ በመጣ የአገራችን ሕዝብና ምጣኔ ሀብት ብሎም የማደግ ፍላጎት በሰጥቶ መቀበል መርህ በጋራ ለመጠቀም ማሰቡ ነበር የሚበጃት፡፡ ሴራው የበረታን እንደሆን እንጂ ሊሰናከል እደማይችል በገቢር ታይቷል፡፡

      ገና ከጀማሬው አንስታ አገራችን የግድቡ ተልዕኮ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትና ማለፍ መሆኑን፣ ግብፅን እንደማይጎዳ፣ እንዲያውም ለግብፅ እንደሚጠቅም፣ ወደ ግብፅ በሚሄደው ውኃ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ እንደሌለውና ለተፋሰሱ አገሮች በአጠቃላይ ለሱዳንና ለግብፅ ደግሞ በተለይ አስረድታለች፡፡ ልዑካኖቻቸውን ተቀብላ፣ የእሷንም ልዑካን ልካ በጉዳዩ ላይ ግልጽ ውይይት አድርጋለች፡፡

በዓለም አቀፍና ከሦስቱ አገሮች በተውጣጡ የዘርፉ ሊቃውንት የግድቡን ፕሮጀክት አስመርምራለች፡፡ ምክረ ሐሳብ ተቀብላለች፡፡ የግድቡ ዲዛይን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑንም በዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን አረጋግጣለች፡፡ በተለይ ዋናው የኃይል ማመንጫ ግድብ በጠንካራ አለት ላይ ያረፈ መሆኑን፣ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደማያሠጋው፣ በብዙ ሺሕ ዓመታት አንድ ጊዜ ጎርፍ ቢከሰት እንኳ ማሳለፍ እንደሚችልና አስተማማኝ መሆኑንም በጥናት  አረጋግጣለች፡፡

     በሒደቱ የባለሙያዎች ቡድን ባቀረበው ምክረ ሐሳብ መሠረት ቀጣዩ ሥራ ምክረ ሐሳብን ተግባራዊ ለማድረግ የሦስቱን አገሮች (ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ) ማዕቀፍ ማደራጀት ነበር፡፡ ሦስቱ አገሮች ተገናኝተውም መነጋገራቸው አይዘነጋም፡፡ ያም ሆኖ ግብፅ በማዕቀፉ አባላት ላይ ተቃውሞ ከመሰንዘር አልተቆጠበችም ነበር፡፡

    ኢትዮጵያና ሱዳን ከሦስታችንም አገሮች የተውጣጡ ባለሙያዎች ሥራውን መከታተል ይችላሉ ሲሉ፣ ግብፅ ግን ‹‹አይሆንም የዓለም አቀፍ ሙያተኞችም ካልገቡበት አሻፈረኝ›› እስከ ማለት ደርሳ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ የአተገባበሩን የማዕቀፍ ኮሚቴ ለማቋቋም ሌላ ዓለም አቀፍ ኮሚቴ አያስፈልግም ብትባልም አይሆንም አለች፡፡ ይህንንም ‹‹እሺ›› ቢሏት ሌላ ተቃውሞ ማምጣቷ አይቀርም ነበር፣ ደግሞም አምጥታለች፡፡  ግብፅ በዓባይ ላይ የቀረበን ሐሳብ ከመቃወም ሌላ ሥራ የላትም እስኪባል ድረስ ስትጥል ስታነሳ ከረመች፡፡

ግድቡ ከተጀመረበት ባለፉት 11 ዓመታት ውስጥ ግብፅ የግድቡን ሥራ ለማወክና በጋራ ላለመሥራት ብዙ ርቀት ሄዳለች፡፡ አንዴ ‹‹የግድቡ ሆድ ሰፍቷልና ይጥበብ›› ስትል፣ ሌላ ጊዜ ‹‹የግድቡ ቁመት ይጠር›› ብላለች፡፡ ሌላ ጊዜ ግድቡ ቢደረመስ አደጋ ያስከትልብኛል ስትል፣ ሌላ ጊዜ የውኃ ድርሻዬን መጠን ይቀንስብኛለች እያለች ለስምምነት የሚደረጉ ጥረቶችን ሁሉ እያጓተተች፣ ቋሚ መንግሥት እስኪመሠረትና እስኪወስን ጠብቁኝ እያለች አስተጓጉላለች፡፡ ሁሉም አሉታዊ ጥረቶች ግን ፕሮጀክቱን ከዳር ከማድረስ አላወኩም፡፡

      ከሁሉ በላይ በምንገኝበት የዕውቀትና የመረጃ ዝመን ለሕዝቦቿም የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ደክማለች፡፡ ዓባይ የግብፅ ብቻ ነው ትላቸዋለች፡፡ ለእኛም ጭምር የኢትዮጵያ መንግሥት የግድቡ ሥራ እየተገባደደ ነው የሚለውት ውሸት ነው፣ የግድቡ ሥራ ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ገጥሞታል፣ ኢትዮጵያ ወጪውን መሸፈን አልቻለችም፣ ሕዝባዊ ተቃውሞም ተነስቶበታል፣ ወዘተ እያለች ወገኖቿን ለማጀገን እኛን ደግሞ ተስፋ ለማስቆረጥና ጥርጣሬ ውስጥ ለመክተት በሚዲያዎቿና በምሁራኖቿ አማካይነት ሰፊ ቅስቀሳ ስታካሂድ ኖራለች፡፡ 

     ‹የግድቡን አካባቢ በአውሮፕላን ልትመታ ትችላለች› እያስባለች የሥነ ልቦና ሰለባ ዘመቻ ታደርጋለች፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርሱና ከመንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና ለማቃቃር፣ በዚህም ምክንያት የግድቡን ሥራ ለማሰናከል ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፡፡ ለዚህም የተለያዩ ሥልቶችን ትጠቀማለች፡፡

    የመጀመርያ ሥልቷ የኢትዮጵያን ሕዝብ በብሔር እየከፋፈለች ማቆሚያ በሌለው የእርስ በርስ ሽኩቻ እንዲወጠር ማድረግ ነው፡፡ የትግራይን ሕዝብ በወያኔ አማካይነት ወደ የማያባራ ጦርነትና ከወገኑ ጋር የማጋጨት ሥራ ውስጥ ከተዋለች፡፡ ኦሮሞን በአማራ ላይ ለማስነሳት የተጀመረ የአፍራሽ ኃይሎች ሴራ ዛሬም ብልጭ ድርግም እያለ ቀጥሏል፡፡ በብሔር ብሔረሰቦች ካባ የተሸፈኑ ነፃ አውጭ ተብዬዎችና አማፅያንን በየቦታው እየደገፈች፣ ቀላል የማይባል ትርምስ ስፖንሰር ማድረጓ በመረጃ ተደጋግሞ የተረጋጋጠ ነው፡፡

      ኦሮሞ ኢትዮጵያዊነቱን እንደሚጠራጠር የሚያወሩና እንዲገነጠል የሚገፋፉ፣ በአማራው ላይ ጥላቻ እንዲያድርበት ከአፄ ምኒልክ ያለፈ ታሪክ ውስጥ መጥፎ መጥፎ የሚሉትን እየለቀሙ ዘረኝነትን የሚያራግቡ የፌስቡክ አርበኞች ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ከእነዚህ ሴረኛ ዜጎች የጥፋት ድግስ በስተጀርባ የግብፅ እጅ አለበት፡፡ ማንኛውንም የግብፅ እንቅስቃሴ ግድቡን ለማሰናከል ከሚደረግ ዘመቻ ጋር አያይዘን ማየት አለብን፡፡ ከዚሁ ጋር አብሮ መታየት ያለበት የግብፅ መንግሥት በሽብርተኝነት የተፈረጁ ቡድኖችን በገንዘብ እያማለለ