Get Mystery Box with random crypto!

የሽርክ  አይነቶች ሁለት ናቸው ፡- ሽርኩል አክበር ሽርኩል አሰስገር ይባላሉ ሽርኩል | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

የሽርክ  አይነቶች ሁለት ናቸው ፡-

ሽርኩል አክበር
ሽርኩል አሰስገር ይባላሉ


ሽርኩል አክበር (ትልቁ ሽርክ) ፡

ይህ ትልቁ ሽርክ የተባለው ከእስልምና የሚያስወጣ ነው ፡ተውበት ሳያደርግ የሞተም ከሆነ
እሳት ዘውታሪ የሚያደርገው የሆነ ትልቅ ወንጀል ነው፡
ይህ ሽርከል አክበር የተባለው ከአምልኮ ዘርፎችን ከአሏህ ሌላ ለሆነ ፍጡር መስጠት ነው ከነዚህም መካከል

ከአሏህ ሌላን መለመን , ቀብሮች ላይ ማረድ , የሞቱ ሰዎችንም እንዲሁም ጂኖችን መፍራት ይጎዳሉ , ይገላሉ ,ያሳምማሉ በማለት ማመን, እንዲሁም ከአሏህ ሌላ በሆነ አካል እርዳታን መፈለግ  አቅም (ችሎታ) በሌለው ነገር እና የመሳሰሉት የሽርክ አክበር ሁኔታዎች አሉት

ሽርኩል አስገር (ትንሹ ሽርክ):-
ይህ ትንሹ ሽርክ የተባለው ከእስልምና የማያስወጣ ሲሆን ነገር ግን ተውሂድን ያጎድላል ወደ ትልቁ ሽርክም አዳራሽ ነው ፡፡
  
ይህም ሁለት ሁኔታዎች ሲኖሩት

አንደኛው፡- በአካል ወይም በግልፅ የሚደርግ ሽርክ

ከነሱም ውስጥ በንግግር ከሚደረጉት የሺርክ አይነቶች

ከ አሏህ ሌላ በሆነ አካል መማል የአሏህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ

  《من حلف بغير الله فقد كفر او أشرك 》.

[ ከአሏህ ሌላ የማለ በእርግጥም ከፍሯል(ከሀይማኖቱ ወጥቷል) ወይም አጋርቷል].

እንዲሁም (አሏህ እና አንተ ከፈለጋችሁ) የሚለው ንግግር መጠቀም
የአሏህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم አንድን ሰው አሏህ እና አንተ ከፈለጋችሁ ባለ ሰአት እንዲህ አሉት


《 اجعلتني لله ندا !؟!  قل: ماشاء الله وحده》.
[የአሏህ አጋዥ(ረዳት)አደረከኝን፡  አሏህ ብቻውን ከፈለገ በል].

ከተግባር ከሚፈፀሙ የሽርክ አይነቶች  ደግሞ ፡

ልክ እርዝን ማንጠልጠል የሚመጡ አደጋዎችን ይከላከላሉ በማለት ይህ ሰብብ ናቸው ብሎ ካመነ ነው ነገር ግን እነዚህን ነገሮች ራሳቸው ጉዳት ያመጣሉ ብሎ ካመነ ግን ይህ ሽርከል አክበር ይሆናል ፡፡

ሁለተኛው አይነት ከትንሹ ሽርክ

ቀላሉ ሽርክ የሚባለው ነው እሱም ምንድነው ይዩልኝ ይስሙልኝ ወይም በኒያ(በሀሳብ) የሚገኝ የሽርክ አይነት ነው ፡

ይዩልኝ ይስሙልኝ ማለት ምን ማለት ነው ፡ አንድን ስራ ይሰራል ወደ አሏህ የሚያቃርበውን በዚህ ስራው ይፈልጋል የሰዎችን ውዳሴ እና ሙገሳ ፡ ልክ ሶላቱን እንደ ማሳመር ወይም ሶዶቃን(ምፀዋት) ያደርጋል የሰዎችን ውዳሴ ፈልጓ ወይም ድምፁን ያሳምራል ቁርአንን በሚቀራበት ሰአት ሰዎች እንዲያሞግሱት

ይዪልኝ ይስሙልኝ ማለት ከስራ ጋር ከመጣ ሰራውን ውድቅ ያደርገዋል
አሏህ سبحنه وتعالى እንዲህ ይላል

《فمن كان يرجوا لقاء ربه فليعمل عمﻻ صالحا ولا يشرك بعبادة ربه احدا》[الكهف :١١٠ ]

[ ከጌታው ጋር መገናኘትን የሚመኝ ጥሩ ስራን ይስራ በጌታው አምልኮም ላይ አንድንም እንዳያጋራ] {ከሕፍ :110}

እንዲሁም የአሏህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ

☆ أخوف ما أخاف عليكم الشرك اﻷصغر ، قالوا يارسول الله ، وما الشرك اﻷصغر؟ فقال : (الرياء ).

ለእናንተ ከምፈራላችሁ ፍራቻ ትንሹን ሽርክ ነው አሉ ,ሶሀቦች ምንድነው ትንሹ ሽርክ ብለው ጠየቁ ? የአሏህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم
(እዪልኝ ስሙልኝ) ማለት ነው አሏቸው ፡፡

ይህንንም ስራ የሚሰራው የዱንያ ኑሮውን ሊያመቻች ብሎ ሊሠራም ይችላል ልክ ሰዎችን በማሰገድ ላይ ያለ ወይም አዛን የሚልም ሊሆን ይችላል ገንዘብን ለመሰብሰብ  ብሎ እውቀትን መውሰድ  ይገኙበታል  ፡፡

ኢብኑል ቀዮም እንዲህ ይላል ፡-

" ይህ የሽርክ አይነት በጣም ሰፊ እንደ ባህር ነው ማቆሚያ የለውም ፡ ከዚህ ነገር የሚድኑት ጥቂቶቹ ናቸው ፡ በስራው ከአሏህ ፊት ውጪ የፈለገበት ከሆነ ይህ በእርግጥም ሽርክን አሰገኝቷል::

   ሼር JoiN & Share

ሌሎችም የተለያዩ ትምህርቶች ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
http://t.me//@arebgendamesjid
┈┅𝑱𝑶𝑰𝑵 𝑨𝑵𝑫 𝑺𝑯𝑨𝑹𝑬