Get Mystery Box with random crypto!

Congratulation هنيأ لكم እንኳን ደስ ያለን ፣ እንኳን ደስ ያለዎ ሼይኻ | NidaTube -ኒዳ ቲዩብ

Congratulation
هنيأ لكم
እንኳን ደስ ያለን ፣ እንኳን ደስ ያለዎ

ሼይኻችን ዶ/ር ሙሐመድ ሐሚዲን አብዱሰመድ በታሪክ ምርምርና ጥናት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ በማጠናቀቃቸው እንኳን ደስ አለዎ ለማለት እወዳለው

ሼይኽ መሐመድ ሀሚዲን ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትልቅ ተስፋ የሚጣልባቸው ታላቅ አሊም ናቸው::

ለሃገራቸውን ሙስሊሞች ኢስላማዊ እውቀት እንዲስፋፋ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን እየተቀዛቀዘ የመጣውን የቂርዓት ክፍተት ለመሙላት የዳዕዋ ቲቪን በመመስረት ለመላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም በየቤቱ ኢስላማዊ ትምህርቶችን በቋሚነት እንዲከታተል ማድረግ ችለዋል::

ከዚህ በበለጠም የኡለሞቻችን በሞት እና በተለያዩ ችግሮች መመናመን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በመረዳት ተተኪ አሊሞችን እና ዱዓቶችን ለማፍራት ትልቅ ኢስላማዊ ተቋም ለመገንባት ታላቅ ፕሮጀክት ነድፈው ወደ ተግባር በመግባት ለኡማው ከሚያስብ ታላቅ አሊም የሚጠበቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ::

ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል ታላላቅ ስራዎችን በእድሜያቸው ለመስራት እየለፉ የሚገኙ እኚህን የመሰሉ ታላቅ አሊም በውስጣችን መገኘታቸው ለሁላችንም ትልቅ እድል ሲሆን በእውቀታቸው ከመጠቀም በተጨማሪ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተጨንቀው ለማሳካት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፕሮጀክቶቻቸውን ማገዝ ከሁላችን ይጠበቃል::

ሼይኻችን ዶ/ር መሐመድ ሀሚዲን የዶክትሬት ድግሪያቸውን በስኬት በማጠናቀቃቸው በድጋሚ እንኳም ደስ አለዎት እያልኩኝ አላህ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እንዲለግሶት ፣ኡማውም ከእርሶ ብዙ የሚጠቀም ያድርገው ዘንድ መልካም ዱዓዬ ነው

@nidatube