Get Mystery Box with random crypto!

NEW PHARMACY and NURSING

የቴሌግራም ቻናል አርማ newepharmacy — NEW PHARMACY and NURSING N
የቴሌግራም ቻናል አርማ newepharmacy — NEW PHARMACY and NURSING
የሰርጥ አድራሻ: @newepharmacy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.70K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ግሩፕ :- 👉 ጤና ነክ ትምህርቶች
👉 coc ጥያቄ ከነ መልሶቻቸው
👉 update information
👉 አዳዲስ የስራ ማስታወቂያ
ለማንኛውም አስተያየት @EBROGC

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-16 15:50:26 #ለሴቶች... በውስጥ መስመር ለተጠየቁት
.
የእርግዝና መከላከያዎችን የሚመለከቱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው :-
.
#1 በወር አበባ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ቢደረግ እርግዝና ይከሰት ይሆን ?

የወር አበባን በምታይ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የምታደርግ ሴት የማርገዝ ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አይከሰትም ለማለት አይቻልም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የወር አበባ ከማለቁ በፊት እንቁላል ሊፈጠር ስለሚችልና ወይንም ደግሞ የወንድ ዘር በማኅፀን ውስጥ እስከ 3 ቀን ወይንም ከዚያ በላይ የሚቆይበት አጋጣሚ ስለሚኖር ነው፡፡

#2 ጡት ማጥባት እርግዝናን ይከላከላል ?

ጡት ማጥባት የእንቁላል መፈጠርን የሚከላከል ቢሆንም የሚቆይበት ጊዜ ግን ለጥቂት ወራት ብቻ ስለሆነ ሰውነት ወደቀድሞ ሁኔታው በሚመለስ ጊዜ የማርገዝ ዕድልም አብሮ ስለሚመለስ ጡት ማጥባት እርግዝናን የሚከላከልበት ጊዜ ውስን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

#3 የመጀመሪያ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ላልተፈለገ እርግዝና ያጋልጣል ?

አዎን! ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላልተፈለገ እርግዝና ላያጋላጥ ይችላል ብለው የሚያስቡ አንዳንዶች ያሉ ቢሆንም ይህ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ሕመምና ደም መፍሰስ ሊያጋጥም የሚችል ቢሆንም እርግዝናን ከመከላከል ጋር ግን ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

#4 የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ምን ያህል እርግዝናን ይከላከላሉ ?

የወሊድ መቆጣጠሪያዎች በትክክለኛው መንገድ ከተተገበሩ ከ90% በላይ የሚሆን የመከላከያ አቅም ያላቸው ሲሆን ተአቅቦ ግን ጥርጥር የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጣሪያ ለመጠቀም በሚታሰብ ጊዜ የትኛውን ዓይነት እንደምንመርጥና አጠቃቀሙን በተመለከተ ሐኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡

#5 በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሁለት ኮንዶሞች ደርቦ መጠቀም በእርግጥ እርግዝናን የበለጠ ይከላከላል?

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሁለት ኮንዶምን ደርቦ በመጠቀም የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው ያስባሉ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ሲሆን ይባስ ብሎ በሚፈጠረው ፍጭት (Friction) ምክንያት የኮንዶም መቀደድ በማስከተል ላልተፈለገ እርግዝና ለአባላዘር በሽታ የመጋለጥን ዕድል በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ሁለት ኮንዶሞችን ደርቦ መጠቅም አይመከርም፡፡

#6 የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን መውሰድ ወዲያውኑ
እርግዝናን ይከላከላል?

የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች አጠቃቀም እና የሚወሰዱበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ እርግዝናን ለመከላከል ጠቃሚ ነው፡፡ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን የወር አበባ በመጣ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አምስተኛው ቀን ውስጥ መጀመር ወዲውኑ ከአልተፈለገ እርግዝና የሚከላከል ሲሆን፣ ከዚያ ጊዜ ውጭ ከመጀመሩ ግን ወዲያውኑ የመከላከል አቅም ስለማይኖረው ኮንዶምን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡

#7 ሁሉም የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ከአባለዘር በሽታዎች ይከላከሉ ይሆን?

ከወሊድ መቆጣጠሪያዎች ውስጥ ኮንዶምን መጠቀም ብቻ ከአባላዘር በሽታ ራስን መከላከል የሚቻልበት ዋነኛው መንገድ
ነው፡፡

#8 የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች የሰውነት ክብደት ይጨምራሉ?

አንዳንድ ሴቶች የሰውነት ክብደት መጨመርን እንዳስከተለባቸው የሚናገሩ ሲሆን ምክንያቱም የምግብ ፍላጎትን መጨመርን ማስከተሉና ፈሳሽ በሰውነታችን እንዲቀመጥ ማድረጉ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ስለዚህም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠነኛ የሚባል የሰውነት ክብደት መጨመርን ያስከትላሉ፡፡

#9 የወሊድ መቆጣጠሪያን መጠቀም መሃንነትን ያስከትላል?

አያስከትልም! ሆርሞኖችን በውስጣቸው የያዙ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ መሃንነትን ያስከትላሉ ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም እነዚህን የወሊድ መቆጣጠሪያዎች መካንነትን እንደማያስከትሉ ሊያውቁት የሚገባ እውነታ ነው፡፡

#10 ኮንዶምን በሌሎች ቁሳቁሶች መተካት ይቻላል?

በፍፁም አይቻልም! በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን በሌሎች እንደ ላስቲክ፣ ፈኛ፣እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ተክቶ መጠቀም በፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እና ከአልተፈለገ እርግዝናም ሆነ ከአባላዘር በሽታም በጭራሽ እንደማይከላከል ሊያውቁት ይገባል፡፡


መረጃ
የማህፀን ና ፅንስ እስፔሻሊስት


Share Link ➟ @NEWEPHARMACY Share

@EBROGc 4any comment

https://t.me/NEWEPHARMACY
1.2K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 11:33:38 anemia is associated with___?

A. Lamivudine

B. Nevirapine

C. Zidovudine

D. Stavudine
1.2K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 17:18:25 ለጓደኞቻችሁ t.me//NEWEPHARMACY ን invite አድርጉ
1.1K views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 13:50:01
የተጣበቁ መንትዮች | Conjoined Twins
~~~

የተጣበቁ መንትዮች ከሰላሳ ሺህ አንድ ሊወለድ የሚችል የተፈጥሮ ሁነት ነው። dicephalus paraphagus ይባላል በምስሉ እንደምትመለከቱት ሁለት ጭንቅላት አንድ ደረት ፣ ሁለት እጅና እግር ያለው ነው። ተጣብቆ ከተወለደ መንታ ምድብ የሚመደብ ሲሆን ሁኔታው እጅግ ያልተለመደ ክስተት እንደሆነ ሳይንስ ያብራራል።

የተለያዩ የተጣበቁ የመንታ አይነቶች ያሉ ሲሆን ስማቸው እንደተጠባበቀው አካል ይለያያል። በጭንቅላት መጠባበቅ (craniophagus) ፣ ደረት ለደረት (Thoracophagus)፣ ዳሌ አካባቢ (pagophagus) ሆድ ለሆድ (omphalophagus ) ወዘተ ናቸው።

የዚህ ሁኔት መንስኤ ስንመለከት በእርግዝና ወቅት አንድ እንቁላል ከወንድ ዘር ፍሬ ጋር ውኅደት ሲያድግ ለሁለት እና ከዚያ በላይ ሊከፈል ይችላል። በዚህ ሂደት የፅንሱ ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ መከፈል የመንታ እና ከዚያ በላይ እርግዝና ይፈጥራል (monochoronic twin)።

ፅንሱ የተከፋፋለበት ጊዜ (ወቅት) በረዘመ ቁጥር (ከ13 ቀናት በኋላ ከሆነ) የተባበቀ መንታ የመሆን እድሉ የሰፋ ይሆናል።

የዚህ አይነት መንታ በእርግዝና ወቅት በአልትራሳውንድ ምርመራ የሚታወቅ ሲሆን ጥብቅ ክትትል በማድረግ በ32-34 ሳምንት በኦፕራሲዮን እንዲወለድ ይደረጋል።

ከወሊድ በኋላ የተጠባበቁ መንታዎች እንደተጠባበቁበት አካል መጠን በረቀቀ ቀዶ ጥገና መለያየት አልያም እንደተፈጠሩ መተው ይቻላል።

የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት


t.me/NEWEPHARMACY
1.2K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 12:54:01
1.1K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:55:47 #የደም #ግፊት #መጨመር #ስንል #ምን #ማለታችን #ነው?
??

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

የደም ግፊት መጨመር የሚከሰተዉ ቀጫጭን የደም ስሮች መኖር እና የደም መጠን መጨመር በልብ መኮማተር እና መለጠጥ ላይ ጫና ሲፈጥር ነዉ፡፡የደም ግፊት መጠን የሚልካዉ የልብ ጡንቻ የሚኮማተርበትን (Systole) በ የልብ ጡንቻ የሚፍታታበት(Diastole) ጊዜ በሚሰራ ስሌት ነዉ፡፡ የደም ግፊት ልባችን በምትረጨው የደም መጠን እና ደም በደም ስሮቸችን ውስጥ ሲያልፍ በሚኖር የመቋቋም ኃይል ይወሰናል።
ብዙ ደም ልባችን በረጨች መጠን የደም ትቦ ይጠባል ከዚያም የደም ግፊታችን መጠናችን ይጨምራል ማለት ነው። ምንም አይነት ምላክት ሳይኖረው ለአመታት የደም ግፊት መጠናችን ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ይህም የደም ቧንቧዎቻችንን ይጐዳቸዋል። ያልተቆጣጠርነው ከፍተኛ የደም ግፊት ለከባድ የጤና ችግር የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል ለዚህም የልብ ድካምና የደም መርጋት ተጠቃሾች ናቸው።
አንድ ሰዉ የከፍተኛ ደም ግፊት ተጠቂ ነዉ የምንለዉ የደም ግፊት መጠኑ ከ 140 በ 90 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ በላይ ሲሆን ነዉ፡፡

የደም ግፊት መጨመር ደረጃዎች
ከፍ ያለ የደም ግፊት - ሴሰቶሊክ ( የላይኛው ) ከ 120 – 129 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ ሲሆን እና ዳይስቶሊክ ( የታችኛው ) ከ80 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ በታች ሲሆን
ደረጃ 1 – ሴሰቶሊክ ( የላይኛው ) ከ 130 – 139 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ ሲሆን እና ዳይስቶሊክ ( የታችኛው ) ከ 80- 89 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ ሲሆን
ደረጃ 2 – ሴሰቶሊክ ( የላይኛው ) ከ 140 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ በላይ ሲሆን እና ዳይስቶሊክ ( የታችኛው ) ከ 90 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ በላይ ሲሆን

የደም ግፊት ምልክቶች
የራስ ምታት
የእይታ ችግር(ብዥ ማለት)
ደረት ፣ ማጅራት እና ጆሮ የመጨምደድ ስሜት
ለመተንፈስ መቸገር
የተዛባ የልብ ምት
የሰዉነት ድካም

የደም ግፊት መከላከያ መንገዶች
ጤናማ የሰውነት ክብደት
በየጊዜው እንቅስቃሴ መስራት
የጨው አጠቃቀማችንን መቀነስ
አልኮል መጠጦችን አለመጠጣት/መቀነስ
ጭንቀትን መቀነስ
ፖታሲየም:- በፖታሲየም የበለፀጉ ምግቦች በደም ግፊት በሽታ ከመያዝ ይከላከላሉ።
ፖታሲየም ከተለያዮ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ከእንሰሳትተዋጽኦዎች እና ከአሳ እናገኛለን።
የአሳ ዘይት፦ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የምናገኝው ከአሳ ሲሆን የደም ግፊትን በመከላከል ይረዳናል።
ነጭ ሽንኩርት፦ የደም ግፊት መጠንን እና ኮሌስትሮልን በማስተካከል ከፍተኛ ጥቅም አለው።

የደም ግፊት ያለባቸው ሰወች አመጋገብ ምን መምሰል ይኖርበታል

መመገብ ያለባቸው ነገሮች
ጎመን
ሰላጣ
ቀይስር
ቅባቱ የወጣለት ወተት
እርጎ
ሙዝ
አሳ
ጥራጥሬ
ነጭ ሽንኩርት ያለበት ምግብ
የወይራ ዘይት

መመገብ የሌለባቸው ነገሮች
ጨው
የታሸጉ ሾርባዎች
የታሸጉ ቲማቲሞች
ስኳር
ቀይ ስጋ
ቂቤ
የዶሮ ቆዳ
አልኮ


t.me/NEWEPHARMACY
1.6K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 08:18:10 ስለ pharmacology ተከታታይ ትምህርት ልንጀምር ስለሆነ ሌሎች ላልደረሳቸው ተማሪዎች እንዳያመልጣቸው
ቢያንስ ለ10 ሠዎች ሸር ያርጉ፡፡ወይም
በየ ጉርፑ ሸር በማድረግ ሌሎች ያልደረሳቸው እንዲገቡ እንተባበራቸው ፡፡


ስለ ትምህርት
ስለ coc
እነዲሁም pdf ፡ መፀሀፎች ለማግኝት ከታች ያለውን ይንኩት
join
t.me/NEWEPHARMACY
313 viewsHERO, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:19:33
578 viewsእኔ ሰው ነኝ, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ