Get Mystery Box with random crypto!

ተወደናል! የማቴዎስ ወንጌል 3 17፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወ | New Life Ministry

ተወደናል!

የማቴዎስ ወንጌል 3
17፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡ አለ።

ክርስቶስ፣ አብ እርሱን በወደደበት ፍቅር እንደወደደን ነግሮናልና ሰማይ ተከፍቶ፣ ''በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው'' ተብሎ የመጣው ድምጽ በአዲስ ኪዳን የእኛ ቃል ሆኗል!

ከእግዚአብሔር ፍቅር ማለትም እርሱ ለእኛ ካለው ፍቅር ሊለየን የሚችል አንዳች የለም! ዮሐንስ በወንጌሉ ውስጥ እራሱን ሲጠራ፣ ''ክርስቶስም ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር'' ብሎ ነው! ይህ ግን ክርስቶስ ከሁሉም የበለጠ ዮሐንስን መውደዱን ሳይሆን ዮሐንስ ከሌሎቹ በተሻለ መልኩ ስለተወደደበት ፍቅር መገለጡ እንዳለው ነው የሚያሳየው! ለእግዚአብሔር ባለህ ፍቅር በመደገፍ እንደ ጴጥሮስ በራስህ ሥራ አትመካ! ይልቁን የተወደድክበትን ፍቅር በማወቅ ስር ስደድ! ምክንያቱም መጽሐፍ፣ '' እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና እንወደዋለን'' ብሎ ስለሚል!

ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጆችና ደስ የተሰኘብን ውድ ልጆቹ ነን! ዋጋችን ክርስቶስ ነውና!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot