Get Mystery Box with random crypto!

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሔደ ነው። ተፈታኝ | ትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሔደ ነው።

ተፈታኝ ተማሪዎችን የመመዝገብ ሥራ ከየካቲት 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

ምዝገባ የጀመሩ አካባቢዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ምዝገባ ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች በቀጣይ ምዝገባውን እንደሚያካሒዱ የአገልግሎቱ ም/ዋ/ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ገልጸዋል።

በመደበኛ እና በማታ መርሐግብር የመልቀቂያ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች ይከናወናል የተባለ ሲሆን በግል፣ በርቀት እና በበይነ መረብ ተምረው የሚፈተኑ ተማሪዎች ምዝገባ በክ/ከተማ፣ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ የትምህርት ጽ/ቤቶች እንደሚካሔድ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል።

@News_For_Student
@News_For_Student