Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉን እንችላለን! ወደ ፊልጵስዩስ 4 13፤ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ክርስ | New Life Ministry

ሁሉን እንችላለን!

ወደ ፊልጵስዩስ 4
13፤ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።

ክርስቶስ፣ አብን ለእኛ የተረከ ትክክለኛ የእግዚአብሔር ነጸብራቅ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ማንነታችንን ገልጦ ያሳየን መስታወታችን ነው! በዚህም፣ በእርሱ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ብቻ ሳይሆን ለእኛ ለአማኞች ሁሉ መቻሉን አየን!

''ይህ ለእግዚአብሔር ቀላል ነው'' አትበል! የተፈለገው ለእግዚአብሔር መቅለሉ ሳይሆን የአንተ ቀሎክ መኖር ነው! በመሰረቱ፣ አንድ ወንድማችን እንዳለው፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ከባድም ቀላልም ነገር የለም! ከባድና ቀላል የሰው ቋንቋ ናቸውና!

ወዳጄ፣ ሁሉን መቻል ምንጫችን ከሆነው ከእግዚአብሔር የተካፈልነው ማንነት ነው እንጂ በአነቃቂ ንግግር የሚመጣ የአዕምሮ ውጤት አይደለም! ሁሉን መቻል ተሰቶኛል!

ወንድም ቢንያም ተስፋዬ

@ye_adis_kidan_hiwot