Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስኮቻቸው የፈቃድ ወቅታ | ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስኮቻቸው የፈቃድ ወቅታዊ መረጃን ይፋ አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ የ 382 ተቋማት ወቅታዊ የፈቃድ መረጃን ይፋ የተደረገ ሲሆን፦

◉ 366 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
- 5 የግል ዩኒቨርሲቲዎች
- 6 የግል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች
- 6 ኢንስቲቲዩቶች
- 349 የግል ኮሌጆች

◉ 16 የመንግሥት ከ/ት/ተቋማት
- 4 የርቀት ትምህርት ፈቃድ የወሰዱ
- 12 የመደበኛ ትምህርት ፈቃድ የወሰዱ

የተቋማቱን የትምህርት መስኮች የፈቃድ ጊዜ ያለበትን ደረጃ ለማሳየት በየትምህርት መስኩ፣ በካምፓሱ እና በፈቃድ ጊዜው ላይ በአረንጓዴ፣ በቢጫ፣ በቀይ እና በወይን ጠጅ ቀለማት ምልክት ተደርጎበታል፡፡

አረንጓዴ የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ከ6 ወራት በላይ የሚቆይ እና አዲስ ተማሪ መመዝገብ የሚችሉ

ቢጫ የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ከ1 እስከ 6 ወር በላይ የሚቆይና አዲስ ተማሪ መመዝገብ የሚችሉ፡፡ ነገር ግን በቀሩት 6 ወራት ፈቃድ ሳያድሱ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡

ቀይ ቀለም የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ያለፈ ስለሆነ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡ ፈቃድ አላደሱም፡፡

ወይን ጠጅ ቀለም የተደረገባቸው
- ያቋረጡ ስለሆነ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡ የተመዘገቡ ተማሪዎች ግን ማስጨረስ ይችላሉ፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ ያገኙበትን የትምህርት መስክ፣ ካምፓስ እና መርሐግብር አሟልቶ የያዘና በየጊዜው ወቅታዊ የሚደረግ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦ https://bit.ly/43Z1Rck

@News_For_Student
@News_For_Student