Get Mystery Box with random crypto!

ንዋየ ቅድሳት

የቴሌግራም ቻናል አርማ newayekidisat — ንዋየ ቅድሳት
የቴሌግራም ቻናል አርማ newayekidisat — ንዋየ ቅድሳት
የሰርጥ አድራሻ: @newayekidisat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.07K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ጹሑፎች፣አበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል.በተጨማሪም ከኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤ/ክ ገድላት ላይ የተገኙ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድላቸው በየቀኑ ይቀርብበታል
ለሀሳብ
አስተያየት(ለ #paid_promotion)
@Newayebot ን ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-22 07:55:00 @newayekidisat
@newayekidisat

#በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው

ዕለተ ዐርብ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አውቀውስ
ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» በማለት
እንደ ተናገረው (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፲፰) ይህ ዕለት
የአይሁድ ካህናት ንጹሕና ጻድቅ የኾነውን
ጌታ ያለበደሉና ያለጥፋቱ በሐሰት ወንጅለው
የሰቀሉበት፤ ጌታችንም በፈቃዱ በመስቀል
የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዅሉ
መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል
በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ
ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን
ነው (ማቴ. ፳፯፥፴፭-፸፭)፡፡ በዚያን ጊዜ
አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት
አይቶ ተጸጸተ፤ ሠላሳውንም ብር ለካህናት
አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ‹‹ንጹሕ ደም
አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ›› አለ፡፡ @newayekidisat እነርሱ
ግን ‹‹እኛስ ምን አግዶን? አንተው
ተጠንቀቅ፤›› አሉ፡፡ ይሁዳም ብሩን በቤተ
መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት
አለቆችም ብሩን አንሥተው ‹‹የደም ዋጋ
ነውና ወደ መባዕ ልንጨምረው
አልተፈቀደም፤›› አሉ፡፡ ተማክረውም
ለእንግዶች መቃብር የሚኾን የሸክላ ሠሪ
መሬት ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ
ድረስ ‹የደም መሬት› ተባለ (ማቴ. ፳፯፥፫-
፱)፡፡
ዕለተ ዓርብ እኛ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት
(ቁራኝነት) እንኖርበት የነበረው የጨለማ
ሕይወት ያከተመባትና ፍጹም ድኅነት
ያገኘንባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች
ዅልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ የክርስቶስን
ሕማሙን፣ ስቅለቱንና ሞቱን የምናስብበት
ጊዜ ነው፡፡ @newayekidisat በሮማውያን ሕግና ሥርዓት
መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት፤
የሕይወት መቅጫ አርማ ኾኖ ሳለ ለእኛ ግን
የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤
በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን
በዚህም ምክንያት ዕለቱ ‹መልካሙ ዓርብ›
በመባል ይታወቃል፡፡

#forward በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ
@newayekidisat
@newayekidisat
451 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 07:01:22 @newayekidisat
@newayekidisat

#በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው

ዕለተ ሐሙስ

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው፤ ፍጹም
አምላክ መኾኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት
ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ዕለቱ ‹ጸሎተ
ሐሙስ› በመባል ይታወቃል፡፡ @newayekidisat
ትሕትናንና
ፍቅርን እንደዚሁም የአገልግሎትን ትርጕም
ለማስረዳትና ለማስገንዘብ ጌታችን የደቀ
መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ዕለቱ ‹ሕጽበተ
ሐሙስ› በመባልም ይጠራል፡፡ ጌታችን የደቀ
መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜም፡- «…
ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?…
እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስኾን
እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ
በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል፤››
በማለት የእርሱን አርአያነት መከተል
እንደሚገባ አስተምሯል (ዮሐ. ፲፫፥፲፪-፳)፡፡ @newayekidisat
ዕለተ ሐሙስ ጌታችን ‹‹… ይህ ስለ እናንተ
በመስቀል ላይ የሚቈረሰው ሥጋዬ ነው፤
እንካችሁ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ
ደሜ ነው፤ ከእርሱ ጠጡ፤›› በማለት
ምሥጢረ ቍርባንን የመሠረተበት
የጀመረበት ቀን በመኾኑ ‹የምሥጢር ቀን›
ተብሎም ይጠራል (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፱)፡፡ @newayekidisat
ይኸውም ምእመናን ሥጋውንና ደሙን
ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት
እንዲኖረን፤ ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም
ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት
መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል
ነው፡፡ አይሁድ ጌታችንን የያዙበት ቀን ስለ
ኾነ በዚህ ዕለት በለኆሣሥ (ብዙ የድምፅ
ጩኸት ሳይሰማ) የቅዳሴ ሥርዓት
ይፈጸማል፡፡ @newayekidisat መላው ሕዝበ ክርስቲያን
የሕጽበት፣ የምሥጢር፣ የጸሎት ቀን
በተባለው በዚህ ዕለት በንስሐ ታጥበው፣
ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን
በአጽንዖት ታስተምራለች፡፡

#forward በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ
@newayekidisat
@newayekidisat
472 views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 07:51:08 @newayekidisat

#በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው

ዕለተ ረቡዕ

ይህ ዕለት ደግሞ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና
ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ
ምክር የጀመሩበት ቀን ነው፡፡ በዚህም
ምክንያት ዕለቱ ‹የምክር ቀን› በመባል
ይጠራል፡፡

@newayekidisat
463 views04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 08:38:05 " ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና "
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ

#መልካም_ቀን
@newayekidisat
480 views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 08:35:30 @newayekidisat

#በሰሙነ_ሕማማት_የሚገኙ_ዕለታትና_ስያሜአቸው

ዕለተ ሠሉስ (ማክሰኞ)

ይህ ቀን ጌታችን ሰኞ በተናገረውና ባደረገው
ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም
መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡
በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት
ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ @newayekidisat ጥያቄውም ጌታ
ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት
ለጸሐፍትና ፈሪሳውያን ይኸውም ትምህርት
ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ
መፍታትን ‹‹በማን ሥልጣን ታደርጋለህ?
ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?» የሚል ነበር
(ማቴ. ፳፩፥፳፫-፳፯)፡፡ ጌታችንም «…
እውነት እላችኋለሁ፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች
ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት
ይቀድሙአችኋል፤›› ሲል አስተምሯል (ማቴ.
፳፩፥፳፰)፡፡

#forward በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ
@newayekidisat
@newayekidisat
464 views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 13:14:54 @newayekidisat
@newayekidisat

በሰሙነ ሕማማት የሚገኙ ዕለታትና
ስያሜአቸው

ዕለተ ሰኑይ (ሰኞ)

ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ (የቤተ
መቅደስ መንጻት) እና መርገመ በለስ
የተፈጸመበት ዕለት ነው (ማቴ.፳፩፥፲፰-፳፪፤
ማር. ፲፩፥፲፩፤ ሉቃ. ፲፫፥፲፮)፡፡ ወንጌላዊው
ቅዱስ ሉቃስ፡- ‹‹… ለአንድ ሰው በወይኑ
አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው፡፡ @newayekidisat
ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም
አላገኘም፤›› በማለት በበለስ ስለ ተመሰለው
የሰው ልጅ እና በንስሐ ተመልሶ በሕይወት
መኖር እንደሚገባው እግዚአብሔር ኢየሱስ
ክርስቶስ ማሳሰቡን ያስረዳል፡፡ @newayekidisat በለሷ እንደ
ጠወለገችና እንደ ተቈረጠች ዅሉ፣ ንስሐ
አልገባም አልመለስም የሚሉም የምግባር
ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቈረጡ፤
እንደዚሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ
ቅዱስ በግልጽ ይናገራል፡፡ በለስ የተባለች
ቤተ እስራኤል፤ ፍሬ የተባለ ደግሞ
ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ ዅላችንም ቤተ
እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት እና ምግባርን
አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ
አልባ እንዳንኾን፣ ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር
የመጽሐፉን ቃል መፈጸም ይጠበቅብናል፡፡


#forward በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ
@newayekidisat
@newayekidisat
517 views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 00:06:47 አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣
አቤቱ እባክህ አሁን አቅና.

እንኳን ለሆሳዕና በዐል አደረሳችሁ አደረሰን
535 views21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 20:31:06 #ሆሳዕና

ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ሆሼዕናህ Â የሚል ሲሆን
ትርጉሙም እባክህ አሁን አድን Â ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ
በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣
አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡
 መዝ.117፡25-26 የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ
ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት
ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም
የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም Â በማለት ጌታችንን በክብር
መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን
ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡
በሌላ አነጋገር ይህ ዕለት የጸበርት እሑድ Â /Palm Sunday/
ይባላል፡፡ ታሪካዊ አመጣጡ የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት
መገለጫ ሆኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ
ነው፡፡ ይኸውም ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ጨርሳ ልማደ እንስት
ከተቋረጠባት በኋላ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ
ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ
የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን
አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ
ድርብ ደስታ በገለጡ ጊዜ፣ እንዲሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ
እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ
እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ አደባባይ
ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር
ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን
መስቀሉ /ሉቃ.22፤18/ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አእሩግ ነጻ
የሚወጡበት ቀን መድረሱን እነርሱ ሳያውቁ እግዚአብሔር ባወቀ ዘንባባ
በመያዝ ዘምረዋል፡፡ እስራኤል ዘንባባ በመያዝ እንዳመሰገኑት እኛም
አስራኤል ዘነፍስ ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን
በየዓመቱ እያስታወስን እናከብራለን፡፡ በዚህ ዕለት ዘንባባ እየተባረከ
ለሕዝቡ ይታደላል፡፡
ሕፃናትና አእሩግ ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል፡፡ Â እያሉ
ዘምረዋል፡፡ ይህ ሁሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት
ሲሆን በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡
ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ
ጸሐፍት ፈሪሳውያን መምህር ሆይ ደቀ መዛሙርትህን
ገሥጻቸውÂ አሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች
ይጮኻሉ Â ሲል መልሶላቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው
ፈሪሳውያንም የዋህ የሆነው ሕዝብ ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ
አድርገዋል፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው በዕለተ ሆሳዕና እሑድ ዘንባባ ይዘው
የዘመሩለትን ጌታ ዓርብ ይሰቀል ዘንድ ይገባል Â ብለዋል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ
ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በዚህም በነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው
ትንቢት ተፈጸመ፡፡እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ
በአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ
ይመጣል፡፡ Â ዘካ.9፡9፤ ማቴ.21፡4፤ ማር.11፡1-10፤ሉቃ.19፡28-40፤
ዮሐ.12፤15፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም
መግባቱ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት
ሲሆንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም
እውነተኛ የኅሊና ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ
መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡
መላእክት በዕለተ ልደቱ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል
በምድር ሰላም ለሰው ሁሉ ይሁን Â /ሉቃ.2፡13/ እያሉ የዘመሩለት
የሰላም ባለቤት ነው፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም ሰላሜን
እሰጣችኋለሁ Â /ዮሐ.14፡27/ ብሎ እንዳስተማረ ያን ሰላም
የሚሰጥበትን ዕለት መቅረቡን ለማመልከት ነው፡፡ በሌላ በኩልም
በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ
የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፣ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡
በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ ቅርብ ሲሆን በእምነት
ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ መሆኑን አስተምሯል፡፡ ስለዚህ
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜያችን ሳትጠልቅ በእምነት
እንፈልገው፡፡ አሞጽ4፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና
የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፣ የተዋረደውንና
የተሰበረውን ልብ አይንቅም፡፡ ኢሳ.66፡2፤ መዝ.50፡17፡፡
ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የሆነ ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች
አህያ እንደተቀመጠ ሁሉ ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት ዛሬም
ያድራል፤ የኅሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ንስሐ ገብተን ጌታችንን
ሆሳዕና በአርያም እያልን ልናመሰግነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡ #eotcmk
(ሐመር ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ መጋቢት/ሚያዝያ 1996 ዓ.ም)
@newayekidisat
@newayekidisat
792 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ