Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ ጸረ ኑክሌር ኃይሏ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዘች የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የ | NidaTube -ኒዳ ቲዩብ

ሩሲያ ጸረ ኑክሌር ኃይሏ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዘች

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጸረ ኑክሌር ኃይላቸው በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዙ፡፡

ፑቲን ከገቡበት የዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከምዕራባዊ ሃገራት ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ጦሩ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ እንዲሆን ያዘዙት፡፡

ዛሬ እሁድ ከከፍተኛ ባለስልጣናቶቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል የሆኑ ሃገራት ጠንከር ያለ መግለጫ እያወጡ መሆኑንና ማዕቀቦችን እየጣሉ በመሆኑ ጸረ ኑክሌር ኃይሉ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዋል፡፡

ፑቲን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎችን በሚወስዱና ጣልቃ በሚገቡ ሃገራት ላይ ጠንከር ያለ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡

አል ዐይን

@nidatube