Get Mystery Box with random crypto!

አንዲት አባቷ የመስጅድ ኢማም የሆነች ልጅ ነበረች። ልጁ በቁንጅናዋ ተማርኮ ዚና እንዲሰሩ ይጠይቃታ | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

አንዲት አባቷ የመስጅድ ኢማም የሆነች ልጅ ነበረች። ልጁ በቁንጅናዋ ተማርኮ ዚና እንዲሰሩ ይጠይቃታል፤ ቆንጆይቱም "እሺ ነገር ግን ሁለት መስፈርቶች አሉኝ እነርሱን ካሟላህ " ትለዋለች። መስፈርቷንም በዚህ መልኩ ትነግረዋለች።
1ኛ) ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።
2ኛ) እንደምታቀው አባቴ የመስጅድ ኢማም ነው እና ስጠኝ እስካልኩህ ግዜ ድረስ መስጅድ እየሄድክ በጀመዐ ሶላትህን ስገድ" ትለዋለች።
:
ልጁም እሺ ብሎ ተስማማ።
ቃሉንና መስፈርቱን ለመጠበቅ ሲል መስጅድ መሄድን አዘወተረ።

በመጨረሻም የሰጣት ግዜም አለቀ።
"ያንን የሰሳጠሁህን መስፈርት ተገበርከው ቃልህንስ በትክክል እያከበርክ ነው" የሚል ጥያቄ አነሳችለት።
እርሱም "አወ! እየተገበርኩ ነው ነገር ግን ቃል ያስገባሁሽን ነገር አላህ ይቅር ይበለኝ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል። መስጅድ በምመላለስበት ሰዓት ወደ አላህ ተመልሻለሁ" አላት።

አርሷም "ማሻ አላህ! እኔም እሺ ያልኩህ ዝሙት ለመስራት ሳይሆን "ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች" በሚለው በዚህ በአላህ ቃል እርግጠኝነት ተሞልቼ ነው።

اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ
ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡
ሱረቱል አንከቡት (45)
http://t.me//@arebgendamesjid
SHARE SHARE