Get Mystery Box with random crypto!

በየመን አንድ ዐይን ያለው ህፃን ተወለደ ህጻኑ በምድር ላይ በህይወት መቆየት የቻለው ለ7 ሰዓታት | NidaTube -ኒዳ ቲዩብ

በየመን አንድ ዐይን ያለው ህፃን ተወለደ
ህጻኑ በምድር ላይ በህይወት መቆየት የቻለው ለ7 ሰዓታት ብቻ ነው

አለማችን ብዙ ለማመን የሚከብዱ አስደናቂ ነገሮችን እያስተናገደች ሲሆን፤ ከሁለት ቀናት በፊትም በየመን የተፈጠረው አዲስ ክስተት በርካቶችን እያነጋገረ ነው።

ክስተቱ የተፈጠረው በየመኗ አል-በይዳ ግዛት በምግተኘው የራዳአ ከተማ ሲሆን፤ በተከማዋም በሚገኝ ሆስፒታል አንድ ዐይን ያለው ህፃን መወለዱ ተሰምቷል።

በአል-ሂላል እስፔሻላይዝድ ሜዲካል ሆስፒታል የህክምና ምንጮች እንደገለፁት፤ ህጻኑ ከሁለት ቀናት የተወለደ ሲሆን፤ ከተወለደ ብዙም ሳይቆይ ህይወቱ ማለፉን ጠቁመዋል።

ህፃኑ ወደ ማሞቂያ ክፍል ከተወሰደ ከሰባት ሰዓታት በኋላ ህይወቱ ማለፉን የሆስፒታሉ ምንጮች አስታውቀዋል።

አል ዐይን

@nidatube